ሁሉም ሱስ የሚያመጡ ነገሮች ሲጀምሩ ደስታን ይፈጥራሉ።ደስታን ፍለጋ የሚደረገው ጉዞ ይጠመዘዝና ራስን ወደ መጉዳት ያመራል።መጀመሪያ አከባቢ በትንሽ መጠን የደስታ ስሜት ይፈጥር የነበረው በሂደት መጠኑ ከፍ ካላለ የሚፈለገውን ደስታ አይፈጥርም።ደጋግሞ መጠቀም አዕምሮ ውስጥ ብዙ ለውጦች ይፈጥራል።ሱስ ውስጥ የሚገኙ አብዛኛዎቹ ሰዎች ሱስ ስለማቆም ያስባሉ።ይሁን እንጂ ሱስን ሳይወስዱ ሲቀሩ የሚሰማቸው የድበርት ስሜት እንቅልፍ መተኛት አለመቻልና ምቾት የሚነሱ አካላዊ ለውጦች ሱሱን እንዲወስዱ ይገፏፏቸዋል።ተጠቅመው ሳይጨርሱ "ከነገ ጀምሮ አቅማለሁ" ወይም "ከሚቀጥለው ሰኞ ጀምሮ አቆማለሁ" ወይም "በአዲስ ዓመት እርግፍ አድርጌ እፋታለሁ።" ይሉና ድንገት ሲያቆሙ የሚሰማቸውን ምቾት የማይፈጥር ስሜት መቋቋም ያቃታቸውና ይመለሱበታል።
📚ርዕስ፦የአማኑኤል ሆስፒታል ታሪኮች
✍️ደራሲ፦ዮናስ ላቀው
📚 @Bemnet_Library
📚ርዕስ፦የአማኑኤል ሆስፒታል ታሪኮች
✍️ደራሲ፦ዮናስ ላቀው
📚 @Bemnet_Library