ከአእምሮ ብልህነት አልፎ መሄድ!
የብልህነት መለኪያው በሁለት ይከፈላል:-የስሜት ብልህነት (Emotional Intelligence) እና የአእምሮ ብልህነት (intelligent Quotient)።የስሜት ብልህነት ማለት የግላችንንና የሌሎች ሰዎችን ስሜት የመለየትና የመቆጣጠር፣እንዲሁም ለግል እና ሌሎች ሰዎች ስሜት ሊሰጥ የሚገባውን ትክክለኛ ምላሽ ለይቶ የማወቅ ግላዊና ማህበራዊ ብልህነት ነው። የአእምሮ ብልህነት ማለት የአእምሮ እውቀት መጠንንና አንድን እውቀት የመገንዘብ ብቃት የሚያሳይ መለኪያ ነው።ይህ ብቃት አዳዲስ ንድፈ-ሃሳቦችን የመገንዘብን፣የማመዛዘንንና የተገኘውንም እውቀትን ተግባራዊ የማድረግን ብቃት ያሳያል።በተጨማሪም፣ የመመራመርንና የመተንተንን ብቃትም ይጠቁማል። ጥናቶች እንደሚነግሩን ከሆነ በስራም ሆነ በማንኛውም የማህበራዊ ኑሮ 80% ስኬታችን የሚመጣው ከስሜት ብልህነት ሲሆን፣የአእምሮ ብልህነት የሚሰጠን ግን 20% ብቻ ነው ።በሌላ አባባል ከፍ ያለ የአእምሮ ብልህነት ኖሮህና አእምሮህ በብዙ እውቀት ተሞልቶ ሳለ፣ ስሜታዊ ብልህነት ከሌለህ እና የራስህንና የሌሎችን ሰዎች ስሜት አያያዝ ካላወክበት የአእምሮ እውቀት ብቻውን የትም አያደርስም።.
📚ርዕስ፦የስሜት ብልህነት
✍ደራሲ፦ዶ/ር እዮብ ማሞ
ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @Bemnet_Library 📚