18/07/2017 ዓ.ም
10ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎችና የመምህራን የሳይንስ የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ በዛሬው እለት ተጠናቀቀ።
አውደ ርዕዩ ዛሬን ጨምሮ ላለፉት ሶስት ቀናት በተማሪዎችና መምህራን የተሰሩ የፈጠራ ስራዎች ለህብረተሰቡ ለዕይታ ቀርበው አድናቆት ያተረፉ ሲሆን በመርሀ ግብሩ ማጠቃለያ የተሻለ የፈጠራ ስራ ላቀረቡ ተማሪዎችና መምህራን ዕውቅና ተሰቷል።
በመጨረሻም የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት አራት ዋንጫዎችንና 19 ሜዳልያዎችን በመሰብሰብ ከአዲስ አበባ 2ኛ ደረጃን በመያዝ አሸናፊ ሆኗል።
እነዚህ አራት ዋንጫዎች የተገኙትም፦
1. በመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች አጠቃላይ የፈጠራ ሥራ 2ኛ በመውጣት
2.በ2ኛ ደረጃ መምህራን አጠቃላይ የፈጠራ ሥራ 1ኛ በመውጣት
3.ከሁሉም ክፍለ ከተማ በሽብርቅ 2ኛ በመውጣት
4. በአጠቃላይ በ 2017 የትምህርት ዘመን የፈጠራ ሥራ ውጤት በከተማ ደረጃ 2ኛ በመውጣት የአራት ዋንጫዎችና የ 19 ሜዳሊያዎች ባለቤት ሆኗል።
በክፍለ ከተማ ደረጃ ለቀረበው አውደ ርዕይም ትምህርት ቤታችን ተማሪዎችንና መምህራንን በማስተባበር ንቁ ተሳታፊ መሆን ችሏል።
በዚህ ሥራ ላይ የተሳተፋችሁና ለደከማችሁ መምህራን፣ ተማሪዎችና ወላጆች ምሥጋናችንን እናቀርባለን።
ት/ቤቱ