በኢትዮጵያ ጨምሮ በሌሎች አፍሪካ ሀገራት የሚንቀሳቀሰዉ "አግራ" በዩኤስኤአይዲ መቋረጥ 40 ሚሊዮን ዶላር አጣየአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ህብረት (AGRA) የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በወሰዱት የእርዳታ ቅነሳ ምክንያት 40 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የገንዘብ ድጋፍ ማጣቱን አስታውቋል።
በኬንያ መቀመጫውን ያደረገዉ አግራ በኢትዮጵያ ጨምሮ በ12 የአፍሪካ አገራት ውስጥ ከትናንሽ አርሶ አደሮች ጋር በመተባበር የግብርና ልምዶችን ለማሻሻል፣ ገቢን ለማሳደግ እና ዘላቂ ልማትን ለማበረታታት የሚሰራ ግዙፍ ግብረሰናይ ተቋም ነው።
ድርጅቱ እንደገለፀዉ ከ ዩኤስኤአይዲ የሚገኘው የገንዘብ ድጋፍ መቋረጥ ቀደም ሲል የተጀመሩ ሥራዎችን እየጎዳ እንደሚገኝ ጠቁሟል።
የአግራ ፕሬዝዳንት አሊስ ሩህዌዛ እንደተናገሩት ሌሎች የአውሮፓ አገራት ለጋሾችም የገንዘብ ድጋፋቸውን እየቀነሱ መሆኑን ። ይሁን እንጂ የአሜሪካ የእርዳታ ቅነሳ የአፍሪካ አገራት በግብርናው ዘርፍ ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ እንደ "ማንቂያ ደዉል" መሆኑን መናገራቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል።
ይህ የ 40 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ አግራ ከ ዩኤስኤአይዲ ሊያገኘው ከታቀደው 100 ሚሊዮን ዶላር የእርዳታ አካል እንደነበር ገልጿል።
በተመሳሳይ በዚህ ሳምንት የተባበሩት መንግስታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ በቂ የገንዘብ ድጋፍ ባለመኖሩ 650,000 የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያለባቸውን ሴቶችና ህጻናት እርዳታ ሊያቋርጥ እንደሚችል አስታውቋል።
Source: capitalethiopia @Ethiopianbusinessdaily