አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከ3.2 ቢሊዮን ብር በላይ ግብር ያለባቸው 62 ግለሰቦች ከአገር እንዳይወጡ ከለከለ
እገዳው የተጣለባቸው ግብር ከፋዮች በተደጋጋሚ ግብራቸውን እንዲከፍሉ የተደረገላቸውን ጥሪ ችላ ያሉ ናቸው።
ቢሮው ይህንን እገዳ ለመጣል የግብር አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 44 (ንዑስ አንቀጽ 1-3) መሠረት በማድረግ ሲሆን የእነዚህ ግለሰቦች ስም ዝርዝር ለፌዴራል ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መላኩ ተጠቁሟል።
ይህ እርምጃ የተወሰደው ቢሮው በ2017 በጀት ዓመት የዕዳ አሰባሰብና አስተዳደር ክፍሉን በማደራጀት ግብር ከመሰወር ጋር በተያያዘ የሚደረገውን ጥረት አጠናክሮ በመቀጠል መሆኑን አስታውቋል።
በድጋሚ በተዋቀረው ክፍል ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ከ6.4 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብን የገለፀዉ የገቢዎች ቢሮ ሁሉም ግብር ከፋዮች ግዴታቸውን በአግባቡ እንዲወጡና ለከተማዋ እድገት እንዲያግዙ አሳስቧል።
Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily