9 Mar, 19:07
💗 እንኳን ለወርኀ የካቲት መጨረሻ ፡ ለዘመነ ዮሐንስም መጋመሻ ዕለት በሰላምና በምሕረት አደረሳችሁ። ወርኀ የካቲትን በቸር ያስፈጸመ አምላከ ቅዱሳን ወርኀ መጋቢትን እንዲባርክልን እንለምነው። ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈ @Yemezmurgtm ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
9 Mar, 18:59
❤️ ከሊባኖስ ❤️
ሐና እና ኢያቄም ወለዱ ሰማይአዲሷም ሰማይ አስገኘች ፀሐይምስራቀ ምስራቃት የአምላክ መገኛከሊባኖስ ድንግል ነይ ወደኛ(፪)
የሕያዋን እናታቸው ሆነሽለቀደመች ሔዋን ጠበቃ ሆንሽደስተኛዋ ደስ ይበልሽ ማርያም ከአንቺ ወጣ የዓለሙ ሰላም(፪)
በወለዱሽ በሐና በኢያቄምተማጽነናል ድንግል ማርያምከአዳኝ ወጥመድ ከክፉ ጠላትልጆችሽን ጠብቂን ከጥፋት ከአዳኝ ወጥመድ ከክፉ ጠላትኢትዮጵያን ጠብቂያት ከጥፋት
9 Mar, 00:46
🌹እንኳን ለዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት ምኩራብ እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። መልካም ዕለት ሰንበት (ምኩራብ)ና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን። ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈ @maedot_ze_orthodox ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
8 Mar, 23:41
8 Mar, 21:15
ምን ሰማህ ዮሐንስ በማሕጸን ሳለህ /2/ህፃን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ /2/እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለህ ደስታ /2/ምን አይነት ድምፅ ነው ምን አይነት ሰላምታ /2/
ከተፈጥሮ በላይ ያሰገደህ ክብር እንዴት ቢገባህ ነው የእናታችን ፍቅር /2/ ሌላ ድምፅ አልሰማም ከእንግዲህ በኋላ ለውጦኛልና የሰላምታ ቃሏ /2/
በረሀ ያስገባህ ለብዙ ዘመናት ምን ያለ ራዕይ እንዴት ያለ ብሥራት/ /2/ አንደ አዲስ ምስጋና ስልቱ የተዋበ ተደምጦ የማያውቅ ጭራሽ ያልታሰበ /2/
ከሴት ከተገኙ ከደቂቀ አዳም ድንግል ስለሆነ በህይወቱ ፍፁም /2/ ከማህፀን ሳለ ተመርጦ በጌታ ለማዳመጥ በቃ የኪዳን ሰላምታ /2/
8 Mar, 12:36
እንደምነህ ቢሉት ዘመዶች ከድተውትሚስቱ ትታው ሄዳ ልጆች ሞተውበትዓይኖቹ በምሬት እንባ አላፈሰሱእግዚአብሔር ይመስገን ነበር የኢዮብ መልሱ /፪/
በሰጠበት መንደር ሲቆም ለልመናሚስቱ ሙት ስትለው ጌታን እርገሞ እናየስንፍናን ነገር አይሰማም ጆሮዬይክሰኛል እርሱ ይችላል ጌታዬ
እግዚአብሔር ይመስገን ቢጎድልም ቢሞላምለዓይኔ ሽፋሽፍት እንቅልፍ እንኳን ባጣምብዙ እንደነበረው ትናንትና ደጄ ክፉውንም ደግሞ ይቀበላል እጄ
8 Mar, 07:00
🛏 አልጋ መግዛት ለምትፈልጉ ኑ አልጋ ላሳያችሁ!
ይህ አልጋ የተራ ሰው ወይም የወታደር አልጋ አይደለም፡፡ የንጉሥ አልጋ ነው፡፡ ንጉሥም ቢባል ተራ ንጉሥ ሳይሆን በዓለም ሁሉ የሚዘመርለት ታላቅ ንጉሥ አልጋ ነው፡፡ የንጉሥ ዳዊትን አልጋ ላሳያችሁ፡፡ ይህ አልጋ ከወርቅ ወይም ከአልማዝ ወይም ከከበሩ ድንጋዮች የተሠራ አይደለም፡፡ ይህ አልጋ ከዕንባ የተሠራ አልጋ ነው፡፡ እርሱ ‘ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን አጥባለሁ ፤ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ’ ብሏልና’’ 'ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ' ♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
7 Mar, 11:45
እኛም ነበረብን(የዘላለም ሞት2×መስቀል ተሸክሞ ሲወጣ ተራራ(2×ይገርፉት ነበረ (ሁሉም በየተራ(2×ድንግል አልቻለችም እንባዋን ልትገታ(2×እያየች በመስቀል( ልጇ ሲንገላታ(2×በአምላክነቱ ሳይፈርድባቸው2×
ኢየሱስ ጌታ ነው (አልፋና ኦሜጋ(2×በመስቀል ተሰቅሎ እንዲያ እየቃተተ(2×አለምን ለማዳን (የማይሞተው ሞተ(2×ከሞት ሊታደገን በመጣልን ፈጥኖ(2×መስቀል አሸከሙት( ሁለታው ይህ ሆኖ(2×መከራውን ሳስብ ሳስታውስ ቀኑን(2×ይቆስላል ይደማል (ልቤ በሃዘን (2×መች ለራሱ ነበር ይህ ሁሉ መከራ(2×
ሙታን ከመቃብር( ተነስተው ሲያስተምሩ(2×እናታችን ሔዋን ወየው በይ አልቅሺየአንቺን ህመም ታሞ ከሞት ሊያድንሽየህያዋን ጌታ (ተሰቀለልሽ(2×አዬ ጉድ አዬ ጉድ አለም የኋላሽ(2×
ሰውነትሽ ራደ ሀዘን ከበበሽስቃይ ከመከራውም ዳግም ፀናብሽተሰቅሎ ስታይው አንድ (አምላክ ልጅሽ (2×ቢፈስም እንባዬ ሆኖ መንታ መንታ መች ዋጋ ይሆናል ለአንዲቱ ጠብታላለቀሽው ለቅሶ (ድንግል የዛ ለታ(2×
7 Mar, 11:37
እንክርዳድ ኑፋቄን ገበሬው ለይቶመልካም ዘር ሲዘራ ወደ ማሳው ወጥቶለአጨዳው ምጽአት ለበጋው አዝመራወዴት ወድቆ ይሆን ክረምት የተዘራ /2/
አዝ= = = = =
7 Mar, 07:00
ብርሃኔ አንተ ነህ ፀዳል አብርሆቴየመንገዴ መሪ መታያ ውበቴበፅልመት ዋሻ ውስጥ መኖሬ ተሰምቶህ ነጠከኝ ከጥልቁ እራስክን ሰውተህ ፪
5 Mar, 22:31
ነገር ግን እርሱ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ በእርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። ኢሳይያስ 53:5 መድኃኔ ዓለም ፍቅርህ ይማርካል ❤️😢
5 Mar, 18:44
እናቱ ታውቅ ነበረ መድኃኒት መሆኑንኢየሱስ አለችው ስታወጣ ስሙን
ከስጋዋ ስጋ ነስቶ ከነፍሷ ነፍስበተዋህዶ ሚስጢር የኛን ስጋ ቢለብስአማኑኤል ተባለ ቢዛመድ ከሰውቅዱስ እግዚአብሔር ከኛ ጋር ነው
የትንቢቱን መጽሐፍ እያነበበችሀር ወርቁን አስማምታ እየፈተለችዙፋኑ መሆኑን አውቃ ነበርናገለጸች እራሷን በፍጹም ትህትና
5 Mar, 18:36
ምን ሊለውጠው ያንተን ውለታምን ሊቀይረው ያንተን ስጦታለዘለአለም ታትሞ የሚኖርማን ይስተካከላል ጌታ ያንተን ፍቅር
አዝ =======
5 Mar, 14:57
ቸሩ ሆይ ቸሩ ሆይ ናና ቸሩ ሆይ አማኑኤል ናና የእስራኤል መና ቸሩ ሆይ ናና ቸሩ ሆይ መድኃኔዓለም ናና
ቸሩ ሆይ ሰምተህ እዳልሰማህ ቸሩ ሆይ አይተህ እንዳላየህ ቸሩ ሆይ ሁሉን ታልፈዋለህ ቸሩ ሆይ ፍቅራዊ አባት ነህ ቸሩ ሆይ አማኑኤል ጌታ ቸሩ ሆይ ቸሩ ፈጣሪያችን ቸሩ ሆይ ውለታህ ብዙ ነው ቸሩ ሆይ ለእኛ የዋልክልን
5 Mar, 10:03
3 Mar, 21:01
አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክበከሃዲዎች እጅ ተይዘህ ቀረብክ
3 Mar, 11:14
የእምነት ገበሬ መልካም ዘር የዘራበአምላኩ ታምኖ መቶ እጥፍ ያፈራአባ ተክለሃይማኖት የነፍሳችን ጌጥበጸና ኪዳኑ ምሕረትን የሚያሰጥ/2/
አዝ= = = = =ከምድር እስከ ሰማይ የተተከለ ዐምድሥላሴ ዘንድ ቀርቦ ለእውነት የሚማልድቅዱስ ተክለሃይማኖት በሁሉ የሚወደድጥግ ላደረጉት ሞገስ የዓለም ዘውድ
አዝ= = = = =ሰይጣን ክህደትን መንቆሮ ያጠፋበኪዳኑ የሚያኖር የድኩማን ተሰፋየዓለም ፀሐይ ነው የተመረጠ ዕንቁየዓለም ፀሐይ ነው የተመረጠ ዕንቁ
2 Mar, 00:45
❤️ እንኳን ለዓቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ቅድስት እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። መልካም ዕለት ሰንበትና (ቅድስት) የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን። ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈ @maedot_ze_orthodox ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
2 Mar, 00:37
ሰንበት ቅድስት ዕለተ እረፍትየደስታ ቀን ናት ዕለተ ትፍስህትየሰማይ መላእክት እግዚአብሔርን አይተው ያመሰገኑባት ሥሉስ ቅዱስ ብለው
ኑ በቅዳሴ በማኅሌት እናክብርጌታችን ሲመጣ እንዳይዘጋብን በርየሰንበት ጌታዋ በሰንበት ይመጣልቅድስቷን ከተማ ለጻድቃን ያወርሳል
በኩር ናት የበዓላት ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት በእሷ ደስ ይበለን በሰንበተ ክርስቲያን
ለአብርሃም ተገልጣለች ለሙሴም በደብረ ሲናበነቢያት የታወቀች ሰንበት ዳራዊት ናት እናበሳምንቱ ሰለጠነች ተሰበከች በሐዋርያትሃሌ ሉያ ዕለተ ሰንበት ተሰጠችን ልናርፍባት
እግዚአብሔር አብ የባረካት እግዚአብሔር ወልድ የቀደሳትከእለታት ሁሉ መርጦ መንፈስ ቅዱስ ከፍ ያደረጋትበእርሷ ሀሴት እናድርግ እናክብራት እንድንከብርየደጀሰላሙ ታዛ በመቅደሱ እንሰብሰብ