በአዲስ አበባ የባቡር ትራንስፖርት ትኬት ሽያጭ በዲጂታል መልኩ ሊጀመር ነው።
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ከወረቀት ትኬት ሽያጭ ወደ ዲጂታል ሽያጭ አገልግሎት ሊሸጋገር መሆኑን ገልጿል።
የዲጂታል ትኬት ሽያጩ ለጊዜው በተመረጡ ቦታዎች ማለትም በሀያት፣ጦርሀይሎች ዳግማዊ ሚኒሊክና ቃሊቲ ጣቢያዎች እንዲሁም በስታዲየም የሽያጭ ቁጥጥር በማድረግ የሚተገበር ይሆናል ተብሏል፡፡
የክፍያ ሥርዓቱ በቴሌ ሱፐር አፕና በዩኤስ ኤስዲ (USSD) ኮድ አማካኝነት መቁረጥ የሚያስችል ነው።
ይህ የፓይለት ሙከራ ድርጅቱ የወረቀት ሽያጭን ሙሉ ለሙሉ በማስቀረት ወደ ዲጂታላይዝድ የክፍያ ስርዓት ለመሸጋገር ለሚያደርገው ስራ መደላድል የሚፈጥር መሆኑን የድርጅቱ የበላይ አመራሮች ተናግረዋል።
በዲጂታል ሽያጭና ቁጥጥር ለሚሳተፉ ሰራተኞች በሁለት ዙር ስልጠና የተሰጠ ሲሆን የፓይለት ሙከራው በቅርቡ እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አስታውቋል።
ባለፉት 10 አመታት ደንበኞች በተዘጋጁት 39 የትኬት መቁረጫ ጣቢያዎች የወረቀት ትኬት በመግዛት የቀላል ባቡሩን አገልግሎት ሲያገኙ እንደነበር ተመላክቷል።
Source: tikvahethmagazine
@Ethiopianbusinessdaily