የዓለም ምግብ ፕሮግራም እርዳታ እንዲያቆም ታዘዘ‼️
የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ በአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ በተለያዩ አገራት የሚሠጣቸውን ዕርዳታዎች እንዲያቆም ትዕዛዝ እንደደረሰው ሮይተርስ ዘግቧል። ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርክ ሩቢዮ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ያስተላለፉት የ90 ቀናት የዕርዳታ እገዳ ትዕዛዝ አሜሪካ በዩ ኤስ ኤ አይ ዲ በኩል በምትሠጣቸው አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታዎችና የነፍስ አድን ዕርዳታዎች ላይ እንዳይተገበር መመሪያ አስተላልፈው ነበር። ኾኖም ለዓለም ምግብ ፕሮግራም የደረሰው የእገዳ ትዕዛዝ 507 ሺሕ ሜትሪክ ቶን የሚደርስ የምግብ አቅርቦትን እንደሚያስተጓጉል ድርጅቱ መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል። ከዚህ ምግብ ውስጥ አብዛኛው በ23 አገራት መጋዘኖች እንደሚገኝና ከፊሉ ወደተለያዩ አገራት በመጓጓዝ ላይ መኾኑን ጠቅሶ ማብራሪያ እንደጠየቀም ዘገባው አመልክቷል። የዓለም ምግብ ፕሮግራም ኢትዮጵያ ውስጥ ዋነኛው የአስቸኳይ ሰብዓዊ ዕርዳታ አቅራቢ ነው።
@Addis_Reporter