የኔ መሃሪ | ዘማሪ ገ/አምላክ ደሳለኝ
የኔ መሀሪ ሁሉን መርሻዬ /2/
እንደ ህልም አልፏል ትናንትናዬ ባንተ ጌታዬ
አዳፋው ልብሴ ከነፃ
ከእዳ ከፈታኝ በነፃ
የፅድቁ ባሪያ ሆኛለው
ሳገለግለው ኖራለው
የእንባ ዘለላን ያቀፈው
አይኔም እልልታ ተረፈው
ደልዳዩ መዳፍ ደርሶሎኝ
ተራራው ሜዳ ሆነልኝ
አይኖቼን ከጉድ ጋርዶልኝ
ክንዶቼን በእጁ ይዞልኝ
ከእግሬ በታች ነው ወጀቡ
አሁን ታይቶኛል ወደቡ።
ሰላም ይነፍሳል ዙሪያዬ
እረፍት ሆኖልኝ ጌታዬ
የባረከኝን ባርኬ
ተለወጠልኝ ታሪኬ
ብርሃንህ ገፏል ድቅድቁን
በልቤ ተክሏል ሰንደቁን
ተቆጣጥሮኛል መውደዱ
መንገዴ ሆኗል መንገዱ
ያበቃው ነገር ቀጥሏል
ጭንቄ በሞቱ ተሰቅሏል
የኢየሱስ ሆኜ ምን አጣሁ
ሁሉን በስሙ ተወጣሁ
እንደኔ ማንን ታግሷል
ይቅርታ ፍቅሩን አልብሷል
ማይገባኝን አድርጎ
ያሳለፈልኝ ሸሽጎ
መልካም ነው ለኔስ መልካም
ፀጋው ያገዘኝ ስደክም
ሞትኩኝ ስል ምህረት ደርቦ
አቆመኝ በህይወት አስዉቦ
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All
የኔ መሀሪ ሁሉን መርሻዬ /2/
እንደ ህልም አልፏል ትናንትናዬ ባንተ ጌታዬ
አዝ
አዳፋው ልብሴ ከነፃ
ከእዳ ከፈታኝ በነፃ
የፅድቁ ባሪያ ሆኛለው
ሳገለግለው ኖራለው
የእንባ ዘለላን ያቀፈው
አይኔም እልልታ ተረፈው
ደልዳዩ መዳፍ ደርሶሎኝ
ተራራው ሜዳ ሆነልኝ
አዝ
አይኖቼን ከጉድ ጋርዶልኝ
ክንዶቼን በእጁ ይዞልኝ
ከእግሬ በታች ነው ወጀቡ
አሁን ታይቶኛል ወደቡ።
ሰላም ይነፍሳል ዙሪያዬ
እረፍት ሆኖልኝ ጌታዬ
የባረከኝን ባርኬ
ተለወጠልኝ ታሪኬ
አዝ
ብርሃንህ ገፏል ድቅድቁን
በልቤ ተክሏል ሰንደቁን
ተቆጣጥሮኛል መውደዱ
መንገዴ ሆኗል መንገዱ
ያበቃው ነገር ቀጥሏል
ጭንቄ በሞቱ ተሰቅሏል
የኢየሱስ ሆኜ ምን አጣሁ
ሁሉን በስሙ ተወጣሁ
አዝ
እንደኔ ማንን ታግሷል
ይቅርታ ፍቅሩን አልብሷል
ማይገባኝን አድርጎ
ያሳለፈልኝ ሸሽጎ
መልካም ነው ለኔስ መልካም
ፀጋው ያገዘኝ ስደክም
ሞትኩኝ ስል ምህረት ደርቦ
አቆመኝ በህይወት አስዉቦ
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All