በ1929 የካቲት 12 ቀን የተፈጸመውን ግፍ ደራሲ ተመስገን ገብሬ በአይኑ የተመለከተውን እንደሚከተለው ከትቦ አስነብቧል
"ቀኑ ብርቱ ፀሐይ ነበር፡፡ በዚያ እስር ቤት በማዘጋጃ ቤት ሜዳ ነበርና ብርቱ ክቢያ ተከበን ታላቅ ፍርሃት ነበር፡፡ ውሃና መብልም አላገኘንም፡፡ በሦስተኛው ቀን ጊዜውም ስድስት ሰዓት ሲሆን አስራ ሰባት ሰዎች በውሃ ጥማቱ ሞቱ፡፡ ይህም ቀን ጨለመ፡፡ እህልና ውሃ ሳናገኝ ሦስተኛው ቀን ነበርና ገንዘብም እየተቀበሉ በኰዳቸው ጣሊያኖች ለእስረኞች ውሃ መሸጥ ጀመሩ፡፡
"ሕይወታችንም በዚህ ስቃይ ውስጥ ታንቃ ስንጨነቅ መሸ፤ እንጂ ለቀን ቀኑ ረጅም ነበር፡፡ ከዚያ ረሐብና ውሃ ጥማት እንዲገድሉን መርጠን ነበር፡፡ ይህንንም ከልክለውን ሁለት ካሚዮን አምጥተው ከዚህ ወደሚሰፋ እስር ቦታ ሊወስዱን እየቆጠሩ ስሙን እየፃፉ 30ውን አሳፈሩት፡፡ እንደተናገርኩት እኔ በጽህፈት ቤቱ በር አጠገብ ስለነበርኩ እስረኛውን አየቆጠሩ አያሳፈሩ መጓዝ የጀመሩ ከወዲያ በኩል ነበርና ስለዚህ የኔ መሄዴ ዘግይቶ ነበር፡፡ ብዙ የሚያሳዝን ቁም ነገሮች በመዘግየቴ አየሁ፡፡
"ሦስት ሴቶች በወሊድ ተጨንቀው ኖረዋል፡፡ ሊወልዱም ቦታ አላገኙምና በአስረኛው ግፊ ተጨፍልቀው ሞተዋል፡፡ ሦስቱም ከትንንሽ ህፃናቶቻቸው ጋር ሬሳቸው ወድቆ አየሁት፡፡ በውሃ ጥማትና በረሃብ እነርሱም በቦምብ ከገደሉት ከሞተው ሰውና ከሬሳው ብዛት የተነሳ እኒህን በወሊድ የሞቱትን ያስተዋላቸው አልነበረም፡፡ እኔንም ሊገድሉኘ ስሜን በሊስት ይዘው ይፈልጉኝ ነበርና ስሜን ፅፈው ሊያሳፍሩኝ ሲሉ ሌላ ስም ነገርኳቸው፡፡ በካሚዮንም እስረኛውን ወደወሰዱበት ስፍራ አጓዙን፡፡
"በመንገድም የካሚዮኑ መብራት በሚወድቅበት እንመለከት ነበር፡፡ መንገዱ ሁሉ ሬሳ ተሞልቶ ነበር፡፡ በገደሏቸው በሐበሾች ሬሳ ተሞልቶ ነበር፡፡ ዝም ብለው በላዩ ይነዱበት ነበር፡፡ በሬሳው ብቻ አይደለም፡፡ ነገር ግን ሬሳውን ደግሞ በካሚዮናቸው በጨፈለቁት ወቅት በሰው ሬሳ መንገዱ ተበላሽቶ ያስጸይፍ ነበር፡፡ ከመንገዱም ዳር የወደቁትን ሬሶች የካሚዮኑ ብርሃን በወደቀባቸው ጊዜ ድመቶች ጐንጫቸውን ነክሰው ጺማቸውን እያራገፉ ሲበሏቸው አየሁ፡፡"
ገጽ 94-95
ተመስገን ገብሬ ህይወቴ (ግለ-ታሪክ)
ክብር ለየካቲት 12 ሰማዕታት !!
@Ethiopian_Digital_Library