የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች በሰሜን ሸዋ ዞን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎችን እየተመለከቱ ነው።
ደብረ ብርሃን: የካቲት 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የክልሉ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተሞች ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር) ጨምሮ የክልል እና የዞኑ ከፍተኛ መሪዎች ናቸው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎችን እየተመለከቱ የሚገኙት።
መሪዎቹ በሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላ እና ጠራ ወረዳ ጨኪ ቀበሌ ጄር የተቀናጀ የምግብ ኢንዳስትሪን ተመልክተዋል።
በምግብ ኢንዱስትሪ ማዕከሉ 11 የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ይገኛሉ።
ፋብሪካው የምግብ ዘይት እና የእንሰሳት መኖ ማቀነባበሪያ ሲኾን በቅርብ ወራት ደግሞ አልሚ ምግብ የማምረት ዕቅድ አለው።
በ20 ሄክታር ላይ ያረፈው ኢንዱስትሪ ማዕከሉ አሁን ላይ በቀን 1ሺህ 400 ኩንታል የኬክ ግብዓት ያመርታል።
መሪዎቹ ሌሎች ኢንዱስትሪዎችንም በመጎብኘት ላይ ናቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporationለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!