ከኢትዮጵያ ህዝብ 3 በመቶ የሚሆነው ሰው የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት እንዳለበት ተነገረ
በአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ላይ በከፍተኛ ደረጃ ትኩረት ቢሰጥ ለውጥ እንደሚመጣ የፍቅር ኢትዮጵያ የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ማህበር አስታዉቋል።የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት የአአዕምሮ ብስለቱ ከአማካኝ በታች የሆነ እና በግላዊና በማህበራዊ ክዋኔዎች ላይ የብቃት መጓደል ሲያጋጥም የሚከሰት መሆኑን ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን የተናገሩት የፍቅር ኢትዮጵያ የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ማህበር ስራ አስኪያጅ ወ/ሬ ሸዋጌጥ ክብረት አንድ ልጅ ሲወለድ ጀምሮ ያለው የተፈጥሮ ዕድገት ደረጃዎች ላይ ጉድለት ሲያጋጥም ነው ብለዋል።
የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው ሰዎች በዕድሜያቸው ማድረግ ያለባቸውን ተግባራት ባያከናውኑም በስልጠና እና በክትትል ግን ማድረግ እንዲችሉ ይደረጋል ።ሙሉ ለሙሉ ምንም አይነት ተግባራትም ማከናወን አይችሉም ማለት እንዳልሆነም ገልፀዋል።ሁሉም ሰው በዚህ ጉዳይ ላይ ትኩረት ቢያደርግ እና ግንዛቤ ቢኖረው የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት በተፈጥሮም እንዲሁም ከውልደት በኃላ የሚከሰት መሆኑን አክለዋል።እናቶች በእርግዝና ጊዜ በቂ ክትትል ባለማድረግ፣በእርግዝና ጊዜ በሚያጋጥም መውደቅ እና መጋጨት ህፃናት ላይ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያጋጥማቸዋል።ከኢትዮጵያ ህዝብ 3 በመቶ የሚሆነው ሰው የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት እንዳለበት መረጃዎች ያመላክታሉ ሲሉ ወ/ሬ ሸዋጌጥ ክብረት ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡
ፍቅር ኢትዮጵያ የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ማህበር በ1997 ዓ.ም በአዕምሮ ዕድገት ቧሏቸው ወላጆች የተቋቋመ ነው።በአሁን ሰዓት በ8 ክልሎች እና በ17 ቅርንጫፎችን ከፍቴ እየሰራ እንደሆነም ሥራ አስኪያጇ ገልፀዋል።በዛሬው ዕለትም የፍቅር ኢትዮጵያ የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ማህበር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸውን ክፍሎች ለመደገፍ የሚያስችለውን የቴሌ ብር አካውንት/513210/ ይፋ አድርጓል።
በምህረት ታደሰ
#ዳጉ_ጆርናል