ዕለትን በታሪክ 🎙
አሁን ሞት ወደኛ ቀርቧል
አቤቱ ጌታዬ ሆይ የዛሬን ብቻ ታደገኝ!!
ጓደኛየ ዛሬ በቃ የመጨረሻ የበረራ ቀናችን ነው!!!
ይቺ ፕሌን በሰላም የምትደርስ አይመስለኝም፣ እንደ ወጣን መቅረታችንን አምኛለሁ።
ስማኝ ጓደኛየ ሞታችን የሚቀር አይመስለኝም ቢሆንም ግን እስኪ ወደኋላ እንቀመጥ ከዛች አውሮፕላን ውስጥ የሚሰማ ድምጽ ነበር።
ጀርመን በበረዶ ተውጣለች፦ ገናም መጀመሩ ነው። የአውሮፕላኗ ካፒቴን በረራው እንዲሰረዝ ጠየቀ። ነገርግን የዩናይትድ ባለስላጣናትና አሰልጣኞች ለቀጣዩ ጨዋታ ዝግጅት ኢንግላንድ መድረስን መረጡ።
ካፒቴኑም ሳይዋጥለትም ቢሆን ፕሌኗን ደጋግሞ ሞከራት፥ ሁለቴ አልተሳካም። በሶስተኛው ተሳካ አውሮፕላኗ መስራት እንደምትችል ታመነ።
ተጨዋቾችም ወደ ፕሌኗ ግቡ ተባሉ። ያኔ የቡድኑ ተጨዋች ሊያም ዊሊያም ለጓደኞቹ እንዲህ አለ። አሁን ሞት ወደኛ ቀርቧል። በኔ በኩል ዝግጁ ነኝ ሲል ተደመጠ።
ተጨዋች በሙሉ ገቡ። ፕሌኗ አኮበኮበች፥ አፍንጫዋን ወደሰማይ አንጋጣ፣ ደመናማውንና በረዷማውን የሙኒክ ሰማይ ልትቀዝፍ ቀና አለች። ነገር ግን ከተነሳች ሶስት ደቂቃኳ በቅጡ ሳይሞላ፣ እንደ ተራራ ከሚረዝመው የበረዶ ክምር ከ 3000 ጫማ ላይ ተወርውራ ተጋጨች።
በሶም አልቆመችም በረዶው አልያዛትም ጠልቃ ገብታ ከቦረዶው መሀል ካለ ተራራ ጋር ተላተመች።
ያኔም በከፍተኛ ተነሳሽነት የእንግሊዝን እግርኳስ አብዮት እየተቆጣጠሩ የነበሩት የዩናይትድ ወጣት ተጨዋቾች፣ (ቤዝቢ ቤቢስ) ከእድለኞቹ ከነ ሰር ቦቢ ቻርልተን ውጪ ሩገር ባይነር፣ ማርክ ጆንስ፣ ኢዲ ኮልማን፣ ጂፍ ቤንት፣ ዴቪድ ፔጅና፣ ሊያምን የመሳሰሉ የወቅቱ በዝቢ ቤቢስ የዩናይትድ ታዳጊወች ላይመለሱ ከበረዶ ተዋሀዱ።
በግዜው ዱካን ኤድዋርድስ፣ ነፍሱ ሳትወጣ ብትገኝም፣ ሀኪም ቤት ገብቶ፣ ዩናይትድ የሻንፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ሲበላ ሳላይ ልሞት ነው እያለ፣ ያረፉትን ጓደኞቹ ተቀላቀለ።
መረጃውን ቀድሞ የዘገበው BBC ማንችስተር ሆይ እርምሽን አውጪ፣ ቢልግሬድን በጥሎ ማለፉ አሸንፎ፣ በ G_aluz601 አውሮፕላን፣ ከቢልግሬድ አውሮፕላን ማረፊያ የተነሳውና፣ ሙኒክ አርፎ ጉዞ የጀመረው፣ ማንችስተር ዩናይትድ ከነ አውሮፕላኗ ከጀርመን ሰማይ ስር ቀርቷል ሲል አወጀ።
ሻንፒዮንስሊግን ለመጀመሪ ግዜ አንስተው እንግሊዝና ደጋፊዎቻቸውን ሊያኮሩ ያለሙት። የመጀመሪያው የእንግሊዝ ክለብ መሆንን ያቀዱት የዩናይትድ ህያው ጀግኖች ከ 3000 ጫማ በላይ ከተንሳፈፈች አውሮፕላን ተከስክሰው አረፉ።
መላው አለም አዘነ። ዩናይትዳውያን ጥቁር ድንኳን ዘረጉ። የእግርኳስ ተጨዋቾች አነቡ። የምንግዜም ባላንጣው ሊቨርፑል። ከጉናቹህ ነኝ አለ። ኤሲ ሚላን ባርሴሎና ማድሪድ ሙኒክና ሌሎችም ክለቦች ለዩናይትድ ተጨዋቾችን በመስጠን ለማገዝ ቃል ገቡ።
አንዳንዶችም ዩናይትድ አበቃለት ዳግም ላይነሳ ከተጨዋቾች ጋር ሞተ ሲሉ ጻፉ። ነገር ግን ዩናይትድ ዩናይትድ ነው። ወድቆ መነሳትን ተበትኖ መሰብሰብን። እንደገና አሸናፊነት ለአለም አስተማረ።
ዩናይትድ ከካሪንግተን ተጨዋቾችን መለመለ። ሌሎችንም አመጣ። የዛን አመት ሻንፒዮን ባይሆንም። አሸናፊ ቡድንን መሰረተ። ነገርግን ባጭሩ ያሰቡት የያኔው ዩሮፒያን ካፕ (ሻንፒዮንስ ሊግ) ዋንጫ ወደ ዩናይትድ የዋንጫ መደርደሪያ ለመምጣት 10 አመታትን ፈጀ።
በ 1968 ዩናይትድ ያኔ የተሰዋለትን ዋንጫ አሸነፈ የመጀመሪያው የእንግሊዝ ክለብ ሆነ። ካደጋው የተረፉት ሰር ቦቢ ቻርልተንና ጓደኞቹ። ዋንጫውን ያኔ አፈር ለለበሱት ጓደኞቻቸው መታሰቢያ አደረጉ። ያው ዩናይትድ ዛሬም ነገም ነግሶ ሊኖር በልጆቹ ደም አወጀ። ነገርግን የካቲት 6 1958 ለዩናይትድና ደጋፊዎቹ ጥቁር ቀን ሆነ።🕶🌑
@Zetena_Dekika_Sport @Zetena_Dekika_Sport