💛💞መልካም ልቦች™💞💛


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOM TO MELKAM LBOCH 💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE ያድርጉ 🙏
➤ For any promotion and Advertising 📩
👉 @Z_afro ያነጋግሩ::

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


✅ አሁን online ላላችሁ ብቻ ቦታችንን /start ላለ ሰው ዛሬ ማታ የ 500 ብር ሞባይል ካርድ እንልካለን መልካም ቀን👏🎉

ቦቱን /start የሚለውን በመንካት Start በሉት ከዛ inbox መተን እንከፍላለን🫡


.            " ሀናን🧡 "

╚─━━━━░★░━━━━─╝

በ የፍቅር ቴሌግራም ♡ የቀረበ
      ልብ አንጠልጣይ ታሪክ

.   
#ክፍል_ሁለት (❷)
┗•━•━•━ ◎ ━•━•━•┛

አሁን መዋደዳችን ወደ ፍቅር እየተቀየረ ነው የሱን ባላቅም እኔ ግን ፍቅሩ በጣም በርትቶብኛል ሁሌም ስለሱ ማሰብ ጀምሪያለው ታድያ አንድ ቀን ጓደኞቼን አህላምና ሰሚራን ቤት ጠራኃቸው ከተጨዋወትን በሃላ ምክራቸውን ፈልጌ ሁሉንም ዘርዝሬ ነገርክዋቸው ሁለቱም ገረማቸው እኔ እንደዚ አይነት ነገር እንደማላስብ ነበር የሚያውቁት ሆኖም ግን ምክራቸውን ጠየቅክዋቸው ሁለቱም መከሩኝ

ሰሚራ፦ "ቆይ መች ነው የጀመረሽ"

እኔ፦ "ቆይትዋል ግን እንዲ በቀላሉ እሸነፋለው ብዬ አላሰብኩም ነበር"

አህላም:- "ውዴ ደግመሽ አስቢበት ትምርትሽ ላይ focus እንደምታረጊ ነበር የማውቀው ደሞም ትምህርታችንን ሳንጨርስ ስለንደዚ አይነት ነገር እንደማናስብ ተነጋግረን አልነበር?"

እኔ:- "አዎ ተነጋግረናል ግን እንዲ አልመሰለኝም መጀመሪያ ባላውቀው ይሄ አይፈጠርም ነበር"

ሰሚራ:- "እሺ አሁን እኛ ምን እንርዳሽ እናናግርልሽ ነው?"

እኔ:- "ሰሙ ፍቅሬን እንዴት እንደምገልፅለት ብቻ ንገሩኝ"

አህላም:- "እሱ ግን እንደሚያፈቅርሽ ወይም ላንቺ ያለውን ስሜት ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ?"

እኔ:- "አዎ በጣም ይወደኛል"

ሰሚራ:- "እንደሚወድሽ ነግሮሻል?"

እኔ:- "አይ አልነገረኝም"

ሰሚራ:- "እሺ ፍቅርሽን አልቀበል ቢልሽስ?"

እኔ:- "ምንም ይበለኝ ብቻ እንደማፈቅረው ነው መናገር ምፈልገው ደሞ እርግጠኛ ነኝ ፍቅሬን ይቀበለኛል"

አህላም:- " እሺ ደስ ያለሽን አድርጊ ግን ውዴ የቀረበሽ የሳቀልሽና የተንከባከበሽ ወንድ ሁሉ ያፈቅርሻል ማለት አይደለም ስለ ሳቀልሽና ሁሌም ስለምታገኚው ይወደኛል ብለሽ እንዳታስቢ"

...ውይይታችን ይሄን ይመስል ነበር ተወያይተን ከጨረስን በሃላ የአህላም ንግግር በጣም አስጨነቀኝ ደጋግሜ ማሰብና  ከራሴ ጋር መከራከር ጀመርኩኝ "የማይወደኝ ከሆነ ለምን እንደሚወደኝ ያስመስላል?" ብዬ ለራሴ እጠይቅና እራሴውም እመልሳለው "ይወደኛል
ውዴታውን ያልነገረኝ አፍሮኝ ይሆናል " እላለው...

..ብቻ የምናፈቅረውን ሰው በጊዜ መናገር ከጭንቀት መገላገል ነው ይህንን በጊዜው አላሰብኩትም ነበር ጓደኛዬ አህላም ያለቺኝን ስላሳሰበኝ እንደሚያፈቅረኝ ለማረጋገጥ ወሰንኩኝ ስለዚ እንደማፈቅረው ከመናገሬ በፊት እንደሚያፈቅረኝ ማረጋገጥ ፈለኩኝ።

#ክፍል_ሶስት ( ⓷  ) .. ይቀጥላል....
┍──━──━──┙◆┕──━──━──╝


✎ክፍል 3 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️    ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።


  ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8

💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333


" ሀናን🧡 "


      ልብ አንጠልጣይ ታሪክ

  
#ክፍል_አንድ ( ⓵ )
   ❦•⊰❂⊱• ════ ❦

... ሰላም ሀናን እባላለው ጓደኞቼ ሃኒ ይሉኛል የ አዲስ አበባ ልጅ ስሆን የቤታችን 2ተኛ እና የመጨረሻ ልጅ ነኝ አልሃምዱሊላህ ቤተሰቦቼ ደስተኛ አድርገው አሳድገውኛል። የሚያስፈልገኝን ሁሉ ያሟሉልኛል አሪፍ ትምርት ቤት ያስተምሩኛል ብቻ ምንም ሳይጎልብኝ ደስተኛ ሂወት እንድኖር ወይም ዛሬ ላይ እንድደርስ አድርገውኛል ..

አባቴ ከልጅነቴ ጀምሮ ጨዋ ሴት ሆኜ እንዳድግ ምኞቱ ነበር ብዙም ጊዜ ይመክረኛል መፃፍትም እየገዛልኝ እንዳነብ ይረዳኛል ሁሉንም የሚያደርገው በእድሜዬ ልክ ነበር ልጅ እያለው የተረት መፃፍት እየገዛ ስጦታ ይሰጠኛል አደግ እያልኩኝ ስመጣ ደሞ ከእምነቴ ጋር የተያያዘ መፃፍት እና  የሃገሬን እንዲሁም የመልካም ሴቶችን ታሪክ የማውቅበትም መፃፍት ይገዛልኛል በአጭሩ አባቴ በራስዋ የምትተማመን ጠንካራ እውቀት ያላትና ብልህ ሴት እንድሆን ይጥር ነበር ( ይህ ሁሉ የሚያደርግልኝ በፍቅር ነበር ፍቅር እየሰጠኝ እንደ ጓደኛ ሆኖ ቀርቦኝ እያጫወተኝ አንዳንዴም ወጣ አድርጎ ወክ እያረግን ነበር የሚመክረኝም የሚያዝናናኝም)

"ሁላችንም መጨረሻችንን አናውቀውም የሆነ ሰው ልክ እንደ  መልአክ  ሆኖ ወደኛ ሂወት ይገባና ህልማችንን ለማሳካት ሰበብ ይሆነናል ወይም ደሞ እንደ ሸይጣን ቀርቦ ህልማችንን ያጨልምብናል"

... ሃናን ማለት ተጫዋች ሳቂታ ለሰዎች የምታዝን ከሁሉም ጋር ግባቢና ስቃ መዋልን የምትችል ግልፅ የሆነች የኮሌጅ የሁለተኛ  አመት ተማሪ ነች...


...ከላይ ያለሁት እኔ ነኝ እራሴን በትንሹም ቢሆን የገለፅኩላቹ ይመስለኛል ዛሬ የኮሌጅ ህይወቴን አጫውታችኋለው ምክንያቱም ማፍቀር የጀመርኩት College ላይ ነበርና..

...College ብዙ ትምህርት ያስተምርሃል ከብዙ ሰው ጋር ያስተዋውቅሃል ከባህሪህ ጀምሮ እስከ አመለካከትህ ይቀየራል ለዛም ነው እኔ College  እንደገባው አካባቢ የድርዋ ሳቂታዋ፣ ከሁሉም ጋር መግባባት የሚያምራት ሃኒ ሳልሆን ኮስተር ያለች ውስን (ቁጥብ) ሴት የሆንኩት ኮሌጅ ውስጥ ሁለት የሴት ጓደኞች ያዝጉኝ ሰሚራ እና አህላም ይባላሉ ሁለቱም እንደምፈልጋቸው አይነት ጓደኞች ናቸው እኔን መሳይ ናቸው...

ሰሚራ ከአንድ ከቆንጆ ልጅ ጋር አስተዋወቀቺኝ የሱፍ ይባላል በጣም ቆንጆ ነው ረዘም ያለ ቀይ አረብ መሳይ ሙሉ ፂም ያለው ብቻ ከቆንጆ ልጅ ጋር አስተዋወቀቺኝ።

..ከብዙ መተዋወቅና መግባባት በኋላ ሁለታችንም ተዋደድን በግልም ከትምርት ቤት ቀን ውጪ መገናኘት ጀመርን ብዙ ነገር አሳየኝ ነገር ግን ሁለታችንም እወድሃለው እወድሻለው አልተባባልንም እንደሚወደኝ አውቃለው እንደምወደውም ያውቃል ግን ተፋፍረን ይሁን ተፎካክረን ሁለታችንም የፍቅር ጥያቄ አላቀረብንም ግንኮ በጣም ነው የምንዋደደው ቆይ እስቲ ግዴታ እወድሃለው እወድሻለው መባባል አለብን ወይስ ዝም ብለን እንደምንዋደድ እናውቃለን ግን ምንም የፈቅር ቃል ሳይወጣን ዝም ብለን እንቀጥል??

#ክፍል_ሁለት...❷..ይቀጥላል
✿❯────「✿」────❮✿

✎ክፍል 2 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️    ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።


  ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8

💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333


ቤተሰብ ነገ አዲስ ታሪክ ልጀምርላችሁ አስቤአለው እስቲ በ reaction አበረታቱ👍👍👍


━━━━━━━✦✦━━━━━━━

         ከፈገግታ ጀርባ



ልሳቅ እንዳመሌ ሁሌም ልፍለቀለቅ
የፊቱም የኋላ ጥርሴ ወቶ እስክያልቅ
የውስጤን ልብ ምት በጥርሴ ልደብቅ
ችግሬን ጉዳቴን ማንም ሰው እንዳያቅ
ይህም ያልፋል በሚል ተስፋየን ልሰንቅ
😅😅😅😅😅😅😅😅😅😅
ማን ቀርቦ ጎበኘው የልቤን ትርታ
ደህና መሠልኩንጂ በፊቴ ፈገግታ
የሳቀ ሰው ሁሉ ከተሰማው ደሰታ
አልቃሽ አይገኝም ሳቅን ትቶ ላፍታ
💔💔💔💔💔💔💔💔💔
ሁሌም የምስቀው ጠፍቶኝ አይደል እንባ
ጤፍም ከፍሬው ይልቅ ብዙኣለው ገለባ
በሰላም ያለእንከን ወጥቼም ብገባ
ደም ነው የማለቅሰው ከፈገግታ ጀርባ
ደም ነው የማለቅሰው ከፈገግታ ጀርባ
👀👀👀💔💔💔💔💔👀👀👀


ነገር በእርጋታ
ቁጣን በፈገግታ
ሳቅን በጫወታ
ፍቅር በትዝታ
ሰላም ያለው ሂወት ይሰጣል  እርካታ😍


💔የማያሽር...ጠባሳ💔
፨።።።💘💘💘።።።፨

ቀኑም አይመሽልኝ ለሊቱም አይነጋ
ልቤ እየተቀጣ በሀሳብ አለንጋ
ከልብ ውስጥ የማይጠፋ ከቶ ማይረሳ
ህመሙ የማይድን የማይሽር ጠባሳ
ቁስሉ የሚቆጠቁጥ የህሊናን ዕዳ
አሸክማኝ ሄደች በሰውፊት አዋርዳ
ሀዘን ድንኳ ጥሎ ጎጆውን ቀልሶ
ልቤውስጥ ይኖራል ጎኔን ተንተርሶ
ልቤ ፍቅርን ብሎ ለፍቅር ባደረ
ሀዘን ቤቴን ወርሶት ቅስሜ ተሰበረ
.
.
.
ያላረኩት የለም ልቤን ለማሳመን
በደልሽን ችዬ ካንቺ ጋር ለመሆን
ግን አንቺ አልገባሽም ባንቺ መጎዳቴ
በብርሀን ጭለማ መሆኗን ህይወቴ።።።።


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━


ታላቁ አስማተኛ


ታላቁ አስማተኛ (Magician) ሃሪ ሁዲኒ፤ በሆነ ወቅት ላይ ከየትኛውም እስርቤት ማምለጥ እንደሚችል ምሎ ተናገረ።

#ማድረግ_የሚጠበቅበትም...

ሱፉን እንደለበሰ መታሰር እና በአንድ ሰዓት ውስጥ ያለምንም ችግር ከእስርቤት ማምለጥ ብቻ ነው።

#እናም

ብዙ አመታትን ያስቆጠረ… አንድ በምዕራብ የሚገኝ እስር ቤት የሁዲኒን (የአስማተኛውን) ጥያቄ ተቀበለ፡፡

ሁዲኒ በሚታሰርበት እለት

ሰዎች መጨረሻውን ለማየት በእስር ቤቱ ቅጥር ማዶ ተሰበሰቡ።

ሁዲኒ በራስ በመተማመን ስሜት እንደተሞላ ወደ እስር ቤቱ ገባ። የእስር ቤት ጠባቂዎችም በብረት በር በተዘጋ ክፍል ውስጥ አስቀመጡት።

ሁዲኒ ኮቶን አወለቀ። ቀበቶውንም ፈታ።

በሁዲኒ ቀበቶ ውስጥ የተሸሸገ፤ እንደ ሸቦ የሚተጣጠፍ እና ሃያ ሳንቲ ሜትርየሚሆን ብረት ነበር። ሁዲኒ ስራውን ጀመረ።

ለሰላሳ ደቂቃዎች ያህል በሩን በያዘው ብረት ለመክፈት ታገለ። ይዞት የመጣው በራስ መተማመን አሁን ላይ ከእርሱ የለም።

አንድ ሰዓት ሆነው። በላብ ተጠምቋል

ሁለት ሰዓታትን ከበሩ የቁልፍ ሸንቁር ጋር ሲታገል አሳለፈ። ደከመው ሁዲኒ በተሸናፊነት ስሜት ጭንቅላቱን በበሩ ላይ አስደገፈው… በሩ በቀስታ ወደ ውጪ ተገፋ… ተከፈተ። ይህ በር በጭራሽ አልተቆለፈም።

ሆኖም በአንድ ሰው አእምሮ ውስጥ ይህ በር ተቆልፎ ነበር።

#በሁዲኒ ጭንቅላት ውስጥ

ከአለም ካሉ ሁሉ ጋኖች በሚበረታ ጋን ተቆልፏል፡፡

ማንም ቁልፍ ሰሪ

እንደዚህ አይነት ጠንካራ ቁልፍ አልሰራም።

አእምሮ ሃይል አለው! ምን ያህል በሮችን በራስህ ላይ ቆልፈሃል? ዖዖዖ

ምን ያህል ጊዜስ… ራስህ በሰራኸው የአእምሮ እስርቤት ታስረሃል? ? ? ?

በቀላሉ የሚፈቱ...

ግን አንተ በራስህ ላይ ያወሳሰብካቸው ምን ያህል ችግሮች አሉብህ? ? ? ?

#አንድ_የአፍሪካውያን_አባባል_አለ

''በውስጥህ ጠላት ከሌለ፤ ከውጭ የሚመጣ ጠላት አንተን መጉዳት አይችልም።''

በአለም ሁሉ ካሉ ውሸታሞች በላይየአንተ አእምሮ አንተን ይዋሸሃል፡፡ ይህን ማድረግ አትችልም… እንዲህ መሆን አትችልም... አቅሙም ብቃቱም የለህም...

#ምክንያቱም

ልክ እንደ ሁዲኒ የተቆለፈውን በር ብቻ ነው የሚያሳየን።

ከፍተህ ውጣ... አእምሮህ የሚልህን አትመነው።

ይህ አስተማሪ መልእክት በርካቶች ጋር ደርሶ ይማሩበት ዘንድ

#like

#share ማድረግን አትርሱ


      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
 💔
@MELKAM_LBOCH13 💔
💔 
@MELKAM_LBOCH13 💔


♾ነገ ማታ አንድ ምርጥ ታሪክ እንጀምራለን🚨


ፈገግ ስትይ ያየሽ ሰው አብሮ ፈገግ ይላል፣ ይጋባል፣ ልብ ይሰርቃል፣ አይንሽ የሚያወራ ይመስላል አንዳንዴ ምን እያልሽኝ እንደሆነ ሳስብ የውስጤን ያየሽ እየመሰለኝ ሀፍረት ይሰማኛል፣ ስትናገሪ የድምፅሽ ቃና ከጭንቅላት አይጠፋም ....🤌❤️‍🔥

እናቴ እወድሻለው...🤌


♾!መልካምነት!♾


ወደ ስራ ስሄድ አንድ የስልክ እንጨት ላይ የተለጠፈ ወረቀት አየሁኝ..

____ ጽሁፉ እንዲህ ይላል

"እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር ጠፍቶብኛል ያገኘ ሰው ካለ እባካችህን አድራሻዬ በሚቀጥለው መንገድ በቀኝ በኩል ስትታጠፉ ያለው አሮጌ ቤት ነው።”

“አይኔ እንደፈለግኩኝ አያይም : እድሜዬም ገፍቷል ልጆችም የሉኝም"

ይህንኑ ጽሁፍ ተከትዬ ወደ አሮጌው ቤት ስሄድ አንዲት ሴትዮ ደጃፍ ላይተቀምጠዋል የእግር ኮቴየን ሰምተው "ማነው? ማን ልበል?" አሉኝ

"እዚህ መንገድ ላይ 50 ብርአግኝቼ ነው እሱን ልሰጥ ነው የመጣሁት" ብዬ መለስኩላቸው

አሮጊቷ እንባ ቀደማቸው -

"ልጄ! እስካሁን ድረስ ከ40 በላይሰዎች 50 ብር መንገድ ላይ ወድቆ አገኘን ብለውኝ መጥተዋል"

ቀጠሉ እማማ - "እኔ ይህንን ጽሁፍ አልጻፍኩኝም: ጽሁፍ ለመጻፍም ሆነ ለማንበብም አይኔ እሺ አይለኝም" _50 ብሩን በእጃቸው አስጨበጥኳቸው

ጽሁፉን ከስልክ እንጨቱ ላይ እንድቀደው ቢነግሩኝም አላደረግኩም: የመጣውን

____ ሰው ሁሉ ይህንኑ ነበር የሚሉት

ይህንን ጽሁፍ የጻፈውን ሰው እንዴት እንዳደነቅኩት : እኚህን ሴትዮ ለመርዳት የሄደበት ርቀት በጣም ነው ያደነቅኩት!

ከሴትዮዋ ቤት ስወጣ አንዲት ወጣት ልጅ አስቆመቺኝ

"ወንድሜ! እዚህ መንገድ ላይ 50 ብርአግኝቼ ነበር የቤቱ አቅጣጫ በየት በኩል እንደሆነ ታውቃለህ እንዴ?"

በልቤ እየሳቅኩኝ ቤቱን ጠቆምኳት

!መልካምነት!


      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀
 
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
💔  @MELKAM_LBOCH13 💔


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ

                        ክፍል  
2️⃣5️⃣

ይዟት ወጣ ቀድም እሱ ዘለለ በዚህ በኩል እኔን እረግጣ ዘለለችና ወደቤቷ ገባች።

በዛ መሀል ልእልት ምን እያሳለፈች እንደሆነ ቤት ምን እንደጠበቃት ከምን አይነት ችግርO እንዳጋፈጥኳት ማሰብ ከብዶኝ እራሴን በጭስ ውስጥ ለመደበቅ ዝም ብዬ ያለማቋረጥ ማጨስ ጀመርኩ።

ከልእልት ችግር በላይ ደሞ የእዮብ ዝምታ ይበልጥ አስፈራኝ።

እስከማታ በጭንቀት ውስጥ ምንም ሳናወራ አሳለፍን ማታ ላይ እዮብ አጠገቤ መጥቶ ቁጭአለና ታቃለህ ፈጣሪ እዚህ ምድር ላይ ብዙ ነገሮችኝ ውብ አድርጎ ፈጥሯል ከዛም ውስጥ በጣም ውቡ ፍቅር ነው ግን ፍቅር ሚዋበው ላደለው ሰው ብቻ ነው።

ፍቅር ላንዳንዱ ህይወትን ይሰጣል ላንዳንዱ ደሞ ህይወትን ይነጥቃል፡፡

ባህራን እኔ በምወደው አባቴ እምልልሀለሁ ልእልትን ከልቤ ነው ማፈቅራት አይቼ አልጠግባትም የዋህነቷ ፍቅሯ የውስጧ ንፅህና እኔጃ ሰው እንደሷ ሚፈጠርእራሱ አይመስለኝም ግን ስላፈቀርኳት ስለወደድኳት ወዳንተ እንድትቀርብ መንገዱን አመቻቸሁ ምክንያቱም እኔ እራስ ወዳድ አደለሁም ይቺን የመሰለች ልጅ ከኔ ከሱስኛና ህይወቱ ካበቃ ቦርኮጋ እንድትሆን ማደርጋት እኔ እራስ ወዳድ አደለሁም

አንተን ስላመንኩህ ከልብህ ሰው ነህ ብዬ ስላሰብኩ ነው ትናት ሁለታችሁ እንድትገናኙ እኔ ወጥቼ የሄድኩት ግን አንተ ይቺን ንፁህ ልጅ ፍቅሯን መቀማትል ሳያንስ ክብሯን ገፈፍካት አሁን ሳትፈልግ በግድህ አብረሀት ትሆናለህ አለኝ አነጋገሩ ይበልጥ አናደደኝ። ደፍሪያት አደለምኮ የሰራሁት ነገር ልክ አደለም ግን ማንም ሰው ሳልፈልግ አብሪያት እንድሆን አያስገድደኝም አልኩት።

እዮብ ተናዶ ትቶኝ ወጣ እኔ ቤት ውስጥ ቁጭ ብዬ በጭንቀት ለመፈንዳት ምንም አልቀረኝም፡፡

የመጨረሻ ደረጃ ላይ ስደረስ ቤቱን ትቼ ወጣሁ እዮብ ሊኖርበት ይችላል ብዬ ያሰብኩት ቦታ ምንም አልቀረኝም ላገኘው አልቻልኩም፡፡

ማታ አምስት ሰአት አካባቢ ምንተኛበት ወደነበረው ቤት ሄድኩ የለም ሁሉንም ጠየኳቸው እንዳላዩት

ዝም ብዬ መጓዝ ጀመርኩ እናቴ ከሞተች ጀምሮ ብቸኝነት በጣም አፈራዋለሁ ጥሩ ስራ ስሰራም ይሁን መጥፎ ስራ ስሰራ ሰው አብሮኝ እንዲኖር እፈልጋለሁ ብቻ ስለመሆን ማሰብ በራሱ ሰላም ይነሳኛል።

ብቻ የዛን ቀን እዮብ ቢያንስ ቤት ከመጣ ብዬ ቤት ገብቼ ጠበኩት የለም። በነጋታው 11 ሰአት አካባቢ ወደናቴ መቃብርጋ ሄድኩኝ ። መቃብሯ ላይ ያለውን ፎቶ ቀና ብሎ ለማየት ድፍረቱን አጣሁ። የተፈጠረወን አንድ ባንድ ነገርኳት።

ለሳምንት ያህል ከእዮብም ከልእልትምጋ ሳልገናኝ ሁለቱም አድራሻቸወን አጥፍተው ጠፉብኝ ሳምንቱ የአመታቶችን ያህል እረዘመብኝ።

መብላት ሁላ አቃተኝ።

ከዚህ በፊት እዮብ ሱሰኛ ስትሆን ሱስህ ነው ጓደኛህ ያለኝን አስታውሼ በየሰአቱ አንዴ አንዱን አንዴ አንዱን በቃ በላይ በላይ እጠቀማለሁ ግን ለኔ ምንም ሱስ ጓደኛ ሊሆነኝ አልቻለም።

ከሳምንት ቡሀላ እኔ ተነስቼ እዮብን ፍለጋ ስወጣ ወደቤት እየመጣ አየሁት፡፡

እንዴት ደስ እንዳለኝ እኔ አቃለሁ ግን የውስጤን እምቅ አድርጌ ይዤ ሳየው ተኮሳትሬ ቆምኩኝ።

አታስመስል ባክህ ውስጥህ እየሳቀ ግንባርህን አትቋጥር ብሎኝ ወደቤት ገባን።

ቁጭ ብለን ማውራት እንዳለብን ነግሮኝ ማውራት ጀመርን፡፡

በተለይ ስለልእልት ብዙ ነገር አወራኝ ሴት ልጅ ጉልበቷ እንባዋ ነው በተለይ ደሞ ለእንደ ልእልት አይነት ሴት ሰውን ተናግሮ ማስቀየም ለማይችል ምስኪን ሴት ከእንባ በላይ ጉልበት የላቸውም። በዚህ ምድር ላይ ለመኖር ተስፋ እንደቆረጥክና ጨካኝ ሰው እንደሆንክ የገባኝ ከልእልትጋ አድረህ ምንም እንዳልተፈጠረ ኖርማል ስትሆን ነው አለኝ ማለት አልኩት?

ቢያንስ ቢያንስ በጣም መፀፀት ማልቀስ ማንባት ነበረብህ ይቺን ልጅ ሳትወዳት ሳታፈቅራት የውሸት ጋጋታ ደርድረህ አብረሀት ካደርክ ከመድፈር በምንም አይተናነስም ባህራን ውስጥህን ሳየውኮ እንደዚህ አይነት ሰው አትመስለኝም አለኝ። አልነበርኩም እናቴ እስክትሞት እንደዚህ አልነበርኩም የእናቴ ሞት ሰወነቴን ንፁህ ልቤን ሁሉንም ነገሬን ነው ያሳጣኝ አልኩት።

ምናልባት ፈጣሪ አንዷን እናትህን ወስዶ ሌላ እናት ሊሰጥህ አለመሆኑን በምን አወክ???

መመለስ አልፈለኩም ይልቁንም ልእልትን ከእናቴጋ ማወዳደሩ አበሳጨኝ።

ዝም ብዬ ተነስቼ ከቤት ወጣሁ ልእልትና ወንድሟ በኛ በር ላይ እያለፉ ነበር፡፡ ስታየኝ አንገቷን ደፋች እኔም ሳያት ልቤ መታ ፊቷን ተመለከትኩት ጥቁርር ብላለች የለበሰችው ልብስ እዚህ ግባ አይባልም ፀጉሯን ሁለት ቦታ ሰርታው አሲዛዋለች በዛ ላይ እንዳለ ተነጫጭቷል፡፡

አሳዘነችኝ ያ የበፊት ነገሯ ፊቴ ላይ መጣብኝ ቢያንስ ደስተኛ ባላደርጋት እንኳን ለሀዘኗ ምክንያት መሆን አልፈልግም ነበር።

ባጠገቤ ከወንድሟ ደና ግልምጫ ደርሶኝ አልፈው ሄዱ።
ባጠገቤሼ ወደውስጥ ገባሁና ለእዮብ ነገርኩት እዮቤ ልእልትንኮ አየኋት አልኩት።
ከተቀመጠበት እንዴት እንደተነሳ አላቅም የታለች የታለች እያለ ወደ ውጭ ወጣ ከሩቅ እየታጠፉ ከጀርባዋ አይቷት ተመልሶ ገባ።

አየሀት እእ እንዴት ናት ካየኋትኮ ሳምንት ሆነኝ ጠቁራለች ወይስ እንደበፊቱ ናት???? አለኝ::

ፊቷ ተቀይሯል አልኩት። ወዲያው የሱም ፊት ተቀየረ ምናለ ላንዴ እኔን በወደደችኝና በምላሹ ምሰጣትን ክብርና ቦታ ምናለ ልእልት ትንሽ ቀደም ብላ ወደህይወቴ

በመጣች ኖሮ አለኝ። ግቢ ውስጥ ከወዲያ ከወዲህ እየተንጎራደደ ባህራን ግን እንዴት አስቻለህ ምንም አልናፈቀችህም ምንም ትዝ አትልህም በቃ የጥያቄ መአት አከታተለብኝ ሲሰለቸኝ ትቼው ከቤት ወጣሁ።

ሰፈር ውስጥ ሰው እንዳያየኝ ፈጠን ፈጠን እያልኩ ስለምራመድ ከመቼው አስፋልት እንደደረስኩ አላቅም ።

እኔ በዚህኛው አስፋልት ቆሜ ልእልት በዛኛው አስፋልት ቆማ ፊት ለፊት መተያየት ጀመርን ። ሳያት ሳያት ውስጤ ምን እንደሚሰማኝ አላቅም እያዘንኩ ይሁን እየተከፋሁ ለራሴም አይታወቀኝም ሳያት ታሳሳኛለች ብዬ እራሴን ለማሳመን ብሞክርም አልችልም አይ በቃ ህይወቴ ውስጥ ምንም ዋጋ የላትም ተራ ሰው ናት ብዬ ለማሰብም እቸገራለሁ ።

ነገሮች ውዝግብ እንዳረጉኝ ጊዜያቶች ተቆጠሩ ጊዜዎች በሄዱ ቁጥር ደሞ እኔ እዛ ሰፈር መሄድም አቆምኩ እዮብ ደሞ የልእልትን አይን ለማየት ከዛ ሰፈር መውጣት አቆመ ብል ማካበድ አይሆንብኝም ቀስ በቀስ ለሱሱ ሚሰውን ጊዜ እየቀነሰ እሷን ጥበቃ ሰፈር መታጠፊያ ላይ ቁጭ ብሎ መጠበቅ ስራው አደረገው......


🔻ክፍል  2️⃣6️⃣ ላልተወሰነ ግዜ ተቋርጧል እሱ እስኪቀጥል አንድ ምርጥ ታሪክ የምናደርሳችሁ ይሆናል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀
 
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
💔  @MELKAM_LBOCH13 💔

➖የዩቲዩ ገፃችን➖
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction33


ምክር ነገር ለ እህቶቼ ይድረስ በደምብ ሼር አድርጉት🙏


እኔና ባሌ አራት አመታትን በፍቅርኖረናል። በትዳር ደግሞ 4 አመታትን ትዳርና ፍቅር የተለያየ ነው እያልኩ አይደለም።

እኔና ባሌ ከትዳር በሓላ ጥሩ የፍቅርህይወት አልነበረንም ለዛ ነው ባሌ በጣም ዝምታኛ ነው ምንም ነገርአጥፊቼ ብሆን አይቶ ዝም ይላል።

ስለዚህ የበላይነት ይሰማኝ ጀመረ ጓደኞቼም ጀግና እንደሆንኩ መሰከሩ ታዲያ ኩራቴ የበለጠ ጨመረ ለባሌ ምንም አይነት ክብር መስጠት አቆምኩ።

የትም ውዬ ማታ ላይ እመጣለሁ ባሌ በጣም ተናዶ እንኳን ዝም ይላል።

ታዲያ አንድ ቀን አምሽቼ ወዴ ቤት ስመጣ በጣም ተናዶ ቆይ ለምን ለትዳርሽ ክብርአይኖርሽም የድሮ ፍቅራችን ወዴት ሄደ አለኝ።

እኔ ንቄ ገፍቼው ልገባ ስል በጥፊ መታኝ ለመጀመሪያ ጊዜ በጥፊ መታኝ ለመጀመርያ ጊዜ በኔ ላይ በር ቆልፎ እሱ ቤት አደረ።

ጠዋት ላይ ቤተሰቦቼ መጥተው ፖሊስ አምጥተው እሱን እስር ቤት ወሰዱት ከዛም ከእስር ቤት አስወጥቼ የፍቺ ጥያቄ አቀረብኩ።

ሁሉም ሰው ትክክል ነሽ አለኝ ጓደኞቼም ጥሩ አደረግሽ የት አባቱ አሉኝ።

ከዛ እሱም በሀዘን ተሞልቶ ድርሻዬን ሰጥቶ ብቻውን ተቀመጠ ። ከሁለት ዓመት በሓላ እሱ ሌላ ሚስት አግብቶ ልጆች ወልዶ ጥሩ ህይወት እየኖረ ነው ።

የኔ ህይወት ግን ተበላሸ ። ትላንት ትክክል ነሽ ያሉት ሁሉ ዛሬ ትክክል አይደለሽም አሉኝ ።

ትላንት የት አባቱ ወንድ የት ጠፍቶ ያሉት እነሱ ለእራሳቸው ጥሩ ህይወት እየኖሩ ነው እኔ ግን ብቻዬን ቀረሁ ትላንት ከአንቺ ጋርነን ያሉት ሁሉ ዛሬ ከኔ ጋር የሉም

እህቶቼ ሴት ልጅ በተፈጥሮ ጠቢብ ናት የተበላሽ ትዳር ማስተካከል ትችላለች ።

ስለዚህ በትዳራችሁ ባልሽ ሞኝ ቢሆን እንኳን አንቺ ትዳርሽን ማስተካከል ትችያለሽ በትዳር መቀልድ ግን ትልቅ ዋጋ ያስከፍላል።

ለትዳራችሁ ክብር ስጡ ትዳር የሴት ልጅ ውበት ነው። በትዳራችሁ መሀከል ለሚገባ ሰው መንገድ አትክፈቱ።

ከእንደዚህ አይነት ሰው እራቁ ምክሩንም አትስሙ።

ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ ደግሞ ፍፁም በጎነት ነው፡፡ በምድር ላይ የምናደርጋቸው መልካም ነገሮች ሁሉ ቀጣይ አለም ላይ ደመወዝ ሆነው ይከፈሉናል ፡፡ ሁሌም ቢሆን ከክፋት ይልቅ በጎ በጎውን ነገር እናስብ መልካምነት ለራስ ነውና።


      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀
 
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
💔  @MELKAM_LBOCH13 💔


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ

                        ክፍል  
2️⃣4️⃣

ለምን ቀና ብላ እንደማታየኝ ጠየኳት፡፡

ማታ ያወራሁት ከልቤ እንደሆነ ጠየቀችኝ፡፡ ማታ ምን እንዳወራሁ ትዝ እንደማይለኝ ነገርኳት፡፡

በቆመችበት እንባዋ ዱብ ዱብ እያለ አየህ እኔምኮ የፈራሁት ይሄን ነበር አለች፡፡

ማለት አልኳት፡፡

በቃ ሌሊቱን ሙሉ ሳለቅስ ያደርኩት ይሄ እንደሚፈጠር ግልፅ ስለሆነ ነው......

ደና ደሩልኝ ሼር እያረጋችሁ ብዙ ሰው እንደምትጋብዙ አምናለሁ አንተ እኔን መውደድ አትችልም በእጅ የያዙት ወርቅ ማለት ልክ እንዳንተ ነው አለችኝ። ማታ ያወራሁት ብዙም ትዝዝዝ አላለኝም ነበር።

ለምን እንደዚህ እንደምትዘባርቅ ጠየኳት። ማታኮ ስላልነገርከኝ እንጂ ከኔ ፍቅር እንደያዘህ ነግረኸኝ ነበር አለችኝ። በሰአቱ የሷን ልብ መስበርም አልፈለኩም ግን ደሞ ከሷ ፍቅር እንደያዘኝ እንድታስብም መፍቀድ አልቻልኩም ዝም ብዬ አየኋትና ለምን እንደዛ እንዳልኳት አብራራሁላት ። መንገድ ላይ ፋኖሰና ባሏን አይቼ ስለቀናሁ ያንን ሁላ ውሸት እንደዋሸሁ ነገርኳት፡፡

አለቀሰች፡፡ ሴት ልጅ በዛ ልክ አሳዝናኝ አታቅም፡፡ ሌላ ውሸት ዋሽቼ ላረጋጋት ፈልጌ ነበር ግን መሆን እንደሌለበት ለራሴ አሳምኜ ዋጥጥ አደረኩት፡፡

ልእልት ከቤት ለመውጣት ፈራች፡፡ ከኔጋም መቆየቱ አልተዋጠላትም። ስልኳን ከፈተችው ወዲያው እዮብ ደወለና መጮህ ጀመረ ። ምን እንደተፈጠረ ደጋግማ ጠየቀችው ልእልት ጠፋች ተብሎ ሰፈሩ በሙሉ ሩዋንዳ እንደተደረገ ነገራት...አውቃው ነበር መሰለኝ ብዙም አልደነገጠችም ገምቼ ነበርሰው ትንሽ እረገብ ሲል በር አንኳኳና እከፍትልሀለሁ እናቴ ግን እንዴት ናት በጣም እያለቀሰች ነው እንዴ አለችው።

መልስ ሳይሰጣት ስልኩን ዘጋው።

ምን እንደተፈጠረ ጠየኳት።

ሰፈር ውስጥ ልእልት ጠፋች ተብሎ ሁሉም ሰው እየተጯጯኸ ነው አለችኝ።

ገናኮ ነው ምንድነው እንደዚህ ሚያካብዱት አልኳት፡፡ ተናደደች ማታ በክብር መኝታ ቤቴ ገብቼ የተኛሁት ልጅ ጠዋት ሲነሱ ሲያጡኝ እንዴት አይጨንቃቸው እእ የት ሄድኩ ሳልል ድንገት ጥፍት ስል ዝም ብለው መቀመጥ ነበረባቸው ሁሉም ሰውኮ አንተን አይደለም ለኔ ሚጨነቅልኝ ሚያስብልኝ ሰው አለ ገባህ እንዳንተ ሲያዩኝ ሚፀየፉኝ በውሸት ሚሸነግሉኝ በሴትነቴ የሚጠቀሙ ሰዎች አደሉም ዙሪያዬን የከበቡት። ቤት ውስጥ ምን እንደሚጠብቀኝ እያወኩ እንኳን ተሸፋፍኜ የተኛሁት አይንህን ለማየት ስላፈርኩና ማታ የነገርኩሽ በሙሉ ውሸት ነው የምትለዋን ቃል ላለመስማት ነው።

ባህራን ሴት ልጅ ላይ ሁሉም ነገር ከባድ ነው አንተ ዛሬ ከኔጋ አደርክ አደል ነገ የትም ቦታ ብትሄድ ከሴትጋ አደርክ አላደርክ ማንም አያቅም እኔ ግን ሴት ነኝ እድሜ ልኬን ጠብቄው የቆየሁትን ክብሬን አጣሁት በቃ አይመለስም አይታደስም በቃ ሄደ አለች።ልእልት በዛ ልክ ፊቷ ሊቀየር እንደሚችል አስቤው አላቅም ስብራቷ አይኗ ላይ በግልፅ ይታያል ህመሟን ፊቷ ይናገራል። በሰአቱ ወንድነቴን ጠላሁት ለምን እንደዛ አደረኩ ከየት ያመጣሁት ፀባይ ነው እኔጃ እናቴን ይሄን ብታይ የሚለው ነገር በራሱ አንገቴን አስደፋኝ። ከኔ ቤት ወጥታ እናትና አባቷ ቤት እንዴት ብላ ተመልሳ እንደምገባ ማሰብ ከበደኝ ምን ምክንያት እንደምንሰጣቸው አናቅም ወይ ከቤት ያባርሯትና ህይወቷ ገሀነም ይሆናል ወይ ቤት ውስጥ አስቀምጠው እስረኛ ያደርጓታል እኔጃ....ዝም ብዬ ቁጭ አልኩና መፍትሄ ማሰብ ጀመርኩ ወዲያው በሩ ተንኳኳ እንደ እብድ

.እሮጬ ከፈትኩት እዮብ ነው።

እዮብ በባህሪው ሲናደድ አይኑ ይፈጥና ሰወነቱ ይንቀጠቀጣል።

በሩን በፍጥነት ዘግቶ ልእልትስ ልእልትስ አለኝ። ወደውስጥ ገብቶ ልእልትን አያት ሶፋ ላይ ቁጭ ብላ ስቅስቅ ብላ ታለቅሳለች።

ካጎነበሰችበት ቀና አድርጎ ፊቷን ተመለከተው ምን እንደተፈጠረ ሁለታችንንም ጠየቀን ዝም አልን ንዴቱ ከመጠን በላይ ሲሆን እኔን በቦክስ መታኝና ያደረካትን ነገር ንገረኝ አለኝ፡፡

ሲመታኝ ትንሽ ቀለል አለኝ ወደቀልቤ ተመለስኩ ነገር ማሰብ ያለብኝና የሌለብኝን ነገር መለየት አቅቶኝ ነበር።

ልእልት ደንግጣ ተነስታ የተፈጠረውን ነገረችው አብረን እንዳደርንም ጭምር።

እዮብ ቁጭ አለ ሳቁም እንባውም እኩል መጡበት። አንዴ እኔን አንዴ እሷን እያየ ሁለት አይናፈር መሳይሾካኮች አለን።

ልእልት አንገቷን ደፍታ መልስ ሳትሰጠው ቀረች።

እኔም ብሆን ፀጥ ብዬ አይን አይኑን ነው ማየው። እዮብ ወደ መፍትሄው እንግባ በቃ ልእልት ዝም ብለሽ ወደቤትሽ ግቢ እኛ በጀርባ በኩል በአጥርእናዘልልሽና በሌላ መንገድ ቀይረሽ ትገቢያለሽ ስልክሽን እዚሁ ትተሽው ሂጂ ፊትሽ እንደተደበደበ ሰው ስለሚመስል በቃ ሌሊት ምን እንደተፈጠረ አላቅም ወስደውኝ ነው በይ አላትና በጀርባ በኩል

🔻ክፍል  2️⃣5️⃣ ነገ ማታ2️⃣🟰3️⃣0️⃣  ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀
 
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
💔  @MELKAM_LBOCH13 💔

➖የዩቲዩ ገፃችን➖
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction33


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ

                        ክፍል  
2️⃣3️⃣

ልእልት ገና ስታየኝ ግን በሰላም ነው አንተጋ መጥቼ እንደማድር ነግሬህ ትተኸኝ ተወጣለህ ሌሊቱን ሙሉኮ ብርድ ላይ ቁጭ ብዬ ያንተን መምጫ ስጠብቅ ነበር ትንሽ እንኳን አላሳዝንህም ደሞስ በር እንደዚህ ምታንኳኳው ጎረቤት ቢሰማህስ እያለች በነገር ታጦዘኝ ጀመር እኔ አይኔን ከከንፈሯ ላይ ሳላነሳ አዳመጥኳት በሩን ዘግታ ወደውስጥ ስትገባ ተከተልኳት ቤት ውስጥ ምግብ አዘገጃጅታ ቡና አቀራርባ እናቴ እያለች የነበረውን ድባብ አምጥታዋለች።

ከዚህ በላይ አልጨቅጭቅህ ደና ደር ብላ ወደማዬ ክላስ ልትገባ ስትል እጇን ያዝኳት።
ደነገጠች፡፡ ባህራን ምን እያደረክ ነው አለችኝ፡፡

እስከዛሬ ስሜቴን ደብቄ ነው የቆየሁት እንጂ እኔ ካንቺ ፍቅር ከያዘኝ ቆይቷል አውቄ ነው ማናድድሽ ማስቀይምሽ እንጂ አፈቅርሻለሀ እናቴ ትክክለኛ ሴት ነው የመረጠችልኝ አልኳት፡፡

እንባ ተናነቃት ባልራን አትዋሸኝ ስትዋሽ አይቼህ አላቅምኮ ዛሬ ምን ሆነህ ነው አለችኝ። አልዋሸሁሽም ልእልቴ በቃ ውልጅልኝ የእናቴን ምትክቆንጆ ሴት ልጅ ውለጅልኝ አልኳት።

ስለሰርኩ እየቀባጠርኩ እንደሆነ ነግራኝ ወደመኝታ ቤት ገባች በሩን ሳትዘጋው ተከትያት ገባሁ።

እንዳቆም ነገረችኝ እኔ መስሚያዬ ጥጥ ነው በቃ ድርቅ አልኩባት በዛ ብትለኝ በዚህ ከአቋሜ ዝንፍ አልል አልኩ ቃላቶቹ ከየት ከየት እንደመጡልኝ አላቅም ግን ብዙ እንደለፈለፍኩ አስታውሳለሁ።

እሷ ግራ ተጋብታ ቆማ ስታየኝ ከንፈሯን ግጥም አድርጌ ሳምኳት ሰወነቷ መንቀጥቀጥ ጀመረ
እኔ እጇን እያሻሸሁ በስሜት ደጋግሜ ሳምኳት። በመሀል አቁም ባህራን ሰክረህ እንዳትሳሳት ሴት ልጀኮ ነኝ አንዴ ክብሬን ካጣሁ መመለሻ የለውም እኔ እራሴን የመቆጣጠር ህይል እራሱ የለኝም ሰወሳቴ ደነዘዘኮ ባህራን በእቴቴ ይዤሀለሁ አቁም በቃ አለችኝ።

እኔ ላዳምጣት ፍቃደኛ አደለሁም።

እኔ እንድቀየር ፍቃደኛ አደለሽም ተለውጬ ካንቺና ከልጃችንጋ በፊት ምኖረውን አይነት ህይወት መኖርነው ምፈልገው አልኳት።

ዝም አለች።

እኔ በመጠጥ ያጣሁትን ሀይል እሷ በኔ ንግግሮች ኋይሏን አጣች።

ዝም ሳነሳት ዝም ሳስቀምጣት ዝም በቃ ዝም ብቻ ሆነ እኔ ያንን ነገር ተጠቀምኩበት በቀስታ እየሳምኳት ልብሷን ማውለቅ ጀመርኩ እንቢ አላለችኝም ስስማት መልሳ አትስመኝም ግን ደሞ እንዳልስማት አትከለክለኝም ብቻ በቃ ከብዙ ነገርቡሀላ አብረን አደረን የእናቴ አልጋ ልብስና አንሶላ በደም ተበላሸ

ጠዋት ቀድሜ ነቃሁ ቢያንስ አምስት ወይ ስድስት ሰአት ይሆናል፡፡

ልእልት ፊቷን አዙራ ተኝታለች። ሳያት አላመንኩም የልብ ምቴ ተደበላለቀ በሚያስደነግጥ ፍጥነት መምታት ጀመረ፡፡

በህልሜ እንዲሆን ብቻ ፈጣሪዬን ለመንኩት ግን አልነበረም ልእልት የእወነት እራቁታን ከጎኔ ተኝታ

በሰአቱ የነበረውን ነገር አሁን ማብራራት የፈሰሰን ውሀ እንደማፈስ ያህል በጣም ይከብደኛል።

ፊቴን አዙሬ ከአልጋዬ ወረድኩ።

ከክፍሉ ወጣሁ፡፡ ልእልት ከተኛችበት ሳትንቀሳቀስ ዝም አለችኝ ተጣጥቤ ልብሴን ቀየርኩና ለማጨስ ወደውጭወጣሁ የብዙ ሰዎች ድምፅ ይሰማኛል የሆነ ነገርእንደተፈጠረ ገብቶኛል ግን ነገሩ ምን እንደሆነ አልገባኝም።

ወደ ውስጥ ተመልሼ ገባሁና ልእልትን ቀሰቀስኳት አልነሳም አለች፡፡ ድምጿን አጥፍታ ፀጥጥጥጥ ስትል ጨነቀኝ የሆነ የሆነ ሰአት ሞታም መሰለኝ። ልእልት ተነሺ የሆነ ነገር ተፈጥሯል ሰፈር ውስጥ አልኳት ፀጥ አለችኝ። የለበሰችውን ብርድ ልብስ ገፈፍኳት ፊቷን በእጇ ሸፈነችው። አውቃ ዝም እንዳለችኝ ሲገባኝ ይበልጥ ተናደድኩ።

ዝም ብዬ በሩ ላይ ቆሜ ተመለከትኳት በፈጠረህ በቃ አትየኝ አለች።

እጇን ካይኗ ላይ ስታነሳው አብጧል። አይኗ ቀልቶ አብጦ አይታይም ብል ማጋነን አይሆንብኝም።

ወይኔ ምናልባት ለመጀመሪያ ጊዜ sex ሲደረግ እንደዚህ ይሆን እንዴ ሚያደርገው ምንድነው የተፈጠረው ታመመች እንዴ በቃ ግራ ገባኝ።

ፊቷን በደንብ አየሁት መልኳ ጥፍት ብሏል ፊቷ ሁላ የተቦጫጨረ ነው ሚመስለው።

ሌሊት እኔ በተኛሁበት የተፈጠረ ነገር ያለ መሰለኝ ምን እንደሆነች ደጋግሜ ጠየኳት ምንም አልሆንኩም አንዴ ውጣልኝና ልብሴን ልቀያይርአለች።

ወጣሁላት ውጭ ያለውን ግርግር ለማጣራት

ወጣሁና በሩ ላይ ከውስጥ ሆኜ ቆምኩ ግር ግርነገር ነው የሚያወሩት አይሰማኝም። ሲጨንቀኝ ተመልሼ ገባሁ ልእልት ልብሷን ለብሳ ከመኝታ ቤት ወጣች አይኔን አታየኝም መሬት መሬት እያየች እኔን ማየት አቆመች

🔻ክፍል  2️⃣4️⃣ ነገ ማታ2️⃣🟰3️⃣0️⃣  ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀
 
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
💔  @MELKAM_LBOCH13 💔

➖የዩቲዩ ገፃችን➖
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction33


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ

                        ክፍል  
2️⃣2️⃣

ሳንገናኝ ከዋልን ። ከእፉ የሷ ስም አይጠፋም ሳልፈልግ ስለሷ እንዳስብ ያደርገኛል። እሷ እያየችው ማጨስ አይፈልግም እሷ ፊት መቃም መጠጣት ነውር መስሎ ነው ሚታየው።

ከአስር አመት ቡሀላ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊቱን በመስታወት ያየው ልእልትን ከተዋወቃት ቡሀላ ነው። የመጀመሪያ ቀን መስታወት ፊት ቆሞ እራሱን አየና አየህ አደል ባህራን ጊዜ ሲጥልህ ሁሉም ይተውሀል መልክህ ግርማ ሞገስህ ካንተ ይሸሻል። ከአስር አመት በፊት እኔን ብታየኝ ትገረም ነበርቁመት ብትል መልክ, አነጋገር, ስርአት, በቃ ምን ልበልህ ሁሉንም አሟልቶ የሰጠኝ ሰው ነበርኩ ከዛ ቤተሰቦቼ ትተወኝ ሲሞቱ ሁሉም ከኔ ሸሹ።

ልእልትን እንዳፈቅራት ያደረገኝኮ ይሄ ነው ያንን ሴጣን ሚቀናበትን መልክ ይዛ ከኛጋ ስትሄድ አይሞቃት አይበርዳት ውይ አሁን እሷም ከኔ ሚስት እኩል ሴት ትባላለች አደል አለኝ።

አትሳሳት የሴት ንፁህ የለም ልእልትም ቢሆን እያስመሰለች ሊሆን ይችላል አልኩት።
ህይወት ከሰጠችኝ ተሰጥኦ ውስጥ አንዱ የሰዎችን ፊት አይቶ ውስጣቸውን ማንበብ ነው ልእልት ከልቧ ሰው ናት አታስመስል አትዋሽ እራሷን ሆና ምትኖርሰው ናት አለኝ፡፡

ቀኑ እለት ሀሙስ የቀን ቅዱስ ነበር ከእዮብጋ ቤት ሄደን ቁጭ እንዳልን መጣሁ አንዴ ወጥቼ ልምጣ ብሎ ሄደ።

ልእልትና እኔ ብቻችንን ቁጭ ብለን መፋጠጥ ጀመርን ሲጨንቀኝ ተነስቼ ወጣሁና ማጨስ ጀመርኩ፡፡

ልእልት መጥታ ካጠገቤ ቁጭ አለች፡፡

ታቃለህ የሆነ ሰወን ስትወድ ግን ከነድክመቱ ነዋ። በፊትኮ እኔ መንገድ ላይ ሲጋራ ሲሸተኝ ሊያስታውከኝ ነው ሚደርሰው አለችኝ።

በንዴትና በቁጣ ተሞልቼ አሁን አንተን ስለምወድህ የሲጋራውንም ሽታ ወደድኩት ልትይኝ ነው አልኳት፡፡

ሳይሆን ካንተ አጠገብ ቁጭ ብዬ ስታጨስ ምንም አይመስለኝም ልልህ ነው ምን አናደደህ አለችኝ።

እንደማትወደኝና እያስመሰለች እንደሆነ እንደማቅ አስረግጬ ነግሪያት ሲጋራውን ፊት ለፊቷ መሬት ላይወርውሬው ወደውስጥ ገባሁ።

ብቻዬን ስሆን የምይዘው የምጨብጠውን ነው ማጣው ለማበድ ትንሽ ነው ሚቀረኝ ልእልት ውጭቁጭ ብላ ትንሽ ስትቆይ ቤቱ ሊበላኝ ደረሰ ጨነቀኝ ፍርሀት ውስጤን ተናነቀው የማብድ ሁላ መሰለኝ ተነስቼ ወጣሁ ጉልበቷ ላይ ድፍት ብላ ስቅስቅ ብላ ナへゆうべド:

ይቅርታ በማለት ፈንታ አጠገቧ ቁጭ አልኩ።

ሁለታችንም ዝም ተባብለን ቆየን። መጣሁ በቃ ዛሬ እዚህ ነው ማድረው አለችኝ።

እሺ እንዳትቆይ ብዬ አስጠንቅቂያት ወጥታ ወደቤቷ ሄደች።

እስከማታ ጠበኳት አትመጣም እዮብም እሷም ድራሻቸው ሲጠፋ ጨንቆኝ ከቤት ወጣሁ።

እየመሸ ስለነበር ወዴት እንደምሄድ አላቅምግን ወደስራ ቦታዬ መንገዴን አቀናሁ።

ዝም ብዬ በዝግታ እጓዛለሁ።

ድንገት ቀና ስል ግን ፋኖስን አየኋት አረጅም ነጭቀሚስ ለብሳለች ከላይዋ ላይ ነጠላዋን ጣል አድርጋ አስፋልቱ ግዛቷ የሆነ ይመስል ትንጎራደዳለች።

ከጎኗ ባሏም እረጅም ነጠላ ለብሶ ልጁን እቅፍ አድርጎ ጎን ለጎን እየተሳሳቁ ሲሄዱ አየኋቸው ኮፍያዬን ድፍት አደረኩና ባጠገባቸው አልፌ ሄድኩ። ካለፍኳቸው ቡሀላ ግን እግርና እግሬ ተያያዘ ወደፊት መሄድ አልቻልኩም ፊቴን ወደነሱ አዙሬ ቆምኩኝ። ፋኖስ ከልቧ ፈገግ ስትል አየኋት ።

እኔ ከልቤ ፈገግ ያልኩባቸው ቀናቶች ናፈቁኝ ህይወት ውስጥ እንደፋኖስ እያበራች ገብታ የነበረችኝን ብርሀን አጥፍታ ነው የወጣችው።

ነገሩን በሙሉ ትቼ እነሱን መከተል ጀመርኩ፡፡
ለምን እንደሆነ አላቅም የልጁ አይን አሳሳኝ ከሩቅ አይቼው አልጠግብ አልኩት፡፡

የሆነ ሰአት ግን እኔ በሀሳብ ሄጄ ቀና ስል ከአይኔ ተሰወሩብኝ።

እንደ እብድ አደረገኝ ቁጭ ብዬ አይን አይናቸወን ማየት ብቻ ስለፈለኩ ከአይኔ ሳጣቸው ልቤ ስንጥቅ አለ፡፡

ወደ ሁሉም አቅጣጫ ተመለከትኩ የሉም ዞር ስል ያገኘሁት አረቄ ቤት ገባሁ ይቀዳል እጠጣለሁ ይቀዳል እጠጣለሁ ከዛ በዘለለ ምን እየተካሄደ እንዳለ አልገባ አለኝ።

በጣም እየመሸ ሲመጣ ምከፍለው ብር ስሌለኝ ጨነቀኝ ኪሴ ገባሁ መቶ ብር ነው ያለኝ።

ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላቅም፡፡ አረቄ ምትቀዳዋን ልጅ ጠራኋት ብር የለኝም ግን የለበስኩትን ጃኬት ልስጥሽ አልኳት። ያንተ ጃኬት ለኔ ምግብ ይሆነኛል ብለህ ነው ጃኬትህ ውድ የመሰለህ አንተ ስለለበስከው ነው እኔ ለመሸጥ ገበያ ላይ ሳወጣው ዋጋውን ያጣል

አይገርምም ውድ ነገር ውድ ሚሆነው ትክክለኛ ቦታወን ሲያገኝ ነው።

እንደምንም ለምሜ ሰጥቻት ወጣሁ ሰው ንፋስ ሲነካው ስካሩ ይለቀዋል የኔ ስካር ደሞ ልክ ንፋስ ሲነካኝ ይብሳል በእግሬ ሰፈር ደረስኩ በሩን በሀይል አንኳኳሁት ልእልት ከመቼው እንደከፈችው ባላቅም ከፍታ አስገባችኝ።


🔻ክፍል  2️⃣3️⃣ ነገ ማታ2️⃣🟰3️⃣0️⃣  ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀
 
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
💔  @MELKAM_LBOCH13 💔

➖የዩቲዩ ገፃችን➖
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction33


ቤተሰብ ከታላቅ ይቅርታ ጋር ዛሬ ለመልቀቅ ስላልተመቸን ነገ በዛ አርገን እንለቃለን🙏


በቃ አሁን ላይኮ ሁሉም እረፍዷል አብቅቷል ህይወት ለኔ በሯን በዘጋችብኝ ሰአት የሷ መምጣት ልክ አደለም ለዛውም አንተን አፍቅራ ስትከተልህ እኔ እሷን መተዋወቄ ልክ አደለም፡፡ እንዳዲስ እንድኖር እያጓጓችኝ ነው፡፡
ዝም ብዬ በማንኛውም ሰአት እሷን ማየት እሷ ወዳለችበት መሄድ ነው ምፈልገው አለኝ። እኔ እንደዛ ሲለኝ ውስጤ ላይ የነበረው ስሜት ምን እንደሆነ ግራ ገባኝ ብቻ ዝም ብዬ ባፌ መለፍለፍ ጀመርኩ፡፡ አረፈደምኮ አሁንም አብራችሁ መኖር ትትችላላችሁ፡፡

ይሄኔኮ እሷም ትወድህ ይሆናል በቃ እሱን ሊያፅናና ይችላል የምላቸውን ቃላቶች መደርደር ጀመርኩ፡፡ እዮብ ግን በአባቱ እየማለ መቼም ቢሆን ልእልትን የራሱ እንደማያደርጋት ነገረኝ፡፡ ከዛ ሁለታችንም መሀል ፀጥታ ሰፈነና ዝም ብለን እየተጓዝን የተከራየንበት ሰፈር ስንደርስ ዝም ብለን ገብተን ተኛን። የእናቴ ሙት አመት አለፈ። ሙት አመቷ ቀን ሁሉም ከንፈሩን እየመጠጠ መቃብሯን ከበው ቆመው ነበር ።እኔ ማንም ሰው ሳያየኝ ከሩቅ አይቻቸው ተመለስኩ።

ልክ በነጋታው ግን ሁሉም ያነሱት ሀሳብ ስለቤቱ ነበር ሁሉም ነገር በልእልት ስም እንደሆነ ሲያውቁ ሊገሏት ምንም አልቀራቸውም ሙሉ እንደጠላት ነበር ያዩዋት ቤቱን ለመውረስ ብላ ልጁን የሆነ ነገር አድርጋው ነው እንጂ በህይወት ቢኖር ኖሮ እኛ እናየው ነበር ይጣራልን ወንጀለኛ ነች ብለው ከሰሷት።

እኔ በአካል ፍርድ ቤት ቀርቤ ወድጄና ፈቅጄ ይሄንን እንዳደረኩ ግልፅ መረጃ ሰጠሁ፡፡
አክስቶቼ ከአመት ቡሀላ ያ የሚያቁት መልኬ ሳቄ ጠፍቶ ሲያዩኝ ምነው ከሳህ ምነው ጠቆርክ አላሉኝም
የሁሉም ጥያቄ ተመሳሳይ ነበር ለማንም ባዳ አሳልፈህ ከምትሰጠው እኛ እህቶቿ ብንጠቀምበት አይሻልም ነበር ያሉኝ። ላያቸውም ስላልፈለኩ ትቻቸው ሄድኩ፡፡
እኔና እዮብ አንዴ ቤት አንዴ የኪራዩ ቤት እያደርን ጊዜያቶች መሄድ ጀመሩ፡፡
ልእልትም ብትሆን የመመረቂያ ጊዜዋ ተቃርቧል።

እዮብ እንዴት እንደምናስመርቃት እያሰበ ብቻውን ይደሳሰታል። ሁኔታውን ሳየው ግራ ይገባኛልም ያሳዝነኛልም፡፡
በአጋጣሚ ሌላ ቦታ ሄደን ከልእልትጋ
ሳንገናኝ ከዋልን ። ከአፉ የሷ ስም አይጠፋም ሳልፈልግ ስለሷ እንዳስብ ያደርገኛል።

እሷ እያየችው ማጨስ አይፈልግም እሷ ፊት መቃም መጠጣት ነውር መስሎ ነው ሚታየው።
ከአስር አመት ቡሀላ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊቱን በመስታወት ያየው ልእልትን ከተዋወቃት ቡሀላ ነው።

የመጀመሪያ ቀን መስታወት ፊት ቆሞ እራሱን አየና አየህ አደል ባህራን ጊዜ ሲጥልህ ሁሉም ይተውሀል መልክህ...

🔻ክፍል  2️⃣2️⃣ ነገ ማታ2️⃣🟰3️⃣0️⃣  ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀
 
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
💔  @MELKAM_LBOCH13 💔

➖የዩቲዩ ገፃችን➖
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction33


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ

                        ክፍል  
2️⃣1️⃣

ይውሰዱት አልኳት።
ሁለቱም ተናደዱብኝ ልእልት ተስፋ በመቁረጥ አይን ተመለከተችኝ፡፡
ተነስቼ ልወጣ ስል እዮብ አስቆመኝና እንግዳኮ ነኝ ለቤቱ ትተኸኝ ልትወጣ ነው እንዴ ብሎ አስቆመኝ፡፡

ተመልሼ ቁጭ አልቁ ስለቤቱ እርእስ ማንሳት አልፈለኩም እነሱም ሁኔታዬ ስለገባቸው ዝምታን መረጡ፡፡
ቀኑ እየመሸ ሲሄድ ልእልት ቤት ደርሼ ሸውጄ እወጣለሁ ካልሆነ እናቴ ትገለኛለች ብላ ተነስታ ወጣች፡፡
ትንሽ ቆይቶ በር ተንኳኳ ተመልሳ እንደመጣች አስበን እዮብ በር ከፈተ ግን እሷ አልነበረችም ከሱቅ ሳጥን ቢራ የያዘ ሰው በር ላይ ቆማል እኔ ደረጃው ላይ ቆሜ ስለነበር እዮብ ግራ ገብቶት ማነው ያዘዘው ማእዶት ናት የላከችው እያለ ነው አለኝ።ግራ ገብቶኝ እኔጃ ማናት ማእዶት አልኩት ሰውዬው ቀበል አድርጎ እዚህ ጎረቤታችሁ ናታ ቆንጅዬዋ ድምፕል ያላት ፀጉረ ረጅሟ ልጅ አለ፡፡

ስለማን እያወራ እንደሆነ ስለገባን ተቀብለነው ወደውስጥ አስገባነው ልእልት እስክትመጣ እዮብ እኔ አልጋ ላይ የነበረውን ፍራሽ ሳሎን አነጣጠፈና ና ዱቅ እንበል አለኝ፡፡ ለአይን ያዝ ያዝ ሲያደረግ ልእልት በድጋሜ በር አንኳኳች ከፍተን አስገባናት እዮቤ ገና ከበር አንቺ ማእዶት ነው እንዴ ስምሽ አላት። አዎ እኔኮ ብዙ ስም ነው ያለኝ ይሄኔ በስሜ ልክ ብር ቢኖረኝ እኔ ነበርኩ ሀብታም ብላ እየቀላለደች ፍራሹ ላይ ቁጭ አለች።

እስክመጣ እንድትጠጡኮ ነው ቀድሜ መጠጡን የላኩላችሁ አጠጡም እንዴ አለችን።
እዮብ አብራን ከጠጣች ብለን እየጠበቅናት እንደሆነ ነገራት፡፡

ታውቁ የለ እንደማልጠጣ እናንተ ጠጡ አለችን ተጀመረ ሞቅታው ሲጀምርን እርስ በርስ መተራረብና ከጣራ በላይ መሳቁን ተያያዝነው፡፡ ልእልት ሁኔታችን ግራ ገብቷት ድምፅ እንድንቀንስ አጥብቃ እየጠየቀችን እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡

ልክ መጠጡ ድንዝዝ ማድረጉን ሲቀጥል ልእልት እንድናቆም ነገረችን እኔ አሻፈረኝ አልኩኝ የእናቴን ፎቶ እያየሁ ድፍት ብዬ እዬዬ ማለት ጀመርኩ ልእልትና እዮብ እንደምንም አስነስተው አስገብተው አስተኙኝ።
ጠዋት አረፋፍጄ ተነሳሁ እዮብ ብቻውን ነው ያለው ፡፡ቁርስ ላቅርብ ተነስና ታጠብ አለኝ።

ተጣጥቤ ቁርስ እየበላን እዮብ አንድ ሀሳብ አቀረበልኝ አሁን አንተ ለዚህ ቤት በብርቱ አላማ የመታገል ሀሳብ ከሌለለህ ለምን ቤቱን በልእልት ስም አታረገውም ቢያንስ ዘመድ ጎረቤት ፊቱን ሲያዞርብህ አንድ ያልተወችህ ሰው እሷ ናት ።

እናትህም ለሷ ነው አደራ የሰጠችህ።
እንደምታያት ጎበዝና ጠንካራ ልጅ ናት በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ አትተውህም ስለዚህ አሁኑኑ ፕሮሰሱን እንጀምርና በሷ ስም አድርግላት አለኝ።

እሺ ማለትም መቃወምም አልፈለኩም።
ዝም አልኩት፡፡እዮብ ቁጭ አድርጎ ብዙ ነገሮችን ነገረኝ መከረኝ ። ያው በሰአቱ ለምንም ነገር ፍላጎት ስላልነበረኝ ዝም ብዬ እሺ እሺ አልኩት።

እስከ ምሳ ሰአት አንዴ ስንጠጣ አንዴ ስናጨስ ከቤት ግቢ ውስጥ ከግቢ እቤት ስንመላለስ ምሳ ሰአት ደረሰ። ልእልት መጣች ትምህርት ቤት እንደሚሄድ ሰው ለባብሳ
ነበር፡፡እዮብ እንዳያት ሄዶ ጥምጥም አለባት።
እኔ ዝም ብዬ ቁጭ አልኩ።
አጠገቤ መጥታ ቁጭ አለችና ዛሬ እቴቴ መቃብርጋ አትሄድም አደል ይኸው ቤቱም ምኑም የሷ ፎቶ ስለሆነ እዚህ እሷን ማየት ትችላለህ ።
ስትወጣ ስትገባ እያዩህ እንዳይረብሹህ ብዬ ነው አለችኝ፡፡ በሀሳቧ ተስማማሁ እዮብ ገና ከመቀመጧ ቤቱን ባንቺ ስም ሊያደርግልሽ ነው አላት።

ደነገጠች አረ አይሆንም በስማም እኔ አልፈልግም ይሄ ቤትኮ እቴቴ ነፍሷን ያጣችበት ቤት ነው ለሱ ደሞ ምን ማለት እንደሆነ ያቀዋል አለች።
እኔ ሀሳብ አልሰጥም ወሳኝም ፈራጅም ሁለቱ ሆነው ቁጭ አሉ።እዮብ ከነምክንያቱ እትትት እያለ ያስረዳት ጀመር።

በመሀል እዮብ ለልእልት በዛውምኮ ይሄ ቤት በስምሽ ከሆነ መቼም ቢሆን ተለያይታችሁ አትለያዩም አናቱን ባሰ ቁጥር ቤቱን ያስባል ቤቱን ባሰበ ቁጥር ደሞ አንቺን ያስብሻል አላት። ትንሽ አንገራገረችና እሺ አለች።
የዛን ቀን ልእልትና እዮብ ባንድ ነጠላ ካላስቀደስን እያሉ አብረው ቤት ሲያፀዱ አብረው ምግብ ሲሰሩ ቀኑ አለፈ። በነጋታው ልእልት ከቤቷ እስክትመጣ ጠብቀን አብረን ወደሚመለከተው አካል ሄድን ።

የሚያስፈልገውን ሁሉንም ፕሮሰስ ጠየቅን ነገሩን ያን ያህል ከባድ አልነበረም ፕሮሰሱን ጀመርን ሙሉ ያለኝ ነገር የቀረኝ አንድ ሀብት ቤታችንን በልእልት ስም አደረግነው አክስቶቼ ቤቱን ሊጠይቁ ሲመጡ በሷ ስም እንደሆነ ሲያውቁ የሚሰማቸውን ስሜት እያሰብኩ ደስታ ተሰምቶኝ ነበር።

ብቻ በዛን ሰአት ልክ ቤቱን በስሟ አድርገን ስንመለስ ፏ ብዬ ለብሼ ፀጉሬን ተስተካክዬ ነበር ምክንያቱም እዛ ቦታ ላይ ከንግግር በላይ የለበስነው ልብስ ዋጋ አለው፡፡

መንገድ ላይ ልእልትና እዮብ ተያይዘው እየሄዱ እኔ ከኋላቸው ብቻዬን እጄን ኪሴ ከትቼ እየተራመድኩ እነሱን እየተመለከትኩ ነበር ሁሉም ሰው አይኑ እነሱ ላይ ነው ሲመስለኝ እዮብና እሶ ፍቅረኛሞች መስለዋቸው ሳይሆን
አይቀርም። ቤት ገባን አሪፍ ጊዜ እንዲያሳልፉ ነግሪያቸው መኝታ ቤቴ ገብቼ ቆለፍኩና ጋደም አልኩ።
ጭንቅላቴ እረፍት አጣ ልእልት የምር ምትታመን ሰው ናት ከፋኖስ ቡሀላ መመማር መቻል ነበረብኝ እንዴት በድጋሜ......

እንዴት በድጋሜ ሰው አምናለሁ እያል መብሰልሰል ጀመርኩ   ትንሽ ቆይታ ልእልት መጥታ በር አንኳኳች እራት እንብላና ወደቤቴ ልሂድ አለች፡፡
እናንተ ብሉና ሂጂ እኔ አልመጣም አልኳት፡፡
በር ላይ ቆማ ለረጅም ሰአት ከለመነችኝ ቡሀላ እሺ ደና ደር ብላኝ ሄደች።

ምሽቱን ሙሉ ብቻዬን ስነሳ ስቀመጥ ዝም ብዬ ክፍሉ ውስጥ ስንጎራደድ አራት ሰአት አካባቢ ሆነ የዛኔ መተኛትም ማሰብም አልቻልኩም የማስበው ግራ ገባኝ ጭንቅላቴ ውስጥ ጭጭጭጭ የሚል ድምፅ ብቻ ይሰማኝ ጀመር።
ተነስቼ ከክፍሌ ወጣሁና ወደ እዮብጋ ሄድኩ ቤት ውስጥ የለም ዞር ዞር ብዬ አየሁትና ወደ ውጭ ወጣሁ ቀጥጥጥ ብሎ ቆሞ ሰማይ ሰማይ እያየ ፈገግ ይላል እግሩ ስር ቢያንስ አራት አምስት የተጨሰ ሲጋራ ተጥሏል።

አየሁትና አጠገቡ ሄጄ ምን እንደሆነ ጠየኩት።
ዝም ብሎ ፈገግ ብሎ እያየኝ ምንም አልሆንኩም አንተ ለምን መጣህ አለኝ። ቤት ስለጨነቀኝ ወክ እንድናደርግ ጠየኩት እሺ አለኝ ቤቱን እንኳን ሳንዘጋው የውጭውን በር ብቻ ቆልፈን ወጣን።

ሰፈሩ ጭር ብሏል እኛ ዝም ብለን መራመዳችንን ቀጥለናል ሁለታችንም ዝም ብለን እስከ አስፋልት ደረስን ወዴት እንሂድ ወደቀኝ ወንስ ወደግራ ተባብለን ወደቀኝ ጉዞ ጀመርን በመሀል እኔ ቅድም ለምን ነበር ብቻህን ፈገግ ስትል የነበረው አልኩት።
ልእልትን እያሰብኩ ነበር አለኝ።

በጥያቄ አይን እያየሁት ከምርህን ነው እሷን አስበ በጥያቄ አይን እያየሁት ከምርህን ነው እሷን አስበህ ፈገግ አልክ አልኩት፡፡ አዎ ፈጣሪ እንደማይወደኝ የገባኝ እሷን ከረፈደ ቡሀላ ባንተ በኩል አድርጎ ወደኔ ሲያመጣት ነው አለኝ፡፡ እንዴት????


ባለፈው አክስትህ መጥታ ነበር እና ሁሉንም የነገረችኝ እሷ ናት ከቻልክ ይሄ ቤት እቴቴ ላንተ የተወችልህ ትልቁ የህይወት አደራ ስለሆነ የሆነ መፍትሄ እንድትፈልግ ነው እንደኔ እንደኔ እንደምንም ብለህ ተመልሰህ እዚህ ቤት መኖር አለብህ አለችኝ

ይቀጥላል...


🔻ክፍል  2️⃣1️⃣ ነገ ማታ2️⃣🟰3️⃣0️⃣  ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀
 
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
💔  @MELKAM_LBOCH13 💔

➖የዩቲዩ ገፃችን➖
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction33

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

120 142

obunachilar
Kanal statistikasi
Kanalda mashhur

♾ነገ ማታ አንድ ምርጥ ታሪክ እንጀምራለን🚨
ፈገግ ስትይ ያየሽ ሰው አብሮ ፈገግ ይላል፣ ይጋባል፣ ልብ ይሰርቃል፣ አይንሽ የሚያወራ ይመስላል አንዳንዴ ምን እያልሽኝ እንደሆነ ሳስብ የውስጤን ያየሽ እ...
♾!መልካምነት!♾ ወደ ስራ ስሄድ አንድ የስልክ እንጨት ላይ የተለጠፈ ወረቀት አየሁኝ.. ____ ጽሁፉ እንዲህ ይላል "እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር ጠ...
      🔸🔸🔺🔺🔹🔸        ❤️ የፍቅር ጥግ ❤️ ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ ❤️ ፀሀፊ ✍️ ማኔ                         ክ...
      🔸🔸🔺🔺🔹🔸        ❤️ የፍቅር ጥግ ❤️ ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ ❤️ ፀሀፊ ✍️ ማኔ                         ክ...