ሕማማት ሰኞ [ መርገመ በለስ ]
በዚህ ዕለት ስለ ተፈጸመው ታሪክ ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ሲናገር ፡- "በነጋም ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ወደ ከተማ ሲመለስ ተራበ። በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ፤ ነገር ግን ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና፦ ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች።" /ማቴ 21÷18-20/ በማለት ጽፏል። በዚህ ክፍል ላይ "በለስ" የተባለችው ኃጢአት ናት። ኃጢአት እንደ በለስ ቅጠል ሰፍታ በዚህ ዓለም ላይ ሞላታ አገኛት አይቶም ረገማት ማለቱ ነው።
በለስ በኃጢአት መመሰሏ ስለ ሦስት ነገር ነው
1, አዳም ከገነት እንዲወጣ ምክንያት የሆነችሁ ዕፀ በለስ ናትና በኃጢአት ትመሰላለች።
2,የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነ የኃጢአት መንገድም ለመራመድ የተመቸና ሰፊ ነው መጨረሻው ግን ጥፋት ነው።
3, በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል ቆይቶ ግን ይመራል። ኃጢአትም ሲፈጽሙት ለጊዜው ስሜትን ያረካል ደስም ያሰኛል ፍጻሜው ግን ሞትና መከራ ያለበት መራራ ሕይወት ነው።
ጌታችን ስለ ናትናኤል ሲናገር "ፊልጶስ ሳይጠራህ በፊት ከበለስ በታች ሳለህ አውቅኸለው" /ዮሐ 1÷47/ ያለውን በማሰብ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን "ኃጢአት ሰርተህ ከበለስ ስር ተሸሽገህ ሳለህ አውቅሀለው" ማለቱ ነው ብለው ያሰተምራሉ። ናትናኤል ሰው ገድሎ በበለስ ስር ደብቆ ነበርና። ስለዚህ በለስን መርገሙ ኃጢአትን መርገሙ ነው ተብሎ ይፈታል።
📖 አንድ ሰዓት መዝ 72÷18
📖 ሦስት ሰዓት መዝ 122÷1
📖 ስድስት ሰዓት መዝ 121÷4
📖 ዘጠኝ ሰዓት መዝ 13÷2
📖 አሥራ አንድ ሰዓት መዝ 13÷2
"እንበለ ደዌ ወሕማም እንበላ ጻማ ወድካም ያብጸሐነ ያብጻሐይክሙ ለብርሐነ ትንሳኤ በፍስሐ ወበሠላም"

የዕለቱ ምስባክ
📖 አንድ ሰዓት መዝ 72÷18
📖 ሦስት ሰዓት መዝ 122÷1
📖 ስድስት ሰዓት መዝ 121÷4
📖 ዘጠኝ ሰዓት መዝ 13÷2
📖 አሥራ አንድ ሰዓት መዝ 13÷2
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )ሀሳብ አስተያየት ካለ @kingo08bot
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇
@Sebhwo_leamlakne
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏
🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊