እንደሚባለው በስኬትና በውድቀት መካከል ያለው መሠረታዊ ልዩነት አንዱ የሚሠራውን ሁሉ አልችለውም ብሎ ሲያስብ፣ ሌላው ግን እችለዋለሁ ብሎ ማሰቡ ነው፡፡ ስኬታማ ለመሆን ከፈለጉ ስኬታማ መሆን እንደሚችሉ በርግጠኛነት ይመኑ፡፡ ይህ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ ይሁን እንጂ አንድን ነገር እችለዋለሁ በማለትዎ ብቻ ያደርጉታል ማለት አይደለም፡፡ ቀደም ስል እንደገለፅኩት አንድን ሊሠሩ የፈለጉትን ነገር ሊያከናውኑት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ይህ የሚሆነው አደርገዋለሁ ብለው ከተነሱ ብቻ ነው፡፡ እንዲህ ብለው ከተነሱ ከፍተኛ ደረጃ ሊደርሱ ይችላሉ፡፡ የተዋጣልዎ ነጋዴ፣ እውቅ ፀሐፊ፣ ወደር የሌለው ሰአሊ፣ ድንቅ ድምፃዊና የሙዚቃ ቀማሪ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አንቱ የተባሉ ሐኪም፣ የህግ ሰውና መሐንዲስም እንዳይሆኑ የሚከለክልዎት የለም፡፡ ዋናው ጥያቄ ግን ያደርጉታል ወይ? የሚለው ነው፡፡
📓አደርገዋለሁ
✍️ቤን ስዊትላንድ
📖@Bemnet_Library
📓አደርገዋለሁ
✍️ቤን ስዊትላንድ
📖@Bemnet_Library