በሸርካ ወረዳ 11 ኦርቶዶክሳውያን ተገደሉ!
በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሽርካ ወረዳ በትናንትናው ዕለት ኦነግ ሸኔ በሚል መጠሪያ በሚታወቁ ታጣቂዎች 11 ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል፡፡
ከግድያው በእግዚአብሔር ፈቃድ ማምለጣቸውን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን የገለጹት መረጃ ሰጭው የ13 ዓመት አዳጊና የ80 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ 11 ሰዎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተወስደው በጥምቀተ ባሕር ማክበሪያው ላይ መገደላቸውንና 6 ምእመናን ደግሞ ያሉበት አለመታወቁን ተናግረዋል፡፡
እየተገደሉ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን አርሰው የሚያድሩና ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎና ግንዛቤ የሌላቸው መሆናቸውን የገለጹት የአካባቢው ነዋሪ የመንግሥት የጸጥታ አካላት የሞቱትን ከመቅበር ባለፈ የተሻለ መፍትሔ አላመጡልነም ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በርካታ የአካባቢው ምእመናን ከአካባቢው የሸሹ መሆኑን ያነሱት መረጃ ሰጭው ሰው ተወልዶ ባደገበት ሀገር በሃይማኖቱ ምክንያት እየተገደለ ነው ያሉ ሲሆን ሀብት ንብረታችንን ጥለን ለመኖር ተገደናል ብለዋል፡፡
አሁን ላይ ከ20 በላይ አብያተ ክርስቲያናት የተዘጉ ሲሆን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን በስደት ላይ ናቸው ሲሉም አክለዋል፡፡
በመጨረሻም ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በዚህ ወረዳ 140 የሚደርሱ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን ገልጸው መላው የዓለም ሕዝብና ኦርቶዶክሳውያን ሞታችንን ባታስቆሙልን እንኳን የነዚህን ሰማዕታት ምስክርነት በማሳወቅ የድርሻችሁን ተወጡ ሲሉ አሳስበዋል፡፡
መረጃው የሰሜን ወሎ ሐገረ-ስብከት ነው!
@Ethionews433 @Ethionews433