በኢትዮጵያ የታገዱ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ቁጥር አራት ደረሰ
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን “ከተቋቋሙበት ዓላማ ውጭ ተንቀሳቅሰዋል” ያላቸውን፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን (EHRDC) ከማንኛውም የስራ እንቅስቃሴ አገደ። ባለስልጣኑ ባለፈው አንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ያገዳቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ቁጥር አራት ደርሰዋል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሁለቱን ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ያገደው፤ ከትላንት ረቡዕ ታህሳስ 16፤ 2017 ጀምሮ እንደሆነ ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተመዘገቡበት ዓላማ መሰረት ስራቸውን ማከናወናቸውን የመከታተል እና የመቆጣጠር ኃላፊነት በአዋጅ የተሰጠው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ፤ ለድርጅቶቹ በትላንትናው ዕለት በላከው ደብዳቤ ለእግድ ያበቃቸውን ምክንያት ዘርዝሯል።
ሁለቱም ድርጅቶች “ከተቋቋሙበት ዓላማ ውጭ” እና “ኃላፊነት በጎደለው መልኩ” በመንቀሳቀስ እንዲሁም “ገለልተኛ ባለመሆን” በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ውንጀላ ቀርቦባቸዋል።
እነዚህ ውንጀላዎች ባለፈው ሳምንት በድጋሚ እንዲታገዱ በተደረጉት፤ የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) እና የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች (LHR) በተባሉት ድርጅቶች ላይም በምክንያትነት ተጠቅሷል።
🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ:- https://ethiopiainsider.com/2024/14668/
@EthiopiaInsiderNews