በዩኒቨርሲቲያችን ሲሰጥ የቆየው የ2017 ዓ.ም የመውጫ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ከጥር 26/2017 ዓ.ም ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች የ2017 ዓ.ም የመውጫ ፈተና እየተሰጠ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ጋንዳባ ካምፓስና ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ ከ26/05/2017 ዓ.ም እስከ 01/06/2017 ዓ.ም ሲሰጥ የቆየው ፈተና ያለምንም እንከን የተጠናቀቀ መሆኑ ተረጋግጧል።
የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር የፈተናው በስከት መጠናቀቁን ምክንያት በማድረግ ለስከቱ አስተዋፅዖ ያበረከቱ አካላትን አመስግነው ለሁሉ ተፈታኞች መልካም ምኞትን ገልጿል።
(ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ)
📄
@Exitnewss