ህወሓት በዝግ የተደረጉ ስብሰባዎች መረጃ ከየት ነው የምታገኙት በማለት ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶችን እያስፈራራ ነው ተባለ
ህወሓት በቅርቡ ያካሄደውን 60 ቀን የፈጀ ዝግ ስብሰባን ጨምሮ በሌሎች ስብሰባዎች የተነሱ ጉዳዮችን የተመለከ መረጃ ለጋዜጠኞችና ለአክቲቪስቶች ማን ነው አሳልፎ እየሰጠ ያለው የሚለውን ለማወቅ ያለመ ኮሚቴ በማቋቋም ምርመራ መጀመሩን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።
በትናንትናው ዕለት አንድ የቀድሞ የድምፂ ወያነ ጋዜጠኛና የተለያዩ ህወሓትን የተመለከቱ ጉዳዮች በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በማጋራት የሚታወቅ ጋዜጠኛ በዚሁ መርማሪ ኮማቴ ጥሪ ቀርቦለት በመቀለ ከተማ በመገኘት ከኮሚቴው አባላት ጋር ቆይታ እንዳደረገ ተናግሯል።
በቆይታውም በቅርቡ የተካሄደው 60 ቀናት የፈጀውን ስብሰባ ላይ የተነሱ ጉዳዮች የተመለከቱ መረጃዎች እንዴትና ከማን ነበር ስታገኝ የነበረው የሚሉ ጥያቄዎች እንደቀረቡለት የገለፀ ሲሆን ጥያቄዎቹም ከትብብር ይልቅ በማስፈራራትና ለማወጣጣት በመሞከር የተቃኙ እንደነበሩ ተናግሯል።
ዳጉ ጆርናል የደረሰው መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነም በጦርነቱ ወቅት የህወሓት ጦር ቃል አቀባይ የነበረው ገብረ ገብረፃዲቅና የቀድሞ የትግራይ ደቡባዊ ዞን አስተዳዳሪ የነበረው ሃይለ አሰፋ የዚህ መርማሪ ኮሚቴ አባላት እንደሆኑ ነው።
#ዳጉ_ጆርናል