ትዝብተ-በርናባስ🔎✍️ dan repost
ከመሬት መንቀጥቀጡ በኋላ...
----◉-----
ከበርናባስ በቀለ
አዲስ አበባና በአካባቢው የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የእኛንም ሰፈር በአንድ እግሩ አቁሞት ነበርና ሰው እየሮጠ ሲወጣ እኔና ቤቴም ከሕንጻው ወደ መሬት ስንወርድ ከለበስነው የምሽት (የቤት ውስጥ) ልብስና ከተማው ውስጥ ያሉትን ሌሎች ወዳጆች ጋር ለመደወል በእጃችን ከያዝነው አንድ ስልክ ውጭ ምንም ይዘን አልወጣንም።
ከሰፈሩ ሕዝብ ጋር በውጭ ስንገናኝም ማንም ምንም አልያዘም፤ ሁሉም ራሱን ብቻ ይዞ ደንብሮ ወጥቷል! ባዶ እጁን። ሁሉም ሰው በውጭ ባለ ሜዳ ተሰብሷል፤ ድሃ የለ፣ ሃብታም የለ! ባለ ሥልጣን የለ... ወዛደር የለ.. ሁሉም በምሽት ልብሱና በነጠላ ጫማው! ክልል የለ፣ ኦሮሞ የለ አማራ የለ...ካምባታ የለ... ጉራጌ..! ሁሉም ሰላም ወጣችሁ!? አራሷ ወጣች? ነፍሰ ጡሯስ? በቃ ሁሉም እኩል አልኳችሁ! እመኑኝ፤ ማንም ምንም ይዞ አልወጣም።
ሕይወት ይህችው ናት። በመጨረሻም የምታስመልጡት ራሳችሁንና ራሳችሁን ብቻ ነው። ያከማቻችሁት የእናንተ አይደለም፤ እጃችሁም ያለው እናንተን (ራሳችሁን) አይደለም። እናንተ ማለት ይዛችሁ የወጣችሁት ማንነታችሁ ነው።
በዚያ ሰዓት ዘር፣ ዝና.. ታዋቂነት እና አዋቂነት አይሠሩም። ሁሉም እኩል! አለኝ የምትለው በፍጻሜ የአንተ አይደለምና ይዘኸው መሸሸ የቻልኸው ራስህን (አንተነትህን) በትኩረት እይ! ትምክህትም አለኝ በምትለው አይሁን፤ ከደቂቃዎች በፊት የተፈጠረው ክስተት አለን የምትለው እንደማይከተልህ አስተውለሃልና!! ይኸው ነው።
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊