MY SOROBAN ETHIOPIA - ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


ማይሶሮባን በተለያዩ ከተሞች 👇👇👇
A.A👉 @MySorobanAA
BDR👉 @MYSOROBANBDR
Derie👉 @DERIEMYSOROBAN
Sodo👉 @SODOMYSOROBAN
Adama👉 @AdamaMysoroban
Bishoftu👉 @BishoftuMySos
Gondar👉 @GondarMySos
Harer👉 @HarerMysoroban
D/Birhan👉 @DBmysoroban
Hawasa👉 @HawasaMySos

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter


2016ዓ.ም ሽልማት

በ 2016 ዓ.ም በማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ ውድድር ላይ በመሳተፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሸነፋችሁ እና ስማችሁ በቴሌግራም የተገለፀ ተማሪዎች ብቻ
የገንዘብ ሽልማታችሁን ለመሸለም ቅድመ ሁኔታዎችን እየጨረስን ስለሆነ ሽልማታችሁ (ገንዘቡ) ገቢ የሚደረግበት አካውንት በሚከተሉት ስልኮች
በቴክስት ወይም በቴሌግራም ይላኩልን።

ማስታወሻ
የምትልኩት አካውንት በተማሪ ስም ወይም
በእናት ወይም በአባት ስም የተከፈተ መሆን አለበት።  ይህም ማለት ከ3 ቱ አንዱ ያለው ይሆናል።

"ጉብዝና ያሸልማል"

3ክፍል አሸናፊዎች ሰማይነህ (0913684896)

4ክፍል አሽናፊዎች  ሱራፌል ( 0910711907)

5ክፍል አሸናፊዎች  ሒሩት ( 0943313492)

6ክፍል አሸናፊዎች ሙባረክ ( 0913413427)

7ክፍል አሸናፊዎች ቤተልሔም ( 0934470784)

8ክፍል  አሸናፊዎች ቤዛዊት ( 0961694070)

9-12ክፍል አሸናፊዎች  ማህሌት ( 0961165551)

አባከስ ተወዳዳሪዎች

(0993811878) ትግስት




ሴልሶች የሚቀጠሩባቸው ከተሞች

1. ጅግጅጋ
2. ሐረር
3. ድሬደዋ
4. መቀሌ
5. አክሱም
6. ሐዋሳ
7. ይርጋለም
8. በንሳ
9. ጩኮ
10.አለታወንዶ
11. ብታጅራ
12. ወራቤ
13. ወልቂጤ
14. ሾኔ
15. አላባ
16. ዱራሜ
17. ሰመራ
18. ሎጊያ
19. ዱፍቲ
20. ጋምቤላ
21. አሶሳ
22. ኢተያ
23. አዳማ
24. ጅማ
25.አሰላ
26. ሁሩታ

ማስታወሻ ሌሎች ከተሞችን በቅርቡ እናሳውቃለን።


የሴልስ ወይም የሽያጭ ሠራተኞች ማስታወቂያ

ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ በ2017 ዓ.ም ከሚያከናውናቸው ዋነኛ ስራዎቹ አንዱ
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የታተመ አዲስ መፅሀፍ በመላው ሀገሪቱ ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች መፅሀፉን ማስተዋወቅ ሲሆን ለዚህም
በሀገራችን ኢትዮጵያ በሚገኙ ከተሞች
የሴልስ ( የሽያጭ) ሰራተኞችን መቅጠር ስለሚፈልግ ለ4 ወር በኮንትራት እና በኮሚሽን
መስራት የምትፈልጉ ተዘጋጁ።

ማስታወሻ

1. ፆታ ሴት

2. የትምህርት ደረጃ 10ኛ እና ከዚያ በላይ

3. የክፍያ ሁኔታ ትራንስፖርት እና ኮሚሽን ብቻ

4. ብዛት በአንድ ከተማ ከ3 እስከ 6 ሴልሶች እንደከተማው ስፋት ይወሰናል ለአዲስ አበባ 30 ሴልሶች

5. ስራ የሚጀመረው ሰኞ የካቲት 24/2017
ዓ.ም

6. የመመዝገቢያ ቦታ በቴሌግራም ተከታተሉ።

7. ሴልሶች የሚቀጠሩበትን የከተሞች ዝርዝር
ነገ እናሳውቃለን

ቦነስ
1.ከፍተኛ መፅሀፍ ሽያጭ ያስመዘገበች ከማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ ስራዎች አብራ በቋሚነት ትቀጥላለች።

2. ከሁሉም ከተማ የተሻለ ሽያጭ ያስመዘገቡ
5 ሴልሶች እንደ አከናወኑት የመፅሀፍ ሽያጭ ብዛት መሠረት 200,000 ሺህ ብር በሽልማት ይካፈላሉ።


የማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ እና አጋዥ ድርጅት ሠራተኞች ሙሉ ለሙሉ ስራቸውን በተሟላ እና በዘመናዊ መንገድ ለመጀመር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅቶች ስላጠናቀቁ ማንኛውንም ዓይነት መረጃ ከየካቲት 15/2017 ዓ.ም ጀምሮ በቅርብ በሚለቀቁት ስልክ ቁጥሮች አማካኝነት በመደወል መረጃዎችን ማግኘት እንደምትችሉ በትህትና እናሳውቃለን።

በ2017 ዓ.ም የሚከናወኑ የውድድር አይነቶች

1. የሒሳብ ትምህርት ውድድር
2. የአባከስ ውድድር
3. የስሌት ውድድር
4. ከ 1 - 3 የወጡ ተማሪዎች ብቻ የሚወዳደሩበት የሒሳብ ትምህርት ውድድር
5. የሴት ተማሪዎች ብቻ ውድድር ናቸው።

ማስታወሻ
በ2017 ዓ.ም የአለም ሪከርድ ለመያዝ ሙሉ ዝግጅት ስለጨረስን የሪከርዱ አካል ይሁኑ።


የአባከስ ሽልማት 2016 ዓ.ም

በ2016ዓ.ም አባከስ ሚሊኒየም አዳራሽ ላይ የወረቀት ፈተና የተፈተናችሁ የወላይታ ሶዶ ከተማ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ እና የድሬደዋ ከተማ ተማሪዎች ሁላችሁም በእኩል ድርሻ እንድትካፈሉ 200,000ብር (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ተሸልማቹሀል።

ሽልማታችሁን በሶስት ዙር በእኩል ድርሻ የካቲት 30፣ መጋቢት30 እና ሚያዚያ 30/2017 ዓ.ም በአካውንታችሁ ገቢ ይደረግላቹሀል።

ገቢ የሚደረግበት አካውንት ከየካቲት 25/2017 ዓ.ም  ጀምሮ እየደወልን እንቀበላለን።


የሒሳብ ትምህርት ውድድር አሸናፊዎች 2016 ዓ.ም

የሒሳብ ትምህርት ውድድር አሸናፊ ተሸላሚዎች ከዚህ በፊት በቴሌግራም ላይ በተለቀቀው መሠረት ሽልማታችሁ ገቢ ይደረጋል።

ገቢ የሚደረግበት አካውንት ከየካቲት 25/2017 ዓ.ም ጀምሮ እየደወልን እንቀበላለን።


ሰበር ዜና

ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ የአለም ሪከርድ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሊያስመዘግብ ቅድመ ዝግጅቶችን አጠናቀቀ።

በምን ይመስላቹል ሪከርድ የምንይዘው?


አንድ ደቂቃ መፅሀፍ የምትታተምበት የቋንቋ አይነቶች
1. አማርኛ
2.ኦሮምኛ
3. ትግርኛ
4. ሱማሌኛ
5. ወላይትኛ
6. ስልጤኛ
7. እንግሊዘኛ

በሌሎች የሀገራችን ቋንቋዎች በቅርቡ እናሳውቃለን።


አንድ ደቂቃ መፅሀፍ

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የምትታተመው አንድ ደቂቃ መፅሀፍ ሚያዚያ 1/ 2017ዓ.ም ብቻ በሁሉም የሀገራችን ክፍሎችና መስተዳደሮች
በተለያዩ የሀገራችን ቋንቋ ታትማ ለተማሪዎች
በነፃ ትታደላለች።

ተማሪዎች ከየካቲት እስከ መጋቢት ወር ብቻ በየትምህርት ቤታቸው ይመዘገባሉ።

ሚያዚያ 1/2017 መፅሀፉ ይሰጣቸዋል።

ሚያዚያ እና ግንቦት መፅሀፉን ያነባሉ ይለማመዳሉ።

በሰኔ ወር ሁለት ፈተናዎች ይፈተናሉ።

በሐምሌ መጨረሻ ለከፍተኛ ሽልማት ይወዳደራሉ።

መፅሀፉ ከ3 እስከ 8 ክፍል ብቻ ነው የሚያገለግለው።

ዝርዝር መረጃ በየትምህርት ቤታችሁ ይመጣል።


ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ

መልካም የጥምቀት በዓል ይመኛል።

         "ጉብዝና ያሸልማል"


100,000 ተማሪዎች

በኢትዮጵያ ብቸኛ የሆነው ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ የአባከስ ስልጠና የተጀመረበትን 10ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ
በሀገራችን 100,000 ተማሪዎችን በነፃ የአባከስ ስልጠና
ሊያሰለጥን ነው።

ለሁሉም ሰልጣኝ ተማሪዎች በነፆ 100,000 አባከሶች ይሰጣል።

"ጉብዝና ያሸልማል"


ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ

መልካም የገና በዓል ይመኛል።

"ጉብዝና ያሸልማል"


ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የአባከስ ስልጠና በትምህርት ቤት ደረጃ መሠጠት የተጀመረበትን 10ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በመላው ሀገሪቱ 10,000 የሒሳብ መምህራንን የአባከስ ስልጠና በነፃ መስጠት ተጀመረ።

"ጉብዝና ያሸልማል"


እንኳን አደረሳችሁ

ነገ ህዳር 29/2017ዓ.ም በአርባ ምንጭ ከተማ በድምቀት ለሚከበረው ለ19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ ብቸኛው ሀገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት አወዳዳሪ እና አባከስ አሰልጣኝ።


በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚጀመረው የ1% ውድድር ።

አጭር መረጃ

1. ውድድሩ የሒሳብ ትምህርት ውድድር ብቻ ነው።

2. ጥያቄዎቹ አጭር መልስ ብቻ ናቸው።
ምንም ምርጫ ጥያቄ የለም።

3. በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ምንም ማጣሪያ ውድድር የለም።

4. በውድድሩ የሚሳተፍ የተማሪ ብዛት በአንድ ከተማ 10 ተማሪ ብቻ ነው።

5.በውድድሩ ላይ የተመዘገበ ተማሪ ለሽልማት ውድድር ብቻ ነው የሚፈተነው።

6.ለተመዘገብ ተማሪዎች በየወሩ መለማመጃ ጥያቄ ይላክላቸዋል።

7. በሐምሌ ወር በዩኒቨርስቲ መምህራን የማጠናከሪያ ትምህርት ይሰጣቸዋል።

8. መመዝገቢያው ውድ ነው።

9. ሽልማቱ ከፍተኛ ነው።

ተጨማሪ መረጃ በቅርብ ይጠብቁ።


በሀገራችን ኢትዮጵያ የአባከስ ስልጠናና ውድድር የተጀመረበትን 10ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ

ከፍተኛ ሽልማት የሚያስገኝ 6 ዙር ያለው በቴሌግራም የሚከናወን የሱዱኩ ውድድር ህዳር 20/2017ዓ.ም ይጀምራል።

ሁላችሁም ተጋብዛቹሀል።

ዝርዝር መረጃ ህዳር 20/2017ዓ.ም ይለቀቃል።


ሱዱኩ ምንድነው ?

ጥቅሙስ ?

እነማን ይወዳደሩታል?

ውድድሩ እንዴት ነው የሚከናወነው?

ሽልማቱ ምንድነው?

የነዚህ መልሶች ህዳር 20/2017 ይቀርባሉ




ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ
በዶ/ር ግሩም ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ከፍተኛ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቹ እና ለስራ ባልደረቦቹ መፅናናትን ይመኛል።

20 last posts shown.