የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና የኢሚግሬሽና ዜግነት አገልግሎት ለውጭ ባለሀብቶች የሚሰጡትን አገልግሎት ይበልጥ ለማቀላጠፍ የሚያስችል የጋራ ስርዓት እንደሚዘረጉ አስታወቁ።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና የኢሚግሬሽና ዜግነት አገልግሎት የኢንቨስትመንት ፍሰትን ይበልጥ ከፍ ለማድረግና በዘርፉ የሚታዩ ማነቆዎችን ለመፍታት ያላቸውን ቅንጅታዊ አሰራርና ትብብር ይበልጥ እንደሚያጠናክሩ የተቋሙ ሀላፊዎች አስታውቀዋል።
ሁለቱ ተቋማት በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን ለማፍሰስ የሚመጡ ባለሀብቶች ሀገር ውስጥ ከገቡ ጊዜ ጀምሮ ቪዛን ጨምሮ የሚያገኙትን የተለያዩ አገልግሎቶች ቀልጣፋ፣ ምቹ እና የተሟላ መረጃ የሚያገኙበት እንዲሆን የተለየ የውጭ ዜጎች አገልግሎት የሚሰጥበትን ዴስክ ለማመቻቸት በቅንጅት እንደሚሰሩ አሳውቀዋል።
በውይይቱ ወቅት መንግስት ኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት መልህቅ ለማድረግ በሪፎርም ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች በመከተል የተፋጠነ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ሌሎች እርምጃዎችን ለመውሰድ የጋራ አቋም የወሰዱ ሲሆን በቀጣይነትም አተገባበሩን በቅርበት የሚገመግም የጋራ ግብረ-ሀይል ለማቋቋም ከስምምነት ደርሰዋል።
በመጠናቀቅ ላይ ያለው የተቋማቱ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስርዓትን ወደ ስራ በማስገባት ቀልጣፋና የተቀናጀ አገልግሎት በመስጠት ቅንጅታዊ አሰራሩን ከፍ በማድረግ የኢንቨስትመንት ዘርፉን ይበልጥ ምቹና ሳቢ ለማድረግ ከመግባባት ደርሰዋል።
የሁለቱ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች ከውጭ የሚመጡ ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በሌሎችም የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ የሚያጋጥማቸውን ችግሮች በፍጥነትና በተገቢው አግባብ ለመፍታት የሚችል የጋራ ግብረ ሀይል ለማቋቋም ተግባብተዋል።
በተጨማሪም መንግስት ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት የወሰዳቸውን እርምጃዎችን የተዘጋጁ የህግ ማዕቀፎችን የሚያስተዋውቁ ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን ለማመቻቸት ከስምምነት ደርሰዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
——
Telegram:
https://t.me/ICS_EthiopiaFacebook:
https://www.facebook.com/ICSEthiopiaTwitter:
https://twitter.com/ics_ethiopiaTikTok:
https://www.tiktok.com/@ics_ethiopiaLinkedIn:
https://www.linkedin.com/company/icsethiopiaYouTube:
https://www.youtube.com/@Ics_EthiopiaInstagram:
https://www.instagram.com/icsethiopia/