በአዲስ አበባና አካባቢዋ ድሮን ያለ ፈቃድ ማብረር አይቻልም- አገልግሎቱ
በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ማንኛውንም አይነት ድሮን ያለ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ፈቃድ ማስነሳትም ሆነ ማብረር እንደማይቻል የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል፡፡
አገልግሎቱ በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ የሚደረግ የድሮን እና ሌሎች በራሪ አካላት አጠቃቀምን በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል።
አገልግሎቱ በመግለጫው÷ተቋሙ በአዋጅ ቁጥር 1276/2014 በተሰጠው ስልጣን መሠረት የመሪዎችን፣ የቁልፍ መሠረተ-ልማቶችን እና ብሔራዊ ኩነቶችን ደኅንነት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የማስጠበቅ ኃላፊነት አለበት ብሏል።
ተቋሙ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ የመጡ ድሮኖች እና መሰል ቴክኖሎጂ ወለድ መሣሪያዎች የሚፈጥሯቸውን ስጋቶች ለመከላከል የሚያስችል በቂ የቴክኖሎጂ እና የሰው ኃይል ዝግጅት ማድረጉንም ጠቅሷል፡፡
ሥራው ውጤታማ እንዲሆንም ለኅብረተሰቡ ግንዛቤ መፍጠር እና ጠንካራ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት እንደሚፈልግ ነው ያመላከተው፡፡
በተለይ ከመጪው የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ጋር ተያይዞ ቅንጅቱን ማጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ማንኛውም አይነት ድሮን ያለ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት መሥሪያ ቤት ፈቃድ ማስነሳትም ሆነ ማብረር እንደማይቻል አጽንኦት ሰጥቷል፡፡
በሥራ ምክንያት ድሮኖች መጠቀም አስፈላጊ ከሆነ ጠያቂው አካል የበረራውን ዓላማ፣ የሚበርበትን ቦታ፣ የድሮኑን አይነት እና የሞዴል ቁጥር በመጥቀስ አስቀድሞ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱን መጠየቅ እና ፈቃድ ማግኘት እንደሚገባ አስታውቋል፡፡
ይህ ሳይሆን ቀርቶ በዘፈቀደ የሚኒሱ እና የሚበሩ ድሮኖች ካሉ ተቋሙ አዲስ አበባንና ዙሪያዋን በጸረ-ድሮን ቴክኖሎጂ ያጠረ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በዚኅም ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም በማንኛውም ጊዜ ድሮኖቹን ከአየር ላይ በመለየት፣ በመጥለፍ እና ወደ አስፈላጊው ቦታ በማሳረፍ እንዲሁም የድሮን አብራሪዎቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ተጠያቂነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልጿል፡፡
ከሥራ ጋር በተያያዘ ድሮኖችን መጠቀም የሚፈልግ ማንኛውም አካል በ+251 983 00 02 98 እና +251 983 00 04 01 ስልክ ቁጥሮች በመደወል ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኘት እንደሚችል በመግለጫው አሳስቧል።
@Ethionews433 @Ethionews433