ሊቨርፑል በዚህ ሲዝን በአርነ ስሎት መሪነት ያስመዘገባቸው ቁጥሮች ፦
✅|| በ 15 ነጥብ ልዩነት የኢንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መሪ (70 ነጥብ)። 🏆
✅|| በሊጉ ብዙ ጨዋታዎችን ያሸነፈ ቀዳሚው ክለብ (21 ጨዋታ)። ከኛ ቀጥሎ ብዙ ጨዋታ ያሸነፈው አርሰናል 15 ጨዋታዎችን ነው 🤷♂️
✅|| በሊጉ ብዙ ጎሎችን ያስቆጠረ ቀዳሚው ክለብ (69)። ከኛ ቀጥሎ ብዙ ጎሎችን ያስቆጠረው ቶተንሃም 55 ጎሎችን ነው።
✅|| በሊጉ ትንሽ ጎሎችን ያስተናገደ ሁለተኛው ክለብ (27)።
✅|| በሊጉ ብዙ የጎል ልዩነት ያለው ቀዳሚው ክለብ (+42)። ከኛ ቀጥሎ ብዙ የጎል ልዩነት ያለው አርሰናል +28 የጎል ልዩነት ነው ያለው።
✅|| የሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሞ ሳላህ (27)። ከሱ ቀጥሎ ብዙ ጎል ያስቆጠረው ሃላንድ 20 ጎሎች ነው ያሉት።
✅|| የሊጉ ከፍተኛ አሲስት አድራጊ ሞ ሳላህ (17)። ከሱ ቀጥሎ ብዙ አሲስት ያደረገው ቡካዮ ሳካ 10 አሲስቶች ነው ያሉት።
✅|| በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ብዙ ጨዋታዎችን ያሸነፈ ቀዳሚው ክለብ (7)።
✅|| በኢንግሊዝ ካራባኦ ካፕ የፍፃሜ ተፋላሚ 🏆
✅|| የካራባኦ ካፕ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ኮዲ ጋክፖ (5)።
እናም ብዙ ብዙ ነገሮችን አድርገናል ፤ አርነ ስሎት የርገን ክሎፕን ተክቶ የሊቨርፑል አሰልጣኝ ሲሆን ብዙ ሚዲያዎች በመጀመሪያ ዓመቱ ይባረራል፣ በሊጉ ቢበዛ ከ 5-10 ባሉት ደረጃ ውስጥ ቢጨርስ ነው እያሉ ሲያወሩ ነበር ግን ስሎት ምንም አላለም በተረከባቸው ተጫዋቾች ከጨዋታ ጨዋታ የአጨዋወት ስታይሉን እንደየ ጨዋታው በመቀያየር ማሸነፉን ተያያዘው።
አሁን ላይ እንደዛ ሲለፈለፉ የነበሩት ሰዎች የት እንዳሉም አይታወቅም ስሎት በስራው አዋርዶዋቸዋል።ሊጉን 9 ጨዋታ እየቀረው በ 15 ነጥብ ልዩነት ይመራል፣ ካራባኦ ካፕ እሁድ የፍፃሜ ጨዋታ አለው 👏
በክረምቱ የእራሱን ተጫዋቾች አስመጥቶ ምን እንደሚሰራ ደግሞ ከዚሁ መገመት ይቻላል። እኔ በበኩሌ ፕሪምየር ሊጉን ብቻ አሸንፎ ቢጨርስም በጣም ደስተኛ ነኝ እንኳን የሌላው ደጋፊ የሊቨርፑል ደጋፊዎች ሊጉ ሲጀምር በስሎት ተስፋ አልነበራቸውም እሱ በመምጣቱም የተከፉ ብዙ ደጋፊዎች ነበሩ ፤ የአንድም ዋንጫ ሻምፒዮን እንሆናለን ብሎ የሚገምትም ያለ አይመስለኝም። ግን ቢሆንም እሁድ ድል አድርገን በስሎት ስር በመጀመሪያ ዓመቱ ዋንጫን እንደሚሰጠን እናምናለን 💪🔥
እንኳን ይሄን ሁሉ ሪከርድ ማስመዝገብ ይቅርና ባለፉት 6 አመታት አንድ ደና ዋንጫ ማንሳት ያልቻለ ስንት ወረኛ ቡድን አለ 😊
WE WILL FIGTH UNTIL THE END, WE ARE LIVERPOOL ❤️
@Ethioliverpool143 @Ethioliverpool143