በቅርቡ ልጄ እጁን ተሰብሮ ለቀጠሮ አለርት ሆስፒታል እየተመላለስኩ ነበር። ወረፋ ይዘን በተቀመጥንበት አንድ አባት ከጎናቸው ላለች ሴት ስለ ጉዳታቸው ይነግሯታል። እድሜያቸው የገፋ አዛውንት ናቸው። ኮፍያቸውን አንስተው መሀል አናታቸው ላይ የታሸገ ቁስል አሳዩዋት። "ምን ሆነው ነው?" አለቻቸው። ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው በለሆሳስ የሆነ ነገር ነገሯት። ምን እንዳሉ አልተሰማኝም። የሷ ድንጋጤ ግን ትኩረቴን ሳበው። እየደጋገመች "በስመ አብ! በስመ አብ!" ትላለች። ትኩረቴን ሰብስቤ በነሱ ላይ አደረግኩ። "እኮ የራስዎት ልጅ?!" ስትል "አዎ!" አሏት። ለካስ በገዛ ልጃቸው በአብራካቸው ክፋይ ተደብድበው ኖሯል። የተጎዱት እሳቸው ሆነው ሊያወሩት ግን ተሳቅቀዋል።
"የሰው ጉድ በሆነ ~ ስንቱን ባወራሁት
የራሴ ሆነና ~ በወጭት ቆላሁት።"
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
"የሰው ጉድ በሆነ ~ ስንቱን ባወራሁት
የራሴ ሆነና ~ በወጭት ቆላሁት።"
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor