Postlar filtri


መምህር ኤስድሮስ የተባሉት ሊቅ ያስተማሩትን የመንፈስ ልጃቸዉን ሲመክሩ እንዲህ አሉት፡፡

"ልጄ ከመሃይም አትጣላ ፣ ደጋፊው ብዙ ስለሆነ ያሸንፍሃል"

@yismakeworku


"...አሜሪካ አእሮን እንዴት ማጠብ እንዳለባት ታውቃለች። ገና ምድሯን ስትረግጥ አሜሪካዊ የሆንክ ያህል እንዲሰማህ የሚያደርጉ ታላላቅ ሰዎች ያሉባት ሀገር ናት ።
እኛ ሀገር ውስጥ ደግሞ ባደክበት ቀየ ባደክበት ምድር ወዘ ልውጥ እየተባልክ ትኖራለህ።ለሀገርህ ባዳ ሆነህ ትሞታለህ።
አሜሪካን ሀያል ያደረጓት አሜሪካውያን ብቻ አይደሉም፤አምባገነን መሪዎቻቸው ያሳደዷቸው የሌሎች ሀገር ስደተኞች ጭምር ናቸው።
ኢትዮጵያ የተማረ ሰው አጥታ አይደለም፤የተማረ ስለማትወድ እንጂ። ግን ለለውጥ እራስን መስጠት ያስፈልጋል።
አየህ...ለውጥን የሚጠላ ኢትዮጵያዊ የለም።ለውጡ ሆዳቸውን ከሚያጎልባቸው ትቂቶች በቀር።
ችግሩ የለውጡ አካል ለመሆን የሚፈልግ የለም።በሌሎች ሞትና ደም ለመጠርቃት እና ኑሯቸውን ለማደላደል የሚመኙ ብዙ ናቸው።..."

- ኢንጅነር ሻጊዝ እና ዶ/ር ሚራዥ ወደ ሀገር (ኢትዮጵያ )ስለመመለስ ሲመካከሩ (ዴርቶጋዳ መፅሀፍ ላይ)


ያሳዝናል...የስንት ሰው ላብ መና ሆኖ ሲያድር 💔

"አይ መርካቶ.." እንዲል ሎሬቱ


በህይወታችሁ "ፀሀይ" ሊሆኑ ያሰቡላችሁን ሳይሆን "ጨረቃ" የሚሆኑት ጋ አመዝኑ።

ምክንያት...

ጨረቃ በቀን ተደብቃ ብትኖርም ቅሉ በይበልጥ ደምቃ የምትወጣው ሲመሻሽ/ሲጨልም ነውና...

በብርሃናችሁ ጊዜ የሚመጣውን ፀሀይ ሰው ተዉት
ጨለማችሁ ላይ አለሁ የሚለውን "ጨረቃ" ውደዱት

@yismakeworku


#ዴርቶጋዳ

"...ጉንዳኖች ውሀ ሲሻገሩ አይተህ ታውቅ ከሆነ በውሃው ላይ ተያይዘው ተያይዘው ይቆማሉ። ጉንዳኖች ተያይዘው በወንዝ ላይ በሚሰሩበት መንገድ ሌሎች ብዙ ጉንዳኖች ይሻገራሉ። ተያይዘዉ ይሻገራሉ። ተደጋግፈው አስፈሪውን ወንዝ ይሻገሩታል። ባይያያዙና ባይደጋገፉ ግን አይቻላቸውም። አንዲት ጠብታ ዝናብ ለአንድ ጉንዳን ውቅያኖስ ብትሆንም ብዙ ጉንዳኖች አንድ ላይ ከተያያዙ ግን ውቅያኖስ መሻገር ይችላሉ።..."


@yismakeworku


ይህ የምወደው ፎቶዬ ነው!!!
በውቀቱ ስዩምም አንድ ግጥሙ ጋር እንዲህ የምትል ጠንካራ ስንኝ ነበረችው።

".. ከፈጣሪ ይልቅ ፎቶ አንሺ ይራራል
ለጋነታችንን ባለበት ያስቀራል..."

@yismakeworku


የሰው ልጅ የልምምድ ውጤት ነው። በልምምድ እንጅ በመወለድ ብቻ ሰው መሆን አይችልም። ከማፍቀር እስከ መቆርቆር ይለማመዳል። ማፍቀርን ያህል ያህል ነገር እንኳ አውቆ አይወለድም። እርሱን ብቻ አይደለም፤ መጥላትን ሳይቀር ይለማመዳል። ከማወቅ እስከ መናቅ፣ ከመወለድ እስከ መታነቅ፤ ከመድቀቅ እስከማድቀቅ፤ ከመጋባት እስከ መፍታት፤ ከስንፈት እስከ ጥረት ... ከመርመጥመጥ እስከ መፈርጠጥ፣ ከቆመጥ እስከ ነፍጥ...ተለማምዶት እንጅ ተሰጥቶት አይደለም። ከክህደት እስከ እምነት ካልተለማመደ አይችልም።

ከራሱ ያገኘው ማንነት የለውም። ሁሉም በሂደት እና በልምምድ የመጣ ነው። መልኩን ቆላ ሲወርድና ደጋ ሲወጣ ይቀያየራል። ልቡን በየግድሙ ይጥላል። ቀልቡን መቋጠሪያ የለውም። በመለማመድ አሁን የደረሰበትን እንጅ ወደፊት የሚሄድበትን ማንም ሊያውቅ አይችልም።


ክቡር ድንጋይ | ይስማዕከ | @yismakeworku


ለሚመለከተው በሙሉ...

ይሄው በድጋሚ ወዳጄ ለወዳጆችህ ንገርልኝ አለኝ!

ወዳጆቼ በቴሌግራም በነፃ "የእንግሊዘኛ" ቋንቋ እጅግ በጣም በቀላል መንገድ ለመማማር ከፈለጉ አሁን ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) የምሰጣችሁን "ቻናል" ተቀላቀሉ።

"ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቻናላችን @ethioenglizegna የምትገቡ ተማሪዎች ትምህርት መማማር ከጀመርን አምስት ቀናት ስላስቆጠርን ወደ ላይ በመውጣት የተማርናቸውን ተመልከቱ" ሲልም ለእናንተ ለማስተላለፍ ፈልጓል።

ማስፈንጠሪያው ወይም ሊንኩ 👉
https://t.me/+hRhOmsnuXG0zYTA0


አንተ ጥፍራም ደራሲ፣
አንተ ጠኔያም ገጣሚ ፣ አድናቂ ጨረቃ
እፈር በማለትህ ፣ ተወለድኩ አፍሪቃ።
ሀገርህ ተመንገድ ፣ ለልመና ወድቃ፣
እህትህ ተመንገድ ፣ ለምፅዋት ተንፏቃ፣
እናትህ ተመንገድ ፣ ለርጥባን ተንቃ፣
እንዴት ታደንቃለህ ፣ የሰማይ ጨረቃ!!

የቀንድ አውጣ ኑሮ
(ይስማዕከ ወርቁ) @yismakeworku


"ምናለ ጎበዝ ተማሪ ባልነበርኩ” እላለሁ

“ከሰው አልጨመርም። አብዝቼ እተክዛለሁ። ፊደል ያልቆጠረ ብዙ የማውቀው ሰው ቤት ንብረት አለው። የተሻለ ሕይወት ይመራል። እኔ ለምን ተማርኩ እላለሁ - አንዳንዴ። እንደሱ አይባልም - አውቃለሁ። ግን ምን ላድርግ? ወደ አእምሮዬ የሚመጣውን ነው የምነግርህ።

ውስጤ ጠንካራ ሆኖ ነው ከራሴ ያለሁት እንጂ ጭንቅላቴ እኮ ልክ አይደለም።

እንደ ባይተዋር ነው የምኖረው።

አንዳንዴ ለብቻዬ እያወራሁ ራሴን አገኘዋለሁ።

ጓደኛ የለኝ፣ ምን የለኝ። ሰው ሆነህ ከሰው ጋ መጨመር ካልቻልክ ማበድ ማለት አይደለም?

ከወር-ወር ኪሴ ባዶ ነው።ከቤት የማልወጣውም ለዚያ ነው። ታክሲ ውስጥ ሰው ባገኝስ ብዬ እሳቀቃለሁ። ከዚህ ሁሉ ለምን ቤት አልቀመጥም ብዬ ነው ያለሁ።

በቀደም ትዝ ሲለኝ ለባለቤቴ የተጋባን ቀን ከገዛሁላት ስጦታ ውጭ ገዝቼላት አላውቅም።

ባትነግረኝም ሞራሏ መጎዳቱ አይቀርም። ለልጄም እንደዚያው። ከዚህ በላይ ምን የሚያሳዝን ነገር አለ?

እኔ መምህር በመሆኔ እና እነሱ የመምህር ቤተሰብ በመሆናቸወ ተጎድተዋል። ምንም ጥያቄ የለውም። አንዳንዴ ‘ምናለ ድሮ ጎበዝ ተማሪ ባልነበርኩ’ የምለውም ለዚያ ነው።

#BBC እንደዘገበው 😭


"... ብዙውን ጊዜ በሕይዎት ውጣውረድ በምናሳልፋቸው ውሳኔዎች ፣ በሚፈጠሩት ክስተቶች መውደቅ መነሳቱ፤ መደቆሱ ያለና የሚኖር ነው፡፡ በተፈጠሩት የህይዎት ፈታኝ ክስቶቶች ዋጋ ያጣን ያህል ሊሰማን ይችላል፡፡ ነገር ግን ምንም ይሁን ምን፣ ያለፍንበት የሕይዎት ጎዳና ምንም ያህል አባጣ ጎርባጣም ቢሆን እኛ ማለት እኛ ነንና የእኛነታችንን፣ የራሳችንን ዋጋ አናጣምም ማጣትም የለብንም ፡፡ "

@yismakeworku


'የመጀመሪያውን እንግሊዘኛ ቋንቋን በቴሌግራም የማስተማር ስራዬ ተጀመረ' ይለኛል ወዳጄ።

ያሳቀኝም "መፎረፍ አይችሉም፣ ለወዳጆችህም አሳውቅልኝ" ብሎ ሀሳቡን ሲዘጋ ነው ሃሃሃሃ።

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርቱን በ @EthioEnglizegna በኩል በቴሌግራም በነፃ መከታተል እንደምትችሉ ጋብዟል።

"ሊንክ" ፡ https://t.me/+hRhOmsnuXG0zYTA0

ለመልካም ስራ እውቅና መስጠቴ ይቀጥላል!


እንክርዳድ

አባቴማ ድሮ
ስንዴ እያበጠረ
አንዳንዱን እንክርዳድ
ይለቅም ነበረ።

እኔ ግን ዘንድሮ
ግርድ አነፍሳለሁ
ከእንክርዳዱ መሀል
ስንዴ 'ፈልጋለሁ።

(ይስማዕከ ወርቁ)


🌟 ብቸኝነት ሲሰማህ ማሰብ ከቻልክ የአሳብህ ጓደኛ ነህ። ማሰብ ካልቻልክ ብቻህን ነህ። መነጠል የስጋ ሳይሆን የአሳብ ስሜት ነው።

🌟 ብቸኝነትህን አሳብህ ሲጋራ የአሳብ ጓደኛ አለህ። ብቸኝነትም ጓደኝነትም ስጋ አይደለም። የአብሮነትና የመነጠል ስሜት ነው። ከሰው ጋር ስትሆን ለብቻህ እንደሆንክ ከተሰማህ በግርግር መሀል ብቸኛ ነህ። በስጋህ ብቻህን ሆነህ ከአሳብህ ጋር አብረህ ከሆንክ አንተማ ጓደኛ አለህ።

🌟 ከቻልክ የወዳጅ አስፈላጊነትን ቀንስ። ሰው ብታጣም ያጣኸው ስጋ ነው። አብሮህ የሆነ አላቂ ነው። ዛሬ የሚቀርብህ ነገ የሚርቅ ነው። ወሳኙ ጉዳይ ህሊናህን አለማጣትህ ነው። የሌላ ስጋ ሲለይ አሳብህ ካንተ ጋር ነው።

🌟 መለየት የስጋ ነው። ብቻህን እንዳልሆንክ ከተሰማህ የአንተ ጓደኛ ስሜትህ ነው።

በድጋሚ!
@yismakeworku


"... ብራሶል አስቀድሞ በእርዳታ ድርጅቶች እጅ ኢትዮጵያን ሲሰልል ነበር። ስለላ ማለት ለግል ጥቅሙ እንጂ ፣ ለሀገሩ ሩሲያ ጥቅም አይደለም። ብራሶል የሚያቀርበው የጠብመንጃ ሽያጭ ሲሆን ፣ እስካሁን በዞረበት ሀገር ሁሉ ለግሉ የሚሰልለው ማዕድናትን ነው። አንድ ሀገር የእርሱ ዓይን ያርፍባት ዘንድ ብዙ ማዕድናት እንዳላት ማወቅ አለበት። የብራሶል አመለካከት እንዲህ ነው። ዓለም ውስጥ ያሉ መንግሥታት በሙሉ ማሳያዎች ናቸው። በህዝብ የተመረጡ ወይም በህዝብ ሳይመረጡ የወጡ ህጋዊ ማፍያዎች። እኛ ከዚህ የምንለየው ህጋዊ አለመሆናችን ብቻ ነው። ፖለቲካ በሚሉት የውሸት አብዮት ፣ ህዝቡን ስለማናታልል ነው።" ይላል ሁልጊዜም።

                ~ከመጽሀፉ የተወሰደ

🌟 ዛምራ የተሰኘው መፀሀፌን ምን ያክሎቻችሁ አንብባችሁታል?

@yismakeworku


እንደ ክረምት ዝናብ፣ ችግሬ ይረግፋል

ምስኪን ትከሻዬ፣ እሱን ይቀበላል

ሰዎቹም ይላሉ፣ እንዴት ቻለው እሱ

ሁሌም ብልጭ ይላል፣ አይከደን ጥርሱ

የተበደለ ሰው፣ ችግር ላላት ነፍሱ

ኑሮ እንዴት ነው ቢሉት፣ ፈገግታ ነው መልሱ

@yismakeworku


#Ad
ከትምህርት ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕዉቅና የተሰጠው...
ቶፕ ኮምፒውተርና ቋንቋ ማሰልጠኛ ተቋም!

በሶስቱም ቅርንጫፎቻችን (መገናኛ፣ ሜክሲኮና ጀሞ) እንዲሁም በኦንላይን በፈለጉት አማራጭ በአጭር ጊዜ ስልጠና ከትምህርት ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕዉቅና ካለዉ ሰርተፊኬት ጋር የሙያ ባለቤት ይሁኑ!

የብዙ አመት ልምድ ባላቸዉ አሰልጣኞች!
* Graphics Design (basic + Advanced)
* Video Editing (basic + Advanced)
* Digital Marketing (basic + Advanced)
* Adobe photoshop (basic + Advanced)
* English language (basic + Advanced)
* Website Design (basic + Advanced)
* Programming Language (basic + Advanced)
* Interior Design
* Database
* Basic Computer
* Accounting Softwares (Peachtree/ Queeck books)
* Engineering Softwares (Autocad,Etabs, Civil 3d,Reviet, solid
work, bill of quantity, software engineering courses)
* SPSS & STATA
* MS-Project
* Foreign (English, Arebic, German, Chinese, French, Italy,
swedish, Norway, Spanish, Turkish..) & Local (Amharic,
Oromiffa, Tigrigna, Geez..) Languages

አድራሻ:-
1. መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 419 (ሊፍት ይጠቀሙ)
☎️ 0991929303

2. ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 639 (ሊፍት ይጠቀሙ ሁለተኛዉን ሊፍት)
☎️ 0991929304

3. ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ
☎️ 0991926707

ማሳሰቢያ፦ወደተቋማችን መጥተው ማለትም ከኦንላይን ስልጠና ውጭ የኮምፒውተር ነክ ስልጠናዎችን ለመሰልጠን ኮምፕዩተር መግዛት አይጠበቅብዎትም!

Telegram:- https://t.me/topinstitutes

Facebook:- https://www.facebook.com/Topinstitutes

TikTok:- https://Tiktok.com/@topinstitute


ወዳጄ፥ የልብ ጓደኛዬ።

እንዲህ አለኝ... "ይስምሽ አንድ ነገር አስቢያለሁ! በቴሌግራም ቁምነገር ለመስራት አስቢያለሁ" ግራ ስለገባኝ የግንባሬን ውጥር ቆዳ በማኮማተር እንዳልገባኝ ላሳየው ሞከርኩ። ስለገባው ማብራራቱ ቀጠለ... "ምን መሰለህ! በቴሌግራም የምችላትን የእንግሊዘኛ ቋንቋ በማካፈል ለወዳጆች ለማስተማር ነው! ሆኖም ግን ከአንተ እርዳታ እሻለሁ ማለትም ቻናሉን በቻናልህ አስተዋውቅልኝ" አለኝ።

ለጥሩ ነገር ስለሆነ እና ለወዳጆቼም ልጋብዝ ስለምሻ ምን ገዶኝ በማለት ጭንቅላቴ ከታች ወደላይ ነቀነቅኩለት። ፈገግ አለ።

ስለዚህ ጓደኞቼ የእንግሊዘኛን ቋንቋ እጅግ በቀላሉ ለማወቅና ለመማር ከፈለጉ ይሄን ቻናል መቀላቀል ይችላሉ::
@Ethioenglizegna ይላል ማስፈንጠሪያው።
h
ttps://t.me/+hRhOmsnuXG0zYTA0


ከመጸለይህ በፊት ተመስገን በል። ስለሁሉም ነገር አመስግን...በረከቶችህን ቁጠር! ጠዋት ገና ከእንቅልፍህ ስትነቃ....አይኖችህን ስትገልጥ በል!!!...ሞተህ ልታድር ትችል ነበርና!!! ደግሞ ከአልጋህ ወርደህ መሬት ስትቆም……‹‹ተመስገን>> በል! በሆነ ምክንያት የአልጋ ቁራኛ ሆነህ ልትቀር ትችል ነበርና!!! በየትኛውም መንገድህ ላይ አመስግን። ምስጋና ቢስ አንደበቶች ልመናን ሲያሻግሩ ለዛቸውን ያጣሉ!

እጅግ የምወደው የሙያ አባቴ ደራሲ ስብአት ገብረ እግዚአብሔር

መልካም በዓል


መልካም የደመራ በዓል!

@yismakeworku

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.