ቤተልሄም ታፈሰ ተወልጄ አድጌበታለሁ የምትለው የኦሮሞ ሕዝብ የነፃነት ተግል የሚያቅለሸልሻት መሆኑን መግለፅ ከጀመረች ውላ አድራለች። በፊትም ቢሆን የኦሮሞነት ስሜት ይኑራት አይኑራት ባይታወቅም ባደገችበት የአርሲ አካባቢ እድል አግኝተው ት/ቤት ገብተው ይማሩ የነበሩ እኩዮቿን የአርሲ ልጆች ትፀየፍና ታንቋሽሻቸው እንደነበር ከጥቂት አመታት በፊት ከተፃፈ ጽሁፍ ማንበቤን አስታውሳለሁ።
ቤተልሄም አብሯት ያደገው ይህ የትምክህት ልክፍት አልለቃት ብሎ ሽህዎች የተሰውለትንና ዛሬም እየተሰውለት ያለውን የኦሮሞን የነፃነት ትግል ስታንቋሽሽና "አላማ ቢስና የሚፈልገውን የማያውቅ" አድርጋ ልትስለው ስትጋጋጥ ትታያለች። ይህም የአቢይኒዝምን ክኒና በወዳጇዋ በሌንጮ በኩል ተልኮላት መዋጧን ያሳብቅባታል።
ከሁሉ በላይ ግን "ከ50 አመት በላይ የኦሮሞ ትግልን መርቼያለሁ፣ የትግሉንም አይዲዎሎጂ ነድፌ፣ በዝያ የተመራ ትግል ኦሮሚያን አዋልዶ አፋን ኦሮሞ የኦሮሚያ የሥራ ቋንቋ እንዲሆን አስችዬያለሁ" የሚልን ግለሰብ "የትግሉን አላማ ስጠይቀው ምንም አንደማያወቅ ነግሮኛል" ብላ ስትገልፅ የትግሉን አላማ ቢስነት ሳይሆን የግለሰቡን የእድሜ ልክ አላማ ቢስነትና ከንቱነት ያጋለጠችበት መሆኑን አንኳን ማወቅ ያልቻለች ግልብ መሆኗን አሳይታለች። የሄደችበት ርቀት ለትግሉ ያላትን ጥላቻ የገለፀችበት ብቻ ሳይሆን መጽሐፉን እንድትጽፍ ያስቻላትንና ከገባበት አዘቅትና ቅሌት ለማውጣት የታተረችለትን ወዳጇን ይሰራ የነበረውን የማያውቅ፣ አድሜውን ሙሉ ደክሜበታለሁ ፍሬም አፍርቼበታለሁ የሚለውን ትግልና በሽዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ከቤት አውጥቶ ጫካ በማስገባት በጦርነት ሲማግድና ከዚያም ትግሉን በመክዳት በአስር ሽህዎች የሚቆጠሩ ታጋዮችን በካምፕ አጉሮ ያስፈጀው ግለሰብ ዛሬ ላይ ቆሞ የትግሉን አላማ አላውቅም ማለቱን እንደ ግለሰቡ የወንጀል ድርጊት ሳይሆን የትግሉ መገለጫ አድርጋ መውሰዷ ራሷን ብቻ ሳይሆን ቀድሞም የተዋረደውን ሰውዬ የባሰ መቀመቅ እንዲገባ እንዳደረገችው አልታወቃትም ማለት ነው።
ይቺ ሴት የዘመኗን የብዙ ታጋዮች አሟሟት ሳትጽፍ እነሌንጮ ለ50 አመት ቀብረው ያቆዩትን የባሮና በdhoን አሟሟት ታሪክ ለምን መጻፍ እንደፈለገች ስትጠየቅ "ይሄ ታሪክ ተጣሞ ተነግሮ ለረጅም ጊዜ "ጃራ ነው የገደለው" ተብሎ ጃራ ሲወነጀልበትና መጽሐፍም የተፃፈበት በመሆኑ ይሄንን ባልሠራው ወንጀል እየተወነጀለ ያለን ሰው ለማንፃት ነው የጻፍኩት ትላለች። "አዛኝ ቅቤ አንጓች" ነው ያሉት?
ሲጀመር "ባሮን ጃራ ነው የገደለው" የሚለውን ኮነሰፒረሲ የፈጠረው ሌንጮ ነው። ሌንጮ ከዚያ ኢንሲደንት በኋላ ሸሽቶ ወደጀቡቲ እንደወጣ የመጀመሪያ ሥራው ያደረገው ይሄን ተንኮል ቀምሞ በፓንፉሌት አውጥቶ መበተን ነበር። በዚህ የተናደደው ጃራ በድርጅቱ ውስጥ የነበሩ ሙስሊሞችን ይዞ ከድርጅቱ ወጥቶ የኢስላሚክ ኦሮሚያ ግንባርን መሰረተ። በሁለቱ ግንባሮች መሃል በተደረገ ጦርነትም በርካታ የኦሮሞ ታጋዮች እርስበርስ ተዋግተው ተሰውተዋል፤ የድርጅቶቹም አቅም ተመናምኖ ትርጉም አልባ እንዲሆኑ በማድረግ ሌንጮ ተልኮውን ተወጥቷል። የሌንጮ ደርጅቱን ከውስጥ የመቦርቦር ሴራ ከዝያ ይጀምራል። በኔ እምነት የሺኒጋውም ገጠመኝ የዚህ ሰው እጅ እንደሌለበት ጥልቅ ምርመራ ይፈልጋል የሚል እምነት አለኝ። ምክኒያቱም ሙሉ አመራሩ በአንድነት ወደ ሞቃዲሾ እንዲሄዱ የጠራቸው አሱ በመሆኑና እንዲህ አይነት ጉዞ የሚደረግበት አመክንዮም በጭራሽ የማይታይ በመሆኑ።
የባሮና የበdho አሟሟትን አስመልክቶ በአጭሩ በኢንተርቪዋ አንደ ገለፀችው በdho አእምሮው በመቃወሱ ያንን ድርጊት እንደፈጸመ ጠቅሳለች። ይሄ በሌሎችም የዝያ አካባቢ ሰዎችም ተደጋግሞ የተነገረ በመሆኑ ከሷ የማይጠበቅ አዲስ ሃሳብ አይደለም። ከጥላቻ በነፃ አእመሮ የምትጽፍ ብትሆን ኖሮ ግን መጠየቅ የነበረባት፣
1)በdho አእምሮው ከተቃወሰ እንዴት ትጥቅ ይዞ ሊንቀሳቀስ ቻለ?
2)ከባሮ ጋር ለወራት ቆይተዋል፣ ባሮን መግደል ከፈለገ የነሌንጮን መምጣት ምን አስጠበቀው?
3)በእለቱ ግድያው እንዲፈፀም ያነሳሳው ምክንያት ምን ነበር?
4)ይሄ ግድያ የተፈጸመው እነሌንጮ በቦታው የደረሱ እለት መሆኑ ግድያውን ለማቀጣጠል የነሱ እጅ መኖሩን አያሳይም ወይ?
4)ሊገደል የተፈለገውስ ትክክለኛ ሰው ማን ነበር፣ ባሮ ወይስ ሌንጮ፣ ወይም ሁሉም?
5)ሌንጮ እንዴት ተረፈ?
6)በdhoን ማን ገደለው?
7)ግድያውስ ይሄን ያህል አመት ለምን እንዲደበቅና አሁን ተጣሞም ቢሆን እንዲወጣ ተደረገ? ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት አለባቸው።
መጽሀፉን ስለላነበብኩ እነኝህንና መሰል ጥርጣሬ አጫሪ ሁኔታዎችን የማይገልፅ ከሆነ ሌንጮን ከወንጀሉ ለማፅዳት የተደረገው መጋጋጥ አሁንም ትርጉም አልባ ሆኖ ማለፉ አይቀሬ ነው።
በጣም የሚገርመው ጃራ ፊንፊኔ መጥቶ ትግሉ እንደተጀመረና የተማረ የሰው ኃይል እንደሚያስፈልገውና እንዲቀላቀሉት ለባሮና ለሌንጮ ሃሳብ አቅርቦ እነሱ መሄድ እንደማይፈልጉና ከደርግ ጋር እየሰሩ አላማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ ነግረውት አዝኖ ሲመለስ ብቸኛው ቆርጦ አብሮት የወጣው ጀግና በdho ደቻሳ ብቻ ነበር።
በdho የግንባሩ የፖለቲካ ኃላፊ ሆኖ የፖለቲካ ትምህርት ማኗል ከማዘጋጀቱም በተጨማሪ "Sagale Bosona" የሚል ፓምፉሌት በማውጣት ሠራዊቱንም ሆነ ህዝቡን በማንቃት ድርሻውን የተወጣ ቢሆንም እነሌንጮ በጠነሰሱት ጦሩን የማፍረስ ተንኮል ተናዶ "ፊንፊኔ ለፍተን ያቋቋምነውን አፍርሳችሁ አሁን ደግሞ ይችን በጃችን የቀረች ኩራዝ ልታጠፉ ነው የመጣችሁት!!?" ብሎ ተናግሮ ነበር ሌንጮን ሊገድል የተኮሰው ነው የሚባለው። ባሮ የተገደለው "ijoollee walnyaattu!!!" ብሎ በሁለቱ መሃል ሲገባ ለሌንጮ የተተኮሰች ጥይት አግኝታው ነው የተመታው ይባላል።
"አንበሶች የራሳቸውን ታሪክ መጻፍ አስከሚጀምሩ የአዳኞች የአሸናፊነት ታሪክ ብቻ ነው የሚጻፈው" እንደተባለው ወገን የሌለው የደሃው በdho ታሪክ በከሃዲዎች (ዛሬ የሚገኙበት ቦታ በቂ ምስክር ነው) ከኦሮሞ የትግል ታሪክ ውስጥ እንዲፋቅ ከመደረግ አልፎ የሞተን ሰው በእብድነት እየከሰሱ ቀጥለዋል።
ይቺ ግልብ ባለጌም ሕይወቱ በአጭር የተቀጨው የበdho ተቀብሮ የቀረ ታሪክ ሳያስጨንቃት ጃራ ባሮን ላለመግደሉ በሌንጮ ለታ የክሊራንስ ደብዳቤ የተሰጠው የጃራ ታሪክ መበላሸቱ እንዴት ሊያሳስባት እንደቻለ ግልጽ አይደለም። ለመሆኑ ሌንጮ ደኛ ነው ወይስ አቃቤሕግ ለአንድ ሰው ከተጠረጠረበት/ከታማበት ወንጀል ነፃ መሆኑን ክሊራንስ የሚሰጠው?
መጽሐፉን አግኝቼ ባለነብም የተጻፈበት ሁለት አላማ እንዳለው እንዲሁ መገመት እችላለሁ።
1) ሌንጮ 50 አመት ሙሉ ደብቆት የኖረውን ይሄን በደም የተጨማለቀ ወንጀሉን ከመሞቱ በፊት በሷ በኩል የሀሰት ኑዛዜውን አስቀምጦ ራሱን ሳኒታይዝና ዲኦደራይዝ አድርጎ ለማለፍ የተጠቀመበት አውትሌት ነው ብዬ እገምታለሁ።
2) ከደርግ ጊዜ ጀምሮ በወለጋና በመሃል ኦረሚያ ኦሮሞዎች መሃል በነሌንጮ ተፈብርኮ ሲነዛ የነበረውና ከፊንፊኔ አሰከ ትግል ሜዳዎች ለትግል የተሰለፉ የብዙ የመሃል ኦሮሚያ ኦሮሞዎችን ነብስ የበላ የጥላቻ መርዝ በቁቤ ትውልድ አስተዋይነትና ትእግስት እየተሸነፈ መምጣቱ ያሳሰባቸው የሴራው ጠንሳሾችና የነዚህ ኦሮሞዎች አንድነት የሚያገለግሉትን መንግሥት ወምበር እያንገጫገጨ ስለመጣ በዚች ወረንጦ ተጠቅመው በበdhoና በባሮ ሞት ስር ተከልለው ጥላቻውንና መበላላቱን እንደገና ለማስቀጠል የመጣ ሴራ ከመሆን አይዘልም። ስለዚህም በሁሉም ወገን ያለ ኦሮሞ እዚህ ወጥመድ