✋🖐ሰላም የዘርዓያዕቆብ ዘኢትዮጵያ ቤተሰቦች ዛሬ የፊደላትን ትርጉም በግእዝና በአማርኛ እናያለን።
➡️ሀ=ሀልዎቱ ለአብ እምቅድመ ዓለም ፤ የአብ አኗኗሩ ከዓለም በፊት ነው።
➡️ለ=ለብሰ ሥጋ እምድንግል ፤ ክርስቶስ ከድንግል ሥጋን ለበሰ
➡️ሐ=ሐመ ወሞተ ፤ ታመመና ሞተ
➡️መ=መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር ፤ የእግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነው።
➡️ሠ=ሠረቀ በሥጋ ፤ በሥጋ ተገለጠ
➡️ረ=ረግዓት ምድር በቃሉ ፤ ምድር በቃሉ ረጋች
➡️ሰ=ሰብዓ ኮነ እግዚእነ ፤ ጌታችን ሰው ሆነ
➡️ቀ=ቀዳሚሁ ቃል ፤ ቃል መጀመሪያ ነበር
➡️በ=በትሕትናሁ ወረደ ፤ በትሕትናው ወደ ምድር ወረደ
➡️ተ=ተሰብአ ወተሰገወ ፤ ጌታችን ሰው ሆነ
➡️ኀ=ኀያል እግዚአብሔር ፤ እግዚአብሔር ኀያል ነው
➡️ነ=ነስአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ ፤ ጌታችን ደዌያችንን ወሰደ
➡️አ=አአኵቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር ፤ ጌታን ፈጽሜ አመሰግነዋለሁ
➡️ከ=ከሃሊ እግዚአብሔር ፤ ጌታችን ቻይ ነው
➡️ወ=ወረደ እምሰማይ ፤ ጌታ ከሰማይ ወረደ
➡️ዐ=ዐርገ ሰማያተ ፤ ወደሰማይ ዐረገ
➡️ዘ=ዘኵሉ ይእኅዝ እግዚአብሔር ፤ ጌታ ሁሉን የሚይዝ
➡️የ=የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኃይለ ፤ የጌታ ቀኝ እጅ ኃይልን አደረገች
➡️ደ=ደመረ ሥጋነ ምስለ መለኮቱ ፤ ጌታ ሥጋችንን ከመለኮቱ ጋር አንድ አደረገ
➡️ገ=ገብረ ሰማያተ በጥበቡ ፤ ጌታ በጥበቡ ሰማያትን ሠራ
➡️ጠ=ጠዐሙ ወታእምሩ ከመኄር እግዚአብሔር ፤ ጌታ ቸር እንደሆነ ቅመሱና እወቁ
➡️ጰ=ጰራቅሊጦስ መንፈሰ ጽድቅ ፤ ጰራቅሊጦስ እውነተኛ መንፈስ ቅዱስ ነው
➡️ጸ=ጸጋ ወክብር ተወህበ ለነ ፤ ጸጋና ክብር ተሰጠን
➡️ፈ=ፈጠረ ሰማየ ወምድረ ፤ ጌታ ሰማይንና ምድርን ፈጠረ
➡️ፐ=ፓፓኤል ስሙ ለአምላክ ፤ ፓፓኤል ማለት የአምላክ ስም ነው።
👉የግእዝ መሠረተ አጻጻፉ የሚጀምረው በ"አ" ሆኖ የሚጨርሰው ደግሞ በ"ፐ" ነው። ነገር ግን ከ4ኛው ክፍለዘመን ጀምሮ የምንጠቀምበት ፊደል ቅደም ተከተል ግን የሚጀምረው በ"ሀ" ነው። በተጨማሪም "ሸ" ፣ "ቸ" ፣ "ኘ" ፣ "ዠ" ፣ "ጨ" ከግእዝ ፊደላት ውስጥ አይካተቱም።
በመጨረሻም ብራና ፈቅፍቀው ቀለም በጥብጠው የማንነታችን መታወቂያ የሆኑትን ፊደላት ጽፈው ላስቀመጡልን አባቶቻችን ክብር ምስጋና ይሁን🙏🙏🙏
🕊አሻም ለሀገራችን
🕊አሻም ለኢትዮጵያችን
🕊አሻም ለሕዝባችን
@zera_yeakob @zera_yeakob @zera_yeakob