ሳፋሪኮም በ3 ዓመታት ውስጥ የኔትዎርክ ማማዎችን በሦስት እጥፍ ለማሳደግ እቅድ እንዳለው ገለፀ
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 3 አመታት ከ1.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት በማድረግ በመላ ሀገሪቱ የኔትወርክ ተደራሽነቱን ለማስፋት የሚያንቀሳቅሳቸውን የቴሌኮም ማማዎች በሶስት እጥፍ ለማሳደግ እቅድ እንዳለው ገለፀ።
ኩባንያው በፀጥታ ችግር ምክንያት በሚፈለገው ልክ ተደራሽቱን ማስፋት እንዳልቻለ ሲገልፅ በአሁኑ ወቅት 2,500 የኔትዎርክ ማማዎችን የሚያንቀሳቅስ ሲሆን 1,000 ያህሉን ከኢትዮ ቴሌኮም የተከራየው መሆኑን የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ዊም ቫንሄሌፑቴ ለሪፖርተር ተናግረዋል።
ሳፋሪኮም በአዲስ አበባ እና በሌሎች 26 የከተማ አካባቢዎች ተደራሽ መሆኑን የገለፁት ሀላፊው ነገር ግን ኩባንያው በመላው ሀገሪቱ አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረስ እስከ 7ሺ የኔትዎርክ ማማ የሚያስፈልገው መሆኑን አንስተዋል።
@TikvahethMagazine