Development Bank of Ethiopia (DBE) dan repost
በደብረ ብርሃን ከተማ በ2.1 ቢሊዮን ብር ካፒታል የተገነቡ አምስት ፋብሪካዎች ተመረቁ።
- ሁለቱ ፋብሪካዎች በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፋይናንስ የተደረጉ ናቸው፡፡
አዲስ ወደ ስራ የገቡት ፋብሪካዎች ለ2ሺህ ስራ ፈላጊ ዜጎች የስራ እድል ተጠቃሚ እንደሚያደርጉም በምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ተገልጿል።
ወደ ምርት የገቡት ፋብሪካዎች የውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት የውጭ ምንዛሬን የሚያስቀሩ መሆናቸውም ነው የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የገፁት።
ሚንስትሩ አክለውም በእለቱ የተመረቁት ፋብሪካዎች ምርትን በማሳደግ የሀገር፣ የዞኑንና የከተማዋን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ይሆናሉም ነው ያሉት።
ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ 48 ፋብሪካዎች ወደ ስራ ማስገባት መቻሉንና በተያዘው ዓመት ደግሞ 17 ኢንዱስትሪዎች እንደሚመረቁ የገለፁት ደግሞ የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት ናቸው። ከንቲባው አክለውም ከዚህ በፊት ወደስራ በገቡት ፋብሪካዎች ለ8 ሺህ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር ተችሏልም ነው ያሉት።
120 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ፋብሪዎች በከተማው እንደሚገኙ የጠቆሙት አቶ በድሉ ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ ሲገቡ ለ112 ሺህ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር ይችላሉ ብለዋል።
11 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ያስመዘገቡ 17 ኢንዱስትሪዎችም በያዝነው አመት እንደሚመረቁ ጠቅሰዋል።
የካቲት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከተመረቁት አምስት ፋብሪካዎች መካከል ሁለቱ (ተሻለ አለባቸው የስፖንጅና ስፖንጅ ውጤቶች ማምረቻ እና በላይ ግዛው የዱቄት ማምረቻ ) በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የፋይናንስ አጋዥነት ወደ ምርት የገቡ ሲሆን፣ ባንኩ ባለፍት ዓመታት ወደ ምርት የገቡ በርካታ ፋብሪካዎችን ፋይናንስ ማድረጉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።