የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ቅ/ጽ/ቤቶች የ6 ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ።
ታህሳስ 26/2017 ዓ.ም
የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት የቅ/ፅ/ቤቶች የስራ አፈፃፀም ግምገማ በአዳማ ከተማ ለ2 ቀናት የተደረገ ሲሆን በቦታው ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢቂላ መዝገቡ ለሕብረተሰቡ ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ የአገልግሎት ስርዓት መዘርጋትና መስጠት የአማራጭ ጉዳይ ሳይሆን ግዴታ መሆኑን አሳስበዋል።
አክለውም ተቋሙ ከሚሰጣቸው በርካታ አገልግሎቶች መካከል የፖስፖርት አገልግሎት ለበርካታ ጊዜያት ሕብረተሰቡ ቅሬታ የሚያነሳበትና ተደራሽነቱ በበቂ መጠን ያልተስፋፋ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ይህን አሰራር በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ አሁን ካለው 12 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በተጨማሪ 14 ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶችን በመጨመር የአገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት ፅቅድ ተይዞ በመሰራት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ ብቻ ሲሰጥ የነበረው የአስቸኳይ ፖስፖርት አገልግሎት በሰው ሀይልና በግብአት በተደራጁ 7 ቅ/ጽ/ቤቶች ተደራሽ እንዲሆን መደረጉን ገልፀው በቀጣይ በሁሉም ቅ/ጽ/ቤቶች ግብአቶችን በማሟላት አገልግሎቱ መሰጠት እንደሚጀምር ተናግረዋል።
ሁሉም ቅ/ፅ/ቤች የ6 ወር ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን አሁን ካለው ፍላጎት አኳያ በቀን የማስተናገድ አቅማቸውን ከፍ ማድረግ እንደሚገባና አገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻል እንደሚገባ አሳስበዋል።
በውይይቱ በ6 ወሩ በእቅድ የተያዙ ተግባራት አፈጻጸም የተገመገመ ሲሆን በአፈጻጸም ወቅት የነበሩ ጥንካሬዎች ማስቀጠል እንዲቻልና ድክመቶችን ማረም እንደሚገባ መግባባት ላይ ተደርሷል።
በተጨማሪም የአገልግሎት ክፍተት በታየባቸው ቅ/ጽ/ቤቶች ላይ የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገልፆል።
በመጨረሻም በፓስፖርት አገልግሎት ማንዋል እና በኦን ላይን ሲስተም ላይ ውይይት በማድረግ የተለያዮ አስተያየትና ቴክኒካል ግብአቶች የተሰጡ ሲሆን በቀሪ ወራቶች ስራዎች ላይ መመሪያ ተሰጥቶ መድረኩ ተጠናቋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
——
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/