BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


SARIS, AKAKI KALITY

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter










Video is unavailable for watching
Show in Telegram


18/07/2017 ዓ.ም

10ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎችና የመምህራን የሳይንስ የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ በዛሬው እለት ተጠናቀቀ።

አውደ ርዕዩ ዛሬን ጨምሮ ላለፉት ሶስት ቀናት በተማሪዎችና መምህራን የተሰሩ የፈጠራ ስራዎች ለህብረተሰቡ ለዕይታ ቀርበው አድናቆት ያተረፉ ሲሆን በመርሀ ግብሩ ማጠቃለያ የተሻለ የፈጠራ ስራ ላቀረቡ ተማሪዎችና መምህራን ዕውቅና ተሰቷል።

በመጨረሻም የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት አራት ዋንጫዎችንና 19 ሜዳልያዎችን በመሰብሰብ ከአዲስ አበባ 2ኛ ደረጃን በመያዝ አሸናፊ ሆኗል።

እነዚህ አራት ዋንጫዎች የተገኙትም፦
1. በመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች አጠቃላይ የፈጠራ ሥራ 2ኛ በመውጣት

2.በ2ኛ ደረጃ መምህራን አጠቃላይ የፈጠራ ሥራ 1ኛ በመውጣት

3.ከሁሉም ክፍለ ከተማ በሽብርቅ 2ኛ በመውጣት

4. በአጠቃላይ በ 2017 የትምህርት ዘመን የፈጠራ ሥራ  ውጤት በከተማ ደረጃ 2ኛ በመውጣት የአራት ዋንጫዎችና የ 19 ሜዳሊያዎች ባለቤት ሆኗል።

በክፍለ ከተማ ደረጃ ለቀረበው አውደ ርዕይም ትምህርት ቤታችን ተማሪዎችንና መምህራንን በማስተባበር ንቁ ተሳታፊ መሆን ችሏል።

በዚህ ሥራ ላይ የተሳተፋችሁና ለደከማችሁ መምህራን፣ ተማሪዎችና ወላጆች ምሥጋናችንን እናቀርባለን።

                              ት/ቤቱ


Forward from: Bulbula GSS Since 2000 E.C student
ቀን - 17/08/2017 ዓ.ም
ለማይ ሶሮባን የተማሪዎች የሒሳብ ውድድር ተሣታፊ ተማሪዎች  በሙሉ
  ቅዳሜ ማለትም በ18/08/2017 ዓ.ም የተማሪዎች የሒሳብ 2ኛ ዙር ፈተና መኖሩ በማወቅ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እንድታከናውኑና እንድትፈፅሙ በሚል መልእክት ማስተላለፋችን  ይታወቃል ፡:
ሆኖም የፈተና ቀኑ ለመጪው ሳምንት ቅዳሜ 25/08/2017 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን እየገለፅን አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
                   ት/ቤቱ


Indeed, the coordination of the participants at today's event was very attractive. Therefore, thank you very much to all the teachers and students (participants) who participated in this program🙏🙏🙏🙏🙏🙏👏👏👏👏👏👍👍👍👍


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


Video is unavailable for watching
Show in Telegram




















ሚያዚያ 16/2017 ዓ.ም

10ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎችና የመምህራን የሳይንስ የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት በወዳጅነት አደባባይ በድምቀት ተከፈተ።

ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሚካሄደው አውደ ርዕይ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች በተውጣጡ ተማሪዎችና መምህራን የተሰሩ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎች ለኅብረተሰቡ ለዕይታ ቀርበዋል።

የትምህርት ቤታችን መምህራንና ተማሪዎችም በዚህ የመክፈቻ አውደ ርዕይ ላይ ተሳታፊ በመሆን የመርሃ ግብሩ ተጨማሪ ድምቀት ሆነው ውለዋል።

20 last posts shown.