የ2.4 ሚሊዮን ሕፃናትን ሕይወት የታደጉት አውስትራሊያዊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
***
በዓለማችን ከከፍተኛ ደም ለጋሾች አንዱ የሆኑት እና በደማቸው በሚገኘው ፕላዝማ ከ2 ሚሊዮን በላይ ሕፃናትን የታደጉት አውስትራሊያዊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ጄምስ ሃሪሰን ሕይወታቸው ያለፈው በአውስትራሊያ፣ ኒው ሳውዝ ዌልስ በሚገኝ የእንክብካቤ ማዕከል በእንቅልፍ ላይ ሳሉ መሆኑን ቤተሰቦቻቸው አስታውቀዋል።
ሃሪሰን የ88 ዓመት አዛውንት ነበሩ።
‘ባለ ወርቃማ ክንዱ' በሚል በአውስትራሊያ የሚታወቁት ሃሪሰን፣ ደማቸው ውስጥ የሚገኘው ፕላዝማ እምብዛም የማይገኘውንና በደም ውስጥ በሽታ የመከላከያ ሥርዓት (አንቲ ቦዲ) የሚዘጋጅበትን ‘አንቲ ዲ’ን የያዘ ነበር። ይህ ‘አንቲ ዲ’ የሚለገሰው የገዛ ራሳቸው ደም ፅንሳቸውን ለሚያጠቃባቸው ነፍሰ ጡር ሴቶች ነው።
ፕላዝማ የሰውነት የበሽታ መከላከያ ሥርዓት (አንቲ ቦዲ) የሚዘጋጅበት በደም ውስጥ የሚገኝ ፈሳሽ ክፍል ነው።
ሃሪሰን ደም ለመለገስ ቃል የገቡት የ14 ዓመት ታዳጊ ሳሉ ቀዶ ሕክምና ሲያደርጉ ደም ከተለገሰላቸው በኋላ እንደነበር የአውስትራሊያ ቀይ መስቀል የደም አገልግሎት ሃሪሰንን ለመዘከር ባጋራው ጽሑፍ ጠቅሷል።
ከዚያም የ18 ዓመት ወጣት ሳሉ ጀምረው ፕላዝማ መለገስ የጀመሩ ሲሆን፤ እስከ 81 ዓመታቸው ድረስ በየሁለት ሳምንቱ ደማቸውን ሲለግሱ ቆይተዋል።
እንደ አውሮፓውያኑ በ2015 ፕላዝማ በመለገስ የዓለምን ክብረ ወሰን ይዘው እስከ 2022 ቆይተዋል። ከዚያ ግን ይህን ክብረ ወሰን በአሜሪካዊ ግለሰብ መነጠቃቸውን የቢቢሲ ዘገባ አስታውሷል።
የሃሪሰን ሴት ልጅ ትሬሲይ ሜሎውሽፕ፣ አባቷ ያለምንም ክፍያ እና ህመም የበርካቶችን ሕይወት ስለታደገ ኩራት እንደሚሰማት ገልጻለች።
"ሁልጊዜም ይህን ማድረጉ ምንም እንደማይጎዳው ይናገር እና ‘የምትታደጊው ሕይወት ያንችም ሊሆን ይችላል' ይል ነበር" ብላለች።
ሜሎውሽፕ እና የሃሪሰን ሁለት የልጅ ልጆች የአንቲ ዲ ተቀባይ ናቸው።
"ይህም ሃሪሰንን ልክ እንደኛ ሁሉ በርካታ ቤተሰቦች በእርሱ ደግነት መኖር በመቻላቸው ደስተኛ ያደርገው ነበር" ብላለች።
@Ethionews433 @Ethionews433