𝐑𝐄𝐒𝐌𝐈🦋༢࿔ྀ
አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ dan repost
ጥያቄ: —
ቁርኣን በሱራ 2:7 ላይ ያላመኑትን ሰዎች አይን ሸፍኖ፣ጆሮና ልብ ላይ አትሞ ለምንድ ነው በእኔ አላመናችሁም ብሎ የሚቀጣቸው? ይሄ ከኣምላክ የማይጥበቅ የፍትህ መዛባት ነው።
خَتَمَ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ وَعَلَىٰ سَمۡعِهِمۡۖ وَعَلَىٰٓ أَبۡصَٰرِهِمۡ غِشَٰوَةࣱۖ وَلَهُمۡ عَذَابٌ عَظِيمࣱ
አላህ በልቦቻቸው ላይ በመስሚያቸውም ላይ አትሞባቸዋል፤ በዓይኖቻቸውም ላይ መሸፈኛ አልለ፤ ለነሱም ታላቅ ቅጣት አላቸው፡፡
መልስ:—
1) በመጀመሪያ የአንቀፁ ሙሉ ሃሳብ ለማግኘት ከቁጥር 6 ጀምሮ መነበብ አለበት። ሰለዚህ " እነዚያ የካዱት ሰዎች ብታስፈራራቸውም ባታስፈራራቸውም በነርሱ ላይ እኩል ነው አያምኑም " ካለ በዃላ ነው ።እንደነዚህ አይነት ሰዎች በ"ክህደታቸው " ምክንያት ነው ይህ ቅጣት የሚጣልባቸው። [ቁርኣን 4:155]
2) አላህ ሱወ ምንግዜም ቅን የሆኑ ሰዎችን ያውቃል ይመራቸዋልም። ለሰው እንጂ ለአምላክ ይህ ቀላል ነገር ነው። ከኛ ውስጥ ማን መመራትን (ቅናቻን) እንደሚፈልግ። ማን መጥመምን እንደሚፈልግ አስቀድሞ ያውቃል። ከዚህም የተነሳ አይደለም ምድር ላይ አቆይቶን ፣ ዛሬ ፈጥሮን ዛሬውኑ ፍርድ ቢሰጥ ፍርዱ ፍትሃዊ ነው።
3) አምላክ የሰውን ልጅ ሁለት ምርጫ ሰጥቶ የፈለገውን እንዲመርጥ ከነጥቅሙና ጉዳቱ ግልፅ አድርጓል [ ቁርኣን 76:3 እኛ ወይ አመስጋኝ ወይም ከሓዲ ሲኾን መንገዱን መራነው፤ (ገለጽንለት) ] በዚህ ሒደት ውስጥ የነብያት ተልእኮ መልእክቱን ማደረስ ብቻ ነው። መመራት በአላህ ሱወ እጅ ያለ ጉዳይ ነው።እርሱ ቅኖቹን ዐዋቂ ነውና። [ቁርኣን 28:56 አንተ የወደድከውን ሰው ፈጽሞ አታቀናም፡፡ ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያቀናል እርሱም ቅኖቹን ዐዋቂ ነው]
4. ሰለዚህ ከላይ የተገለፁ ሰዎች [ ከሃዲዎች] ከክህደታቸው ከተመለሱ ወደ ቅኑ መንገድ ይመራሉ ምክንያቱም ። አላህ ሱወ ለባሮቹ ክህደትን አይሻምና።[ቁርኣን 49:7]
እንዲህማ ባይሆን ትላንት የሌላ እምነት ተከታይ የነበሩ ሰዎች በዚህ አንቀፅ እያሳበቡ ባልሰለሙ ነበር። ለእውነት ያደረጉት ጥረት ፍሬ እያፈራ በየግዜው ሰዎች ወደ እስልምና ይገባሉ።
ቁርኣን 8:38 ለነዚያ ለካዱት በላቸው፡- ቢከለከሉ ለእነሱ በእርግጥ ያለፈውን (ሥራ) ምሕረት ይደረግላቸዋል።