እውን መረጃ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Music


📌#ቀዳሚ_ምርጫዎ ➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ ➠ወቅታዊ መረጃዎች ➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች የምታገኙበት ቻናል
ጥቆማ ለመስጠት
👉 @ewun_mereja_bot
#እውነተኛ እና #ትኩስ #መረጃዎች
#እውንነት

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Music
Statistics
Posts filter


ሲፒጄ ባወጣው ሪፖርት በአለም ላይ የታሰሩ ጋዜጠኞች ቁጥራቸው 361 ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ 67 ጋዜጠኞች አፍሪካ ውስጥ ናቸው::

ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር በአፍሪካ በሶስተኛነት ተቀምጣለች::

#እውን_መረጃ


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
እናት እና አባቱ ፊት ልጃቸውን ያማል 😭

ኦሮሚያ ውስጥ ወታደሮች አንድ የሲቪል ልብስ የለበሰ ወጣትን እጁን ወደኋላ አስረው በጭካኔ ሲረሽኑ የሚያሳይ ቪድዮ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ተለቋል

ቆይ፣ ይህ በቪድዮ የተቀረፀ ነው። እንዲህ ተቀርፆ ለህዝብ ያልደረሰ ምን ያህል ግፍ በየቀኑ ይፈፀማል?

ቪዲዮ የማየት አቅሙ ካላችሁ ከላይ ተለቋል

ነፍስ ይማር ወንድሜ!

#እውን_መረጃ


በአፋር ክልል የሴት ልጅ ግርዛት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ

በአፋር ክልል በሴቶች ላይ የሚፈፀመውን የሴት ልጅ ግርዛት ለመከላከል በርካታ ሥራዎች ቢሰሩም፤ በቂ ለውጥ ማምጣት አለመቻሉን የክልሉ ሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮን ጠቅሶ አሐዱ ዘግቧል።

ጎጂ ባህላዊ ልማዶች እና ሃይማኖታዊ የሚመስሉ አካሄዶች የችግሩ ዋነኛ መንስኤ እንደሆኑ ነው የተገለጸው።

#እውን_መረጃ


እናት ፓርቲ የጣሪያ ግድግዳ ግብር ላይ የመሠረተው ክስ ተቀባይነት ማግኘቱን አስታወቀ

እናት ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጣሪያ ግድግዳ (የንብረት ግብር) ብሎ ከከተማዋ ነዋሪ እየሰበበሰበ ባለው ግብር ላይ መስርቶ የነበረው ክስ ተቀባይነት ማግኘቱን ዛሬ ባወጣው መግለጫው አስታውቋል።

ፓርቲው ግብሩ "ሕገ ወጥ" መኾኑን በመግለጽ ክስ መስርቶ ነበር።

ክሱን የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አስተዳደር ችሎት በዛሬ እለት ባስቻለው ችሎት የንብረት ግብር ማሻሻያ ጥናት ተብሎ በሚያዝያ ወር 2015 ዓ/ም የወጣውና ለግብሩ መሰብሰብ መሠረት የሆነው መመሪያ "ተፈጻሚነት ሊኖረው አይገባም" ተብሎ መመሪያው እንዲሻር በሙሉ ድምጽ መወሰኑን እናት ፓርቲ አስታውቋል።

#እውን_መረጃ


ጄኔራሉ ማዕቀብ ተጣለባቸው

ዩናይትድ ስቴትስ በሱዳን ጦር መሪው አብደል ፋታህ አል ቡርሃን ላይ ማዕቀብ መጣሏን በግምጃ ቤት ሚኒስቴር በኩል አስታውቃለች።

በአል-ቡርሃን ባለቤትነት የሚተዳደሩ ማንኛዉንም በአሜሪካ የሚገኝ ንብረት እንዳይንቀሳቀስ የሚያግድ እና አሜሪካውያንም ከጄነራሉ ጋር እንዳይገናኙና ንግድ እንዳይፈፅሙም ይከለክላል።

ማዕቀቡ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ሄሜቲ በመባል በሚታወቁት የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሎች (አርኤስኤፍ) መሪ መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ ላይ የተወሰዱ ተመሳሳይ እርምጃዎችን ተከትሎ የመጣ ነዉ፡፡

#እውን_መረጃ


“የህዳሴ ግደቡን በተመለከተ ሰሞኑን የሚነሳው ወሬ መሰረተ ቢስ ነው”  ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)

“ለህዳሴው ግድብ ይህን ያህል ያስፈልጋል በሚል ከመንግስት የተገለጸ የገንዘብ መጠንም የለም” ሲሉ ዶክተር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር   ለገሰ ቱሉ ዶ/ር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም መንግሥት  ለህዳሴው ግድብ ይህን ያህል ያስፈልጋል በሚል ከመንግስት የተሰጠ የገነዘብ መጠን የለም ብለዋል፡፡

በተለያየ ምክንያት ለህዳሴ ግድቡ ብቻ ሳይሆን ለተለያዩ ሜጋ ፕሮጀክቶች  የሚያሥፈልጉ ገንዘቦች አሉ  ግን "በተለያዩ ሰዎች" እንደሚወራው ይሄንን ያክል አይደልም ብለዋል፡፡

የማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያውን ተከትሎ  የወጪ ልዩነቶች ሊኖሩ ይችላሉ ለዚህም መንግስት  የሚያስፈልገውን ወጪውን ያውቀዋል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በዚህም የተጠቀሰውን ገንዘብ ያክል እንኳን ለህዳሴ ግደቡ ቀርቶ የሌሎች ፕሮጀክቶችም ተደምሮ ይሄን ያህል  ሊያስፈልግ ይችላል በመሆኑም የሚነዛው ወሬ ማህበረሰቡን  ለማደናገር ያለመ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ሙሉ ግንባታው ሊጠናቀቅ 2 ነጥብ 4 በመቶ ብቻ የቀረው ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ቀሪ ስራዎች ለማጠናቀቅ 80 ቢሊዮን ብር  ያስፈልገዋል መባሉን መዘገቡ ይታወሳል።

#እውን_መረጃ


ታጋቾችን ለማስለቀቅ ከስምምነት መደረሱ ተሰማ

ታጋቾችን ለማስለቀቅ ከሐማስ ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን የጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ቢሮ አስታወቀ።

ኔታንያሁ ሐሙስ ዕለት ድምጽ እንደሚሰጥበት ሲጠበቅ የነበረውን የጋዛን የተኩስ አቁም ስምምነት 'ሐማስ በመጨረሻ ሰዓት ሃሳቡን ለመለወጥ እየፈለገ ነው' በማለት ስምምነቱን ለማፅደቅ የሚሰጠውን የምክር ቤት ድምፅ እንዲዘገይ አድርገው ነበር።

ሆኖም አርብ ጥዋት፣ ጥር 9/ 2017 ዓ.ም ተደራዳሪው ቡድን ስምምነት ላይ መደረሱን ለኔታንያሁ እንዳሳወቃቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ገልጿል።

#እውን_መረጃ


የጥምቀትን በዓል ያለምንም አደጋ ለማክበር ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ

የጥምቀት በዓልን ከአደጋ በፀዳ ሁኔታ ለማክበር ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ጥሪ አቅርቧል፡፡

ለበዓሉ አከባበር የተለያዩ ዝግጅቶችን የሚያደርጉ ወጣቶች ማስጌጫዎችን ከመስቀላቸው በፊት የኤሌክትሪክ መስመሮችን በጥንቃቄ እንዲመለከቱ እና አስቀድመው ቅኝት እንዲያደርጉ ያሳሰቡት፤ የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ናቸው።

ከዚህ ቀደም በነበረው የበዓሉ አከባበር የኤሌክትሪክ መስመሮችን ለበዓሉ ተብለው በሚተከሉ ድንኳኖች ውስጥ የሚያስገቡ ሰዎች እንዳጋጠሙ ያስታወሱት አቶ ንጋቱ፤ ከዚህ በፊት ለታቦታት መሸፈኛ የሚውሉ የብረት ሰረገላዎች ከኤሌትሪክ መስመር ጋር በመገናኘታቸው 4 ወጣቶች ሕይወታቸው ማለፉን አስታውሰው የጥንቃቄ መረጃዎች እንዲወሰዱ አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪም ፀበል ለመረጨት ወደ ባህረ ጥምቀቱ የሚያመሩ አካላት ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው፣ ነፍሰ-ጡሮች እና የታወቀ ሕመም ያለባቸው፣ አቅመ ደካሞችና ሕጻናት መገፋፋት ያለባቸው ቦታዎች እንዳይገቡ እንዲሁም ሁሉም የበዓሉ ታዳሚዎች የጥንቃቄ መመሪያዎችን እንዲያከብሩም መጠየቃቸውን አሃዱ በዘገባው አመልክቷል።

ለማንኛውም የአደጋ ጥቆማ 939 አጭር መስመር ላይ መደወል እንደሚቻል የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል፡፡

#እውን_መረጃ


የሱዳን መንግስት ሰራዊት በደቡብ ሱዳናውያን ላይ የፈፀመው ጅምላ ግድያ ቁጣ ቀሰቀሰ

ደቡብ ሱዳን በሱዳን የሚገኙትን አምባሳደሯን ጠርታለች የሱዳን መንግስት ሰራዊት ከሰሞኑ በተቆጣጠረው የጀዚራ ግዛት  በስደት የሚኖሩ ደቡብ ሱዳናውያንን ሲገሉ እና ሲያሰቃዩ የሚያሳዩ በተንቀሳቃሽ ምስል የተደገፉ ሪፓርቶች መውጣታቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል።

በጀነራል አብዱልፈታ አልቡርሃን የሚመራው የሱዳን መንግስት ሰራዊት ለወራት በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ቁጥጥር ስር የነበረውን የጀዚራ  ግዛት ከቀናት በፊት በእጁ ካስገባ በኋላ ፥ በግዛቱ በስደት የሚኖሩ የደቡብ ሰዱን ዜጎች ላይ ጅምላ ግድያ ፈፅሟል ተብሏል።

የደቡብ ሱዳን ኘሬዝደንት ፅ/ቤት ዛሬ ምሽቱን ባወጣው መግለጫ በንፁሃን ዜጎቻችን ላይ ጭካኔ የተሞላበት ግድያ ተፈፅሟል የሚል ክስ አቅርቧል።

በዚህም ደቡብ ሱዳን በፓርት ሱዳን የሚገኙትን አምባሳደሯን ወደ ጁባ እንደጠራች አስታውቃለች።

የሱዳን ሰራዊት ግድያውን የፈፀመው የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ አባል ናቸው በሚል እንደሆነ ከግድያው ያመለጡ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል ።

የሱዳን ሰራዊት ፈፅሟል በተባለው ጅምላ ግድያ በርካቶች ቁጣቸውን የገለፁ ሲሆን የአሜሪካ መንግስት በመሪው አብዱልፈታ አልቡርሃን ላይ ማዕቀብ ሊጥል መሆኑም እየተገለፀ ነው።

#እውን_መረጃ


አሽከርካሪዎች በቀን እስከ 140 ብር ድረስ ለመኪና ማቆሚያ እንደሚከፍሉ በጥናት መረጋገጡ ተገለጸ

ሐሙስ ጥር 8 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)በአዲስ አበባ ኮሪደሮች ላይ የሚጠየቀው የመኪና ማቆሚያ ዋጋ የሕብረተሰቡን አቅም  ያላገናዘበ እንደሆነ ጥናት ማመላከቱ ተገልጿል፡፡

በዚህም ጥናት በፒያሳ ፣ በቦሌ ፣ በአራት ኪሎ ያሉ አራት የኮሪደር መንገዶችን ላይ ባሉ የመኪና ማቆሚያዎች ላይ ትኩረት የተደረገ ሲሆን  በቀን  አሽከሪከዎች ከ40 እስከ 140 ብር ድረስ ለመኪና ማቆሚያ ወጪ እንደሚያደርጉ ተመላክቷል።

እንዲሁም አሽከርካሪዎቹ በቀን ለመኪና ማቆሚያ የማያወጡት ብር አቅማቸውን ያላገናዘበ እንደሆነ ተናግረዋል።

አንድ ወር የፈጀው ጥናት በእነዚህ ኮሪደር መንገዶች የእግረኛም ሆነ የመኪና ፍሰቱ ቀልጣፋ መሆኑን ከ400 የጥናቱ ተሳታፊዎች 65 በመቶ የሚሆኑት የገለጹ ቢሆንም የመንገድ የኮሪደር ልማቱ የእግረኛና የመኪና መጨናነቅን ቀንሷል ብሎ ቢያመላክትም ከንግድ ሱቆችና ከመኖሪያ ቤቶች መፍረስ እግረኛንም ሆነ የመኪናን ቁጥር ከመቀነሳቸው ጋር ያያያዘው ነገር የለም ተብሏል፡፡

ጥናቱን ያጠኑት ሻካ አናላይቲክስ ከ አለም አቀፍ የቢዝነስ ልማት  ጋር በመተባበር ሲሆን የቢዝነስ ልማቱ  በኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ አሰፋ " ጥናቱ ያተኮረባቸው ኮሪደሮች  ከፒያሳ አራት ኪሎ ፣ ከአራት ኪሎ እንግሊዝ ኤንባሲ ፣  ከአራት ኪሎ ቦሌ ድልድይና   ከሜክሲኮ ሳርቤት እንደሆነና  አጠቃላይ ጥናቱ አንድ ወር ፈጅቷል" ማለታቸው ተገልጿል፡፡

#እውን_መረጃ


የማለዳ ዜናዎች

1፤ መንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች በወጪ መጋራት ፖሊሲ የሚከፍሉትን ክፍያ እስከ አምስት ዕጥፍ ገደማ እንደጨመረው ዋዜማ ሰምታለች። የወጪ መጋራት ክፍያ የተጨመረው፣ የአንድ ተማሪ የቀን የምግብ በጀት ከ22 ብር ወደ 100 ብር መጨመሩን ተከትሎ ነው። በአዲሱ ማስተካከያ መሠረት፣ ለአራት ዓመት የዩንቨርሲቲ ቆይታ አንድ ተማሪ ይከፍለው የነበረው ከ25 ሺሕ ብር የማይበልጥ ክፍያ ወደ 120 ሺሕ አሻቅቧል። 35 ሺሕ ብር ገደማ ይከፍሉ የነበሩት አምስት ዓመት የሚማሩ የምህንድስና ተማሪዎች ደሞ ወደ 150 ሺሕ ብር አካባቢ እንዲከፍሉ ይደረጋል። ትምህርት ሚንስቴር አዲሱን የወጪ መጋራት ተመን ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገና ባይልክም፣ በቅርቡ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዋዜማ ተረድታለች።  

2፤ መንግሥት በኦሮሚያ ክልል በክላስተር ከተዘራው የስንዴ ምርት 70 በመቶውን ከአርሶ አደሮች በወቅታዊ የገበያ ዋጋ ገዝቶ እየወሰደ መኾኑን ዋዜማ ሰምታለች። ባኹኑ ወቅት አንድ ኩንታል ነጭ ስንዴ በገበያ ላይ 5 ሺሕ 500 ብር እየተሸጠ ሲኾን፣ አርሶ አደሮች ግን በማዳበሪያ ዋጋ ውድነት የተነሳ ዋጋው አትራፊ እንዳልኾነ ተናግረዋል። ዋዜማ ያነጋገረቻቸው አርሶ አደሮች፣ የምርታቸውን 70 በመቶ ለመንግሥት ለመሸጥ የገቡት ስምምነት ባይኖርም፣ የበላይ አካል ትዕዛዝ ነው በሚል እንዲሸጡ እየተገደዱ መኾኑን ገልጸዋል። ኾኖም ይህ አሠራር በክልሉ ወጥ በኾነ ኹኔታ እየተተገበረ አይደለም ተብሏል። የስንዴ ግዥውን ትዕዛዝ የሚያስፈጽሙት፣ የዞን፣ የወረዳና የቀበሌ መዋቅሮች እንደኾኑ ዋዜማ ተረድታለች።

3፤ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አዋጅ ረቂቅ ማሻሻያ ማዘጋጀቱን አስታውቋል። ረቂቅ ማሻሻያው፣ ቦርዱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አዋጅ የሚጥሱ ፓርቲዎችን ሕጋዊነት ከመሰረዙ በፊት በጥፋቱ ክብደት ልክ እስከ 5 ዓመት ለሚደርስ ጊዜ ማገድ የሚያስችለውን ሥልጣን የሚሠጥ ነው። ቦርዱ የጣለበትን እገዳ የተቃወመ ፓርቲ፣ ውሳኔው በደረሰው በ30 ቀናት ውስጥ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ እንደሚችል የተሻሻለው አዋጅ ይፈቅዳል። ቦርዱ አገራዊ ምርጫ ማካሄድ የማይችልባቸው "ኹኔታዎች" የሚለው አንቀጽም፣ የጸጥታ ችግር፣ ወረርሺኝ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ተብሎ ተዘርዝሯል። ለሕዝብ ተወካዮችና ለክልል ምክር ቤቶች ምርጫ የተመዘገቡ ዕጩዎች ከባድ ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፍንጅ ካልተያዙ በስተቀር፣ የምርጫው ውጤት እስኪገለጽ በወንጀል ተጠርጥረው እንዳይያዙ የሚከለክል አንቀጽም በማሻሻያው ተካቷል።

4፤ ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች ተከላካይ ቡድን (ሲፒጄ) ትናንት ባወጣው ልዩ ሪፖርት፣ ኢትዮጵያን "የተድበሰበሰ ክስ" ከሚመሠርቱ ወይም "በሽብር" ወይም "በአክራሪነት" ውንጀላ ቅጣት ከሚጥሉና ከታጣቂ ኃይሎች ጋር ግንኙነት አላችሁ በማለት ከሚያስሩ አገራት ተርታ መድቧታል።
በዙህም ኢትዮጵያ ከግብጽ፣ ሩሲያ፣ ማይነማርና ቤላሩስ ተርታ ተመድባለች። ኢትዮጵያ ካሠረቻቸው ስድስት ጋዜጠኞች አምስቱ በአማራ ክልል የሚካሄደውን ግጭት ከዘገቡ በኋላ የሽብርተኝነት ክስ እንደተመሠረተባቸው ሪፖርቱ ጠቅሷል። ስድስተኛው ጋዜጠኛ የሺሃሳብ አበራ በመስከረም 2017 ዓ፣ም መታሠሩንና ባለሥልጣናቱ ጋዜጠኛው የታሠረበትን ምክንያት እስካኹን እንዳልገለጡ ወይም ክስ እንዳልመሠረቱበት ሪፖርቱ ገልጧል። ኤርትራ ከሰሃራ በታች ካሉ አገራት 16 ጋዜጠኞችን በማሠር ቀዳሚዋ ኾና የቀጠለች ሲኾን፣ በዓለም ላይ ደሞ ከኢራንና ቬትናም ጋር ሰባተኛዋ ቀዳሚ ጋዜጠኛ አሳሪ ተብላለች።

5፤ አሜሪካ፣ በሱዳን ወታደራዊ መሪና በጦር ሠራዊቱ ዋና አዛዥ ጀኔራል ቡርሃን ላይ ትናንት ማዕቀብ ጥላለች። አሜሪካ በጀኔራል ቡርሃን ላይ ማዕቀብ የጣለችው፣ ከድርድር ይልቅ የጦርነት አማራጭን መርጠዋል በማለት ነው። ጄነራል ቡርሃን የሚመሩት ሠራዊት፣ በሲቪል መሠረተ ልማቶች ማለትም በትምህርት ቤቶች፣ በሆስፒታሎችና በገበያ ቦታዎች ላይ ጥቃቶችን እና ከፍርድ ውጭ የኾኑ ግድያዎችን ይፈጽማል በማለት አሜሪካ ከሳለች። ለሱዳን ጦር ሠራዊት ጦር መሳሪያ ያቀብላሉ የተባሉ አንድ የሆንግኮንግ ኩባንያና አንድ የሱዳንና ዩክሬን ተወላጅ ግለሰብም የማዕቀቡ ሰለባ ኾነዋል። ማዕቀቡ የንብረትና ገንዘብ የማንቀሳቀስና ማንኛውም አሜሪካዊ ዜጋና ኩባንያ ጋር የንግድ ልውውጥ እንዳያደርጉ የሚያግድ ነው። አሜሪካ፣ በፈጥኖ ደራሹ ኃይል ዋና አዛዥ ጀኔራል ደጋሎ ላይ ከቀናት በፊት ተመሳሳይ ማዕቀብ እንደጣለች ይታወሳል።

via:ዋዜማ

#እውን_መረጃ


የአብኑ ጋሻው መርሻ በምክትልዳይሬክተርነት የሚመራው የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት 450 ሰራተኞችን “የአንድ ብሄር የበላይነት አለ” በሚል አባረረ።

በኢትዮ ፖስት የተለያዩ ዲስትሪክቶች ከ20 ዓመት በላይ ያገለገሉ ሰዎችን ጨምሮ እነዚህ ሰራተኞች አሁን ላይ ተቋሙ ላይ እየተደረገ ካለው 'ሪፎርም' ጋር ተያይዞ መሰናበታቸውን ጠቁመዋል።

#እውን_መረጃ


ነብስ ይማር 😭

በሴቶች ላይ ሚደረግ ግድያ  ይቁም!

እቺ ልጅ ስሟ አበበች ትባላለች በአፉን ኦሮሞ አጫጭር የኮሜዲ ቪዲዮ በመስራት ትታወቃለች

አበበች ከሁሉም ጋር ተግባቢ ልጅ ስትሆን ከትላንትና ወዲያ በጀሞ ልዩ ስሙ ሙዚቃ ሰፈር በሚያሳዝን ሁኔታ ባልታወቁ ሰዎች በጩቤ ተወግታ ህይወቷ አልፏል።

አስክሬኗም ወደ ትውልድ ስፍራዋ ወለጋ የሄደ ሲሆን ብዙ ኢትዮጵያውያን ፍትህ ለአበበች እያሉ ይገኛል::

ገዳዮቿን የሚመለከተው አካል አፈላልጎ ለህግ
እንዲያቀርባቸው በትህትና እንጠይቃለን።

የሴት ልጅ ጥቃት ይቁም

#እውን_መረጃ


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ዜና መዝናኛ❗️

የእርሶ ውሻ እንደዚህ ይፈጥናል ?

ግሬይሆንድ የተባሉት ድቅል ውሾች በሰዓት እስከ 72 ኪሎ ሜትር መጓዝ ይችላሉ።

#እውን_መረጃ


መረጃ‼️

በቅርቡ በሱማሊያዋ ፑንትላንድ ጠረፍ አቅራቢያ አንዲት የቻይና አሳ አጥማጅ መርከብ ያገቱት ሱማሊያዊያን፣ የባሕር ላይ ወንበዴዎች አይደለንም በማለት ማስተባበላቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

ሱማሊያዊያኑ መርከቧን ያገቱት፣ የባሕር ላይ ሃብታችን በውጭ አገራት አሳ አጥማጅ መርከቦች በየጊዜው እየተሟጠጠ ነው በሚል ቁጭት እንደኾነ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። መርከቧ ከሰባት ሳምንታት እገታ በኋላ ከጥቂት ቀናት በፊት መለቀቋ ይታወሳል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኃያላን አገራት በሚያደርጉት ቅኝት ሳቢያ ባካባቢው የባሕር ላይ ውንብድና የቀነሰ ሲኾን፣ ይህንኑ ተከትሎ ግን በአገሪቱ የባሕር ግዛት አሳ የሚያጠምዱ የውጭ አገራት መርከቦች ቁጥር ጨምሯል ተብሏል። ማዕከላዊ የሱማሊያ መንግሥት ከፈረሰ ወዲህ፣ የውጭ አገራት መርከቦች መርዛም ዝቃጮችን ጭምር በአገሪቱ የባሕር ግዛት ላይ ሲደፉ እንደኖሩ ይታወቃል።

ቱርክ ከሱማሊያ ጋር በደረሰችው የጋራ መከላከያ ስምምነት መሠረት፣ የአገሪቱን የባሕር ግዛት ለመጠበቅና ከአሳ ሃብቱ ለመጋራት የባሕር ኃይሏን በቅርቡ ማሠማራት መጀመሯ አይዘነጋም።

#እውን_መረጃ


የነዳጅ ማደያዎች በሙሉ ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የኃይል መሙያ ጣቢያ ለመቀየር ጥናት እየተደረገ ነው ተባለ‼️

“ከዚህ በኃላ የተሽከርካሪ አስመጪና የሚገጣጥሙ ድርጅቶች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የኃይል መሙያ ሳይተክሉ በሥራ ላይ መሰማራት አይችሉም” የትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ሚኒስቴር በመዲናዋ የሚገኙ የነዳጅ ማዲያዎችን ወደ ኤሌክትሪክ የሃይል መሙያ ጣቢያ ለመቀየር ጥናት ተጀምሯል ያለው የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ነው፡፡

#እውን_መረጃ


በኢትዮጵያ ወዳጅነታቸው የሚታወቁት አንጋፋ ዲኘሎማት በትራምኘ አስተዳደር አዲስ ሹመት ተሰጣቸው❗️

ቀደም ሲል በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት እና አሁን ድረስ ኢትዮጵያ በጎ ምልከታ ያላቸው አምባሳደር ቲቦር ናዢ በአዲሱ የትራምኘ አስተዳደር አዲስ ሃላፊነት እንደተሰጣቸው አስታውቀዋል።

አምባሳደር ቲቦር ናዢ በኤክስ ገፃቸው እንዳስታወቁት በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ ቦታውን ባልገለፁት ሃላፋነት መመደባቸውን ገልፀዋል።

ከመጪው ሰኞ ጀምሮ  ሃላፊነቱን ተረክበው መስራት እንደሚጀምሩ ጨምረው ገልፀዋል።

ቲቦር ባለፉት ሶስት አመታት በቋሚነት በግል የማህበራዊ ገፃቸው እና በሚድያዎች ቀርበው በሚሰጧቸው በጎ አስተያየቶች ይታወቃሉ።

አሁን በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ውስጥ አዲስ የተሰጣቸው የመንግስት ሃላፊነት ከአፍሪካ ጋር የሚገናኝ አለመሆኑን በደፈናው ከመግለፅ ባለፈ ምን እንደሆነ አልተናገሩም።

አምባሳደር ቲቦር ናዢ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በከፍተኛ ሃላፊነት ከዚህ ቀደም ያገለገሉ ሲሆን በአፍሪካ ቀንድ የካበተ ልምድ እና ተሰሚነት ካላቸው አንጋፋ ዲኘሎማቶች አንዱ ናቸው።

#እውን_መረጃ


የተኩስ አቁም ስምምነት በተደረሰባት ጋዛ እስራኤል በፈጸመችው የአየር ጥቃት 73 ፍልስጤማውያን መገደላቸው ተገለጸ

እስራኤል እና ሐማስ የደረሱበት የተኩስ አቁም ስምምነት በመጪው እሁድ፣ ጥር 11/ 2017 ዓ.ም ተግባራዊ መሆን ይጀምራል የተባለ ሲሆን እስራኤል በጋዛ እየፈጸመችው ያለችው ጥቃት እንደቀጠለች ነው።

ሁለቱ ወገኖች የደረሱበት የተኩስ አቁም ስምምነት ከእስራኤል በኩል የምክር ቤቱን ይሁንታ ማግኘት አለበት ተብሏል።

የተኩስ አቁም ስምምነቱ ረቡዕ፣ ጥር 9/ 2017 ዓ.ም ይፋ መሆኑን ተከትሎ እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት 73 ፍልስጤማውያን በአንድ ምሽት መገደላቸውን በሐማስ የሚተዳደረው የሲቪል መከላከያ ኤጀንሲ አስታውቋል።

#እውን_መረጃ


ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሰጠ ማሳሰቢያ❗️

በካናዳ የሥራና ትምህርት ዕድል ለማመቻቸት ህጋዊ ውክልና በውጭ ጉዳይ ሚኒስት ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞትዮስ የተሰጣቸው በማስመሰል ህገ ወጥ ደብዳቤ አዘጋጅተው እያሰራጩ ያሉ አካላት መኖራቸውን ተገንዝበናል።

የሚኒስትሩ ስም ተጠቅሶ በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያ አውታሮች እየተዘዋወረ የሚገኘው ደብዳቤ ሀሰተኛ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

እንዲህ አይነት የወንጀል ተግባር እየፈፀሙ የሚገኙ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ጋር እየተሰራ መሆኑን በመግለፅ ህብረተሰቡ ይህንን ተገንዝቦ ራሱን ከአጭበርባሪዎች እንዲጠብቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳስቧል።

#እውን_መረጃ


“በወር ከ50 ሺህ በላይ ወጪ እያወጣን ነው” በትግራይ ክልል ያሉ የኩላሊት ህመምተኞች

በትግራይ ክልል ያሉ የኩላሊት ህመምተኞች ለመድኃኒት በወር ከ 50 ሺህ በላይ ወጪ እያወጣን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በትግራይ የኩላሊት ሕሙማን ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሃፍቶም አባዲ፣ ለአንዴ የኩላሊት እጥበት ለማድረግ መድኃኒት 4ሺ 500 ብር እየገዙ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ወጪያቸው በወር 50 ሺህ ብር እንደሚደረስ አመልክተዋል። በገንዘብ እጥረት ምክንያት የከፋ ችግር ላይ እንደሚገኙ ዋና ስራ አስኪያጁ ከአንድ የሀገር ውስጥ ዘጋቢ ጋር በነበራቸው ቆይታ አብራርተዋል።

#እውን_መረጃ

20 last posts shown.