🙏ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬ🙏


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


ገና እንዘምራለን እንደ መላእክቱ
ብርሃንን ለብሰን ገና እንዘምራለን
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርሰቲያን አሰተምሮ ና ሰርአት የጠበቁ
✥👉መንፈሳዊ ትምህርቶች
✥👉መንፈሳዊ መዝሙሮች
✥👉መንፈሳዊ ንግሰ እናሳዉቃለን
✥👉መንፈሳዊ ምክር ነክ ፁሁፍ
✥👉መንፈሳዊ ታሪኮች
📢ለማስታወቂ ሥራ @Mane_tekel

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri




MUUDAMEERA MIKAA'EEL

Muudameera Mikaa'eli
Kan nuun loluu kufeera saaxnaa'eeli (2)
Kan nu gargaaru muudameera Mikaa'eli(2)

Karaa keenyaa isat geggeessaa
Harkaa diinatti yoom nuun nu dhiisa
Mikaa'el jechuun isa waammanna
Araarsummaasaas nut nii amanna


Maqaan Waaqayyoo kan irra jiru
Yeroo rakkinaa kan nama furuu
Kabajni isaa akka aduu ifaa
Fayyina fidee garkeenya dhufaa

Fuuldura bala'aam inni dhaabbateera
Abaarsi darbee Eebba ta’eera
Saba Waaqayyoof inni ni dhaabbataa
Qulqulluu Mikaa'el hangafa Ergamoota


Daandii jireenyaa nutti agarsiisa
Galaanaa du’aa hiree nu ceesisaa
Mootummaa Waaqayyoof inni nu qopheessa
Mikaa'el jechuun ni waamna maqaasaa

Sher tasisaa




✞ቅድስት ሐና✞

መርአተ ኢያቄም ፀጋዊተ ህይወት
ቅድስት ሐና  ብርሃን ለፍጥረት
አዝ
ሐና ኅሪት ወለተ ብሩካን
የወለደች ለኛ ቅድስት ቅዱሳን
አሰራሯ ያማረ የምስክር ድንኳን/2/
ተፈፀመ ሐና በወለትኪ
ተስፋ ቅዱሳን አበውኪ /2/
አዝ==========
ሐና ቡርክት ወለተ ቡሩካን
ለፍጥረት ያስገኘች የሚያበራ ተስፋን
በሐዘን ለነበርን ማይቋረጥ ደስታን /2/
ተፈፀመ ሐና በወለትኪ
ተስፋ ቅዱሳን አበውኪ /2/
አዝ==========
ሐና  ቅድስት ንግስተ ሃይማኖት
ተስፋ የወለደች በስለት በጸሎት
ለደከመው ዓለም በመድኃኒት እጦት /2/
ተፈፀመ ሐና በወለትኪ
ተስፋ ቅዱሳን አበውኪ /2/
አዝ==========
ብፅዕተ ብፁዓን እናታችን ሀና
እመ ማርያም ይድረስሽ ምስጋና
አወድስሻለሁ በፍጹም ትህትና/2/
ተፈፀመ ሐና በወለትኪ
ተስፋ ቅዱሳን አበውኪ /2/

ዘማሪ ዲ/ን ማኑሄ ዳዊት


✞ከሊባኖስ✞

ሐና እና ኢያቄም ወለዱ ሰማይ
አዲሷም ሰማይ አስገኘች ፀሐይ
ምስራቀ ምስራቃት የአምላክ መገኛ
#ከሊባኖስ ድንግል ነይ ወደኛ(፪)

ተጨነቀ አዳም በመከራ
በእርግማን ቀን ለቅሶ እየዘራ
በልጅሽ ሞት ዓለም ተቀደሰ
የፍጥረቱ ዕንባ በመስቀል ታበሰ(፪)
አዝ= = = = =
የሕያዋን እናታቸው ሆነሽ
ለቀደመች ሔዋን ጠበቃ ሆንሽ
ደስተኛዋ ደስ ይበልሽ ማርያም
ከአንቺ ወጣ የዓለሙ ሰላም(፪)
አዝ = = = ==
ጽኑ ገመድ በአንቺ ተቆረጠ
የፍዳ ዓመት ይኸው ተለወጠ
በሐና ልጅ በኢያቄም ፍሬ

በወለዱሽ በሐና በኢያቄደስታ ሆነ ቅኔ እና ዝማሬ(፪)
አዝ= = = = =
ተማጽነናል ድንግል ማርያም
ከአዳኝ ወጥመድ ከክፉ ጠላት
ልጆችሽን ጠብቂን ከጥፋት
ከአዳኝ ወጥመድ ከክፉ ጠላት
ኢትዮጵያን ጠብቂያት ከጥፋት


ዘማሪ ዲያቆን አቤል


✞ የጽዮን ደጆች ✞

የጽዮን ደጆች ቅኔ ተሞሉ
ለድንግል ክብር እልል እያሉ
አንደነጭ እንቁ የሚያበራ
አልፈናል ስሟን ስንጠራ/2/

ሀይልን ለሚያደደርገው ለተወዳጅ ስምሽ
የዜማ እቃችንን አነሳን ልጆችሽ
መሀተበ ቡራኬሽ በልባችን አለ
አፋችን ማሪያም ሲል ጭንቃችን ቀለለ
           
         አዝ=====

የምስጋና ጥበብ የቅኔ ሀብት ጸጋ
ከደጃፍሽ መጥተን ገዛን ያለዋጋ
ጥልቁን ለቀነዋል በትከሻሽ ሆነን
ጽዮንን በእልልታ በዜማ ሸፍነን
          
        አዝ=====

ጠቢባን ምክራቸው ታየ ተሰውሮ
ሚስጢር ተገለጠ በህጻናት አእምሮ
ቤተልሔም ሰማች የብስራቱን ዜማ
ፍቅር ተለቀመ ከእግዚአብሔር ከተማ
            
         አዝ=====

ከአሸናፊው ልጅሽ ከክርስቶስ ጋራ
አንደዘበት ወጣን የሞትን ተራራ
ፍሬሽን ቀመሰነው ልቦናችን ረጋ
ሰላም ነው ከእንግዲህ አንኖረም ስንሰጋ

https://t.me/zmaredawt_zeortodocs


ወደ ቀድሞ ነገር

ወደ ቀድሞ ነገር እንመለስ
የአምላክን እናት እናወድስ
ከፍቅሯ ርቃችሁ የምትኖሩ /2/
ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ /2/

ቃል ተጽፎባታል የመዳኛ ፊደል ጥበብየሚሞላ ጨለማን የሚሰቅል
ለቃል ስጋ መሆን ምክንያት ስለሆነች
ቀርባችሁ ተማሩ ማርያም ፊደል ነች


አዲሱ ቃልኪዳን ከላይ የተጻፈው
በገሊላ ናዝሬት ገብርኤል ያበሰረው
በማርያም እቅፍ ላይ ታገኙታላቹ
የሚስጢር መዝገቡን አንብቡ ገልጣቹ

ያዘለችው ወንጌል ቃሉ ያፈውሳል
አምኖ ላነበበው ነፍስ ያለመልማል
በጀርባዋ ያለው እግዚአብሔር ነውና
አቅርቡ ለማርያም ውዳሴ ምስጋና


ቡዙዎች ተማሩ ስሟን እየጠሩ
በአባታቸው መንግስት እንደ ጸሀይ በሩ
ክብረ ልዕልናዋን ገብርኤል ነግሮናል
ካወደሷት ጋራ ለክብሯ ቆመናል


🌹 “ማርያም ማርያም“ 🌹

ማርያም ማርያም ልበል
እረፍቴ ሆይ በስምሽ ልጠለል
የቃል እናት ያድናል ቃልሽ
ታምር ይሰራል ስምሽ


አዝ==========

ማር ልበል በምድር ያም ልበል በሰማይ
የማይጠግቡት መና የማይጨርሱት ሲሳይ
መንፈስ ቅዱስ ቃኝቶ ሰርቶ በሚስጥሩ
አፌ ላይ ጣፈጠኝ ስምሽ አጠራሩ (2)

አዝ==========

መዳኒት ታቅፈሽ የአለሙን ጌታ
ከቤተልሄም ደጅ እስከ ጎለጎታ
የዓለሙን ህምም የዓለሙን በሽታ
ታክሚው ነበረ ድንግል በዝምታ (2)

አዝ==========

በምን እንመስልሽ የለሽም ምሳሌ
አንጠግብም ብንጠራሽ ብንዘምርልሽ ሁሌ
ምስክር አያሻም ያንቺ ልእልና
የአለሙን ንጉሥ ወልደሺዋልና (2)

አዝ==========

የወርቅ ማእጠንት እሳት የታቀፍሽ
የአዲስ ኪዳን ኪሩብ ማርያም አንቺ ነሽ
የአርያም እጣን ነሽ መአዛሽ ያማረ
ዘላለም አይወድቅም አንቺን ያከበረ (2)

🕊🌺🕊🌺🕊🌺🕊🌺🕊🌺🕊🌺
https://t.me/zmaredawt_zeortodocs


✞ ዮም ፍስሐ ኮነ ✞

ዮም /ፍስሐ ኮነ/(፪)
በእንተ ልደታ ለማርያም

በባርነት ሳለን - - - ፍስሐ ኮነ
ኃጢአት በአለም ነግሳ - - - ፍስሐ ኮነ
በድንግል መወለድ - - - ፍስሐ ኮነ
ቀረልን አበሳ - - - ፍስሐ ኮነ
እግዚአብሔር መረጠሸ - - - ፍስሐ ኮነ
ልትሆኚው እናቱ - - - ፍስሐ ኮነ
ይኸው ተፈፀመ - - - ፍስሐ ኮነ
የዳዊት ትንቢቱ - - - ፍስሐ ኮነ

አዝ = = = =

የሔዋን ተስፋዋ - - - ፍስሐ ኮነ
የአዳም ዘር ህይወት - - - ፍስሐ ኮነ
የኢያቄም የሐና - - - ፍስሐ ኮነ
ፍሬ በረከት - - - ፍስሐ ኮነ
ምክንያተ ድኂን - - - ፍስሐ ኮነ
ኪዳነምህረት - - - ፍስሐ ኮነ
ድንግል ተወለደች - - - ፍስሐ ኮነ
የጌታዬ እናት - - - ፍስሐ ኮነ

አዝ = = = =

በሔዋን ምክንያት - - - ፍስሐ ኮነ
ያጣነውን ሰላም - - - ፍስሐ ኮነ
ዛሬ አገኘነው - - - ፍስሐ ኮነ
በድንግል ማርያም - - - ፍስሐ ኮነ
የምስራች እንበል - - - ፍስሐ ኮነ
ሀዘናችን ይጥፋ - - - ፍስሐ ኮነ
ተወልዳለችና - - - ፍስሐ ኮነ
የአለም ሁሉ ተስፋ - - - ፍስሐ ኮነ

@zmaredawt_zeortodocs
@zmaredawt_zeortodocs
@zmaredawt_zeortodocs




𓆩 ፈራሁ 𓆪

ቀኑ ከረፈደ ከመሸብኝ መጣሁ
ደጃፍህ ላይ ቆምኩኝ እንዳልገባ ፈራሁ
በደሌን ሳትመዝን ግቢ ብትልኝም
ሀጥያቴ ከበደኝ አላራመደኝም /2/

የሰው እድሜ አጭር ነው ጥቂት ነው
እንዴት ነው ሳላውቅህ ዘመኔ ያለቀው
ጉብዝናዬን አለም ሲቃ ተጫወተብኝ
እንዴት ብዬ ልርገጥ ደጅህን በድፍርት

ፈራሁኝ ልግባ ወይ አልግባ
እንዴት ይመዝናል ያንተ ደም በኔ እንባ


እኔ ፈራሁ እንጂ አንተ እኮ አታስፈራም
መምጣቴ ነው ደስታህ ፍቅርህ አይታማም
ሽምቅቅ አለች ነፍሴ መስቀልህን ሳየው
በደሌን አሰብኩት ደምህን እያየሁ

ፈራሁኝ ልግባ ወይ አልግባ
እንዴት ይመዝናል ያንተ ደም በኔ እንባ


በንፅህና ፊት እንዴት እቆማለሁ
እንደ መላእክቱ በምን ጋርዳለሁ
እራሴን መሸፈኛ ክንፍ የለኝም እኔ
ይታያል ሀጥያቴ የበደል እርቃኔ

ፈራሁኝ ልግባ ወይ አልግባ
እንዴት ይመዝናል ያንተ ደም በኔ እንባ


ጠዋት እና ማታ ለመጣህ አንድ ነው
አምሽቶም ለገባ እኩል ትከፍላለህ
አብርሃም ወይ ይስሃቅ በድንኳንም ቢያድሩ
በአንተ መንግስት ግን ከወንበዴ አይቀድሙም

ፈራሁኝ ልግባ ወይ አልግባ
እንዴት ይመዝናል ያንተ ደም በኔ እንባ


መዝሙር
ዘማሪት በዛወርቅ አስፋው










✞ ማር ሊቀ ሰማዕት ✞

ማር ሊቀ ሰማዕት ገባሬ መንክር
        ጊዮርጊስ ኃያል፪

የዱድያኖስ አምላክ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ያንን ደራጎን - - ጊዮርጊስ ኃያል
አምላክ እንዳልሆነ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ገድለህ አሳየኸን - - ጊዮርጊስ ኃያል
የቤሩት ኮከብ ነህ - - ጊዮርጊስ ኃያል
የልዳ ፀሐይ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ለባሴ ሞገስ ነህ መክብበ ሰማዕት ፪
አዝ= = = = =
መከራና ስቃይ - - ጊዮርጊስ ኃያል
እያጸኑብህ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ትናገር ነበረ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ስለ አምላክህ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ሥጋህን ፈጭተው - - ጊዮርጊስ ኃያል
ይድራስ ሲበትኑት - - ጊዮርጊስ ኃያል
ዳግመኛ አስነሳህ አምላከ ምሕረት ፪
አዝ= = = = =
አንገትህ ሲታረድ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ምድር ተናወጠች - - ጊዮርጊስ ኃያል
ወተትና ውሃ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ደምም አፈለቀ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ሰብዐ ነገሥታት - - ጊዮርጊስ ኃያል
እስኪደነቁብህ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ሰባት አክሊላትን ጌታ አቀዳጀህ ፪
አዝ= = = = =
የዚህን ዓለም ጣዕም - - ጊዮርጊስ ኃያል
ንቀኸው ጥቅሙን - - ጊዮርጊስ ኃያል
በፍቅር ተቀበልክ - - ጊዮርጊስ ኃያል
መራራ ሞትን - - ጊዮርጊስ ኃያል
ሰማይና ምድር - - ጊዮርጊስ ኃያል
ሳርና ቅጠሉ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ሰማዕተ ክርስቶስ ቅዱስ ጊዮርጊስ አሉ ፪


✞ እንደ ትላንትናው ✞

እንደ ትላንትናው /2
ከአፌ ላይ አይጠፋም የስምሽ ምስጋና
እንደ ልጅነቴ/2
በፍቅር ያነሳሻል ዛሬም አንደበቴ
በቅዱሱ ስፍራ በአውደምህረት
ስጠራሽ አድጌ ኪዳነምህረት/2

አዝ--------------------

ገና ልጅ ሳለው ነበር ሳወድስሽ
አፌን የፈታሁት ዘምሬ ለክብርሽ
ብወድሽ ባነሳሽ መቼ ቀን ጠግቤ
ይኸው ለዚህ ደረስኩ አትሜሽ በልቤ
የአፌ ዜማ ነሽ ጥበብ ለከንፈሬ
ኪዳነምህረት ነው አሁንም መዝሙሬ

አዝ------------------

የእናትን ውለታ ያውቃል የቀመሰ
በእቅፏ ያደገ ለክብር የደረሰ
እኔም አውቀዋለሁ ያንቺን ደግነት
ከቃላት በላይ ነው ያጥራል አንደበት
የተደረገልኝ አለ ብዙ ነገር
ለዚህ ነው እናቴ ማነሳሽ በፍቅር

አዝ--------------------

አይኖቼ በናፍቆት በስስት ያዩሻል
ልሳኔ በፍቅር ደጋግሞ ያነሳሻል
ከመቅደስሽ ቆሜ የውስጤን ነገርኩሽ
ህልሜን ስትፈቺ እናቴ አየሁሽ
እውነትም አዛኝ ነሽ ለተማፀነሽ
ግራ ለገባው ሰው ቅርብ ነው ምልጃሽ


ዘማሪ
ሙሉቀን ከበደ


✞ ስምሽን ስጠራዉ ✞

ስምሽን ስጠራው ድንግል
ስምሽን ስጠራው ማርያም
ላንደበቴ ማር ነው ለልቤ ሰላም
ስምሽን ስጠራው ማርያም/2/


ትውልድ ነኝና ልጅሽ የፈጠረኝ
ድንግል እመቤቴ ላንቺ ምስጋና አለኝ
በፈቃደ እግዚአብሔር ባባቶቼ ፀጋ
ሰዓሊ ለነ እላለው ሲመሽም ሲነጋ

በጠየቅሽው ጊዜ ወይኑን እንዲመላ
አክብሮሻልና በቃና ገሊላ
የሰላም እናት ሆይ ሰላም ልበልሽ
ዘመኔ ይፈፀም ሳመሰግንሽ



በሰላምታ ድምፅሽ መንፈስ ተመልቼ
አደግድጌ ልቁም እጆቼን ዘርግቼ
በአብይ ቃል ጮሄ ልመስክር በብርቱ
ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር እናቱ

ከሰማይ ሲገኝ ነው አንችን ማወደስ
ሲገለጥ ሲፈቀድ ከመንፈስ ቅዱስ
ማርያም ህይወቴ ነሽ ምክንያት ለመዳኔ
ብዙ ነው ምስጢሩ አንችን ማመስገኔ


ስምሽን ስጠራው ድንግል
ስምሽን ስጠራው ማርያም
ላንደበቴ ማር ነው ለልቤ ሰላም
ስምሽን ስጠራው ማርያም

እስትንፋ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )


✞ ገብርኤልን ላከው ✞


የመላእክት አለቃ ገብርኤልን ላከው ኃያሉ እግዚአብሔር በሰማያት ያለው የባሕርይ ልጄ ወደ አንቺ ይመጣል ብለህ ለጽዮን ልጅ ንገራት ለድንግል

ኀይለ ልዑል ወልድም ሥጋሽን ይለብሳል በተለየ አካሉ ወደ አንቺ ይመጣል ከሥጋሽሞ ሥጋ ከነፍስሽም ነፍስ ነሥቶ ይዋሐዳል በግዕዘ ሕፃናት ከአንቺ ይወለዳል

ደንቆሮ ሊሰማ ድዶች ሊናገሩ በጌታ ተአምራት ዕውራን ሊበሩ መታን ይነሡ ዘንድ በማሕፀንሽ ፍሬ ከእግዚአብሔር ወደ አንቺ ተልኬአለሁ ዛሬ

ደስ አሰኛት አለው በልዩ ሰላሞታ ሐሴት እንድታደርግ ምሥራቹን ሰሞታ ዲዳ እንዳደረግከው ካህን ዘካርያስን እንዳታሳዝናት ከእርሷ ጋር ስትደርስ

ገብርኤል በደስታ ምሥራቹን ይዞ ከሰማይ ወረደ በአምላኩ ታዝዞ በሊባኖስ መንደር እስኪሰማ ድረስ ክንፋን እያማታ መጣ ሲገሰግስ

ደስ ይበልሽ አላት እየተሳለማት ሐርን ከወርቅ ጋር ስትፈትል አግኝ±ት እውነተኛው ንጉሥ ከአንቺ ይወስዳል ስአንቺ ፍቅርና አንድነት ይገባል

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
የአእላፋት ዝማሬ


✞ምስጢረኛዬ ነሽ✞

አውቀዋለሁ ደጅሽን የእረፍት ቦታዬን
ጽኑ ስላም ጸጥታ ማግኛዬን
የት እሄዳለሁ አልልም ሲከፋኝ
ኪዳነምሕረት አንቺ እያለሽልኝ/2/
አዝ••••••••••
ከአጸደ መቅደስሽ ከስዕልሽ ስር
እረፍቴ በዚያ ነው በቅዱሱ ደብር
ከተራራው አናት ከደጅሽ መጥቼ
ሰምሮልኛል ስምሽን ጠርቼ
ምሥጢረኛዬ ነሽ ምሥጢረኛዬ
ኪዳነምሕረት መጽናኛዬ/2/
አዝ••••••••••
የሮማን አበባ መዓዛሽ ተወዳጅ
በረከትን ልቅሰም ሳልለይ ካንቺ ደጅ
አስራትሽ አድርጊኝ ጠቅልይኝ እናቴ
ታብብልኝ ትፍካልኝ ሕይወቴ
ምሥጢረኛዬ ነሽ ምሥጢረኛዬ
ኪዳነምሕረት መጽናኛዬ/2/
አዝ••••••••••
አጠገቤ ጎኔ በዙሪያዬ እንዳለሽ
እንደርሱ ነው ልቤ እማ የሚያወራሽ
አልቅሼ ሲቀለኝ ነግሬሽ የውስጤን
አትዘገይም ስትሠሪልኝ ቤቴን
ምሥጢረኛዬ ነሽ ምሥጢረኛዬ
ኪዳነምሕረት መጽናኛዬ/2/
አዝ••••••••••
የእንጦጦዋ እናቴ እምዬ የምልሽ
ኪዳንኪ ደጓ የልብን ሰሚ ነሽ
በሄድኩበት አለሽ ተከትለሽኛል
ስላለሽኝ ሰላም ይሰማኛል
ምሥጢረኛዬ ነሽ ምሥጢረኛዬ
ኪዳነምሕረት መጽናኛዬ/2/

ዘማሪ ዲያቆን
አቤል መክብብ

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.