Posts filter


10k channel መግዛት የሚፈልግ inbox @pilupadier


#አግኝቼሻለሁ_በጎልጎታ

አግኝቼሻለሁ በጎልጎታ አለሽ በፊቴ
በእግረ መስቀሉ ስታነቢ ድንግል እናቴ
አይረሳኝም ያነ እለት አስታውሳለሁ
ልጅሽ ተሰቅሎ አንች አልቅሰሽ እኔስ አምናለሁ(2)
አዝ


በኤፍራታ በምድረ ይሁዳ
ታቅፈሽው ታላቁን እንግዳ
በያውግስጦስ ቄሳር ትእዛዝ
ህዝቡም ሲቆጠር በጀርባሽ ላይ ስየዋለሁ የአምላኬን ፍቅር

ከሁሉም የበለጠ ከቦሁት ህሊናዬ
የቀራኒ ትዝታ አይጠፋም ከአእምሮዬ የቀራኑ ትዝታ(2)          
አዝ

ሰብአ ሰገል ከምስራቅ የመጡ
በአስተብርኮ እጅ መንሻ  ሰጡ
ለክህነቱ ለመንግስቱ ለምቱ የሚሆን
በልቦናሽ  አንዱ ደስታ አንዱ ልብ የሃዘን

ከሁሉም የበለጠ  ከትቦት ህሊና   የቀራኒዮ ትዝታ አይጠፋም ከአእምሮዬ(2             
አዝ

ከሄሮድስም አስከፊ ጭከና
ልታተርፊው ተሰደሻልና
በበርሃ ወንበዲዎች ይገሉታል ብለሽ
ስታለቅሺ አይቻለሁ በእንቫ ታጥቦ ገጽሽ
    
ከሁሉም የበለጠ  ከትቦት ህሊና   የቀራኒዮ ትዝታ አይጠፋም ከአእምሮዬ(2    
አዝ

ጽሃፍትና ፈሪሳዊያኑ
በዘመኑ እርሱን ሲፈትኑ
ያለበደል በመስቀል ላይ
በሰቀሉት ጊዜ አገኘሁሽ
ተሰጥተሽኝ ሳለሽ በትካዜ

ከሁሉም የበለጠ  ከትቦት ህሊና   የቀራኒዮ ትዝታ አይጠፋምከአእምሮዬ(2


ዘማሪ ሮቤል ማቲያስ



እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@Sebhwo_leamlakne
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊
ሀሳብ አስተያየት ካለ @kingo08bot


ክርስቶስ ሊያዝ በነበረበት ወቅት የቀኝ ጆሮው የተቆረጠው ወታደር ስሙ ማን ነበር?የቆረጠዉስ ማን ነበር?
Poll
  •   ሌንጌኒዮስ በጴጥሮስ
  •   ቀያፋ በዮሐንስ
  •   ማልኮስ በጴጥሮስ
  •   ዳክርስ በጴጥሮስ
49 votes


[ ሐዋርያው ፊልጶስ፣ አቡነ ዮስጣጤዎስ፣ ቅዱስማርያዕቆብ፣ሰማዕቱ ሮማኖስ፣ ሊቁ ቅዱስ አባ ዳንኤል፣ አቡነአኖርዮስ፣ማዕቀበ አልፋ]

አክብረን እና አስበን እንውላለን።
#ዕለት:- ረቡዕ
#ቀን:- ሚያዝያ ፲፰ ፳፻፲፯ ዓ.ም


እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@Sebhwo_leamlakne
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊

ሀሳብ አስተያየት ካለ @kingo08bot


Forward from: ነይ ነይ እምዬ ማርያም መዝሙሮች
የሚሸጥ አዲስ ክራር🪕🪕

📍አዲስ እና ለአገልግሎት በጣም የሚፈለግ ክራር ነው።

📍 በጣም አሪፍ ድምፅ አለው።

📌ዋጋ:- 4000 ✅3500 ብር

📞ስልክ:-0960723309

📲በቴሌግራም @Ale_0960_09


#ጌታ_ተነስቷል

ጌታ ተነስቷል እልል እልል በሉ
አምላክ ተነስቷል የምስራች በሉ
ሙስና መቃብር በኃይሉ አጥፍቶ
ሁላችን አየነው ክርስቶስ ተነስቶ
አዝ

አዳምን ለማዳን ቃልኪዳን ገብቶለት
ዘመኑን ጠብቆ ካሳ ሊከፍልለት
ከሰማያት ወርዶ የተሰቀለው
ሞትን በሞት ሽሮ ይኸው አየነው
አዝ

ደቀ መዛሙርቱ እጅጉን ተጨንቀው
በጌታቸው መሞት በኀዘን ተመተው
በተዘጋ ደጃፍ ተሰብስበው ሳለ
እጆቹን ዘርግቶ ሰላም ለእናንተ አለ
አዝ

ማርያም መግደላዊት እየገሰገሰች
በለሊት ተነስታ ወደ አምላኳ ሄደች
አይሁድ አንገላተው የሰቀሉት ጌታ
ተነስቶ አግኝታው ተመላች በደስታ

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@Sebhwo_leamlakne
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊
ሀሳብ አስተያየት ካለ @kingo08bot


#ሂዱ_ንገሩ_አውሩ_ለአለም

ሂዱ ንገሩ አውሩ ለአለም
ተነሥቷል በዚህ የለም/2/ መድኃኔ አለም
ሞት የማይችለው የበረታ ኃያል ነው የማይረታ
ማኅተሙን የፈታ የትንሳኤው ጌታ

ገዳዩ ሞት በእርሱ ድል መንሳት ተዋጠና
ሰንሰለቴን ቀንበሬን ተካው በበገና
ሞት ሆይ መውጊያህ የታል እያልን እምንዘምረው
መስቀልህ ጦር ስምህ ጋሻችን ሆኖልን ነው
ዳንን የምንለው

ተሻግረናል ስላሻገርከን ለዘላለም
በመቃብር ሞት ይይዘህ ዘንድ ከቶ አልቻለም
ኃይለኛውን በኃይል አስረኸው ላይፈታ
መመርንልህ አሸናፊ ነህ የእኛ ጌታ
ከፍ በል በእልልታ

ማቶ ማዳን ለማን ተችሏል ካንተ በቀር
ጌትነትህ ስራህ ይኖራል ሲመሰከር
ወዳጄ ሆይ ውበትህ ውብ ነው የሚያበራ
ተጨነቀ ተንቀጠቀጠ ጥላት ፈራ
ዕጹብ ያንተ ስራ

መስክሩለት የምስራች ነው ታላቅ ዜና
መላዕክቱ ነጭ ለብሰዋል ድል ነውና
ከተማዋ አንዳች ሁናለች በሌሊቱ
በዝማሬ ተንቀጠቀጠ ወኅኒ ቤቱ
ከበረውን ምቱ

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@Sebhwo_leamlakne
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊
ሀሳብ አስተያየት ካለ @kingo08bot


ክርስቶስ ተንስአ እሙታን!
  በዐቢይ ኃይል ወስልጣን!
አሠሮ ለሰይጣን!
  አግዐዞ ለአዳም!
ሰላም!
  እምይእዜሰ!
ኮነ!
  ፍሥሐ ወሰላም!
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን❤❤


“ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።”

በእውነት ተስፋችን ክርስቶስ ኢየሱስ ተነሥቷልና ሀሴት አድርጉ.. እንኳን አደረሳችሁ ለዝች ቀንም

@Apostolic_Answer




#ኢየሱስ_ልበል ♡

ኢየሱስ ልበል ኢየሱስ እርሱ ነው ኅይወቴ
የምኖርበት ተስፋ እርሱ ነው እረፍቴ
ያለ ጌታ ብኖርማ እንዴት እኆናለሁ
ስለስሙ ብነቀፍም ነፍሴን እሰጣለሁ

በአይሁድ መንደር ስሄድ የቤቱ ቅናት በላኝ
ኢየሱስ የሚሉትን ስሙን አትጥራ ቢሉኝ
እንቢ ብያለሁ ያለ ፍቅሩ አልመላለስም
ያበራልኝ ይታየኛል እኔ አላፍርበትም

በሙሴ ወንበር ሳሉ ፀሃፍቱን ሳነጋግር
በኅጋቸው ኮነኑኝ ለጌታዬ ስዘምር
ከሰዎች ይልቅ ክርስቶስን መስማት ስላለብኝ
በመከራ ተከብቤ አዳኜን ፈለኩኝ

አላስደነገጠኝም የቄሳር ቀጭን ትእዛዝ
በምኩራብ ተፈልጌ በመሰዊያው ፊት ብያዝ
ልቤ አይክድም የተገዛው ለእውነት ነውና
ምንም አይኖር የሚያቆመኝ ከአምላኬ ምስጋና

ኢየሱስ በተአምር ሁሉን እየከወነ
በግንበኞች ከተማ ታላቅ ፍርሃት ሆነ
በየጥቂቱ እየበዛ ቃሉ እያደገ
በተፈታ አንደበቴ ምርኮውን ፈለገ

            
  ገብረ-ዮሐንስ ገብረ-ጻድቅ

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@Sebhwo_leamlakne
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊
ሀሳብ አስተያየት ካለ @kingo08bot


#ዝቅ_ብዬ_ላመስግነው ♡


ዝቅ ብዬ ላመስግነው
ጉልበቴ ነው ላወድሰው
የፍቅሩ እሳት ልቤን ነክቷል
የድል ዜማ በአፌ ሞልቷል
  
ምን አገኘህ ሰው ይለኛል
ላያኖረኝ ይጨነቃል
መኖርያዬ በሰማይ
አባት አለኝ ኤልሻዳይ
አባት ና ንጉስ ጌታ ቅዱስ ለነብስ
ህይወቴ ነው ክርስቶስ

ተራመድኩኝ በጉልበቴ
ስላቆመኝ ደጉ አባቴ
እሩቅ አይደል ቅርቤ ላለው
ምስጋናዬ ለእርሱ ይድረሰው
አባትና ንጉስ......
 
የከበረ የተፈራ
ምህረት ያለው የሚራራ
ያገኘኝን አይቻለው
ሞት አያየኝ ፊቱ እያለው
አባት ና ንጉስ.........
 
ርህራሄው ስላኖረኝ
ከሰው ድንኳን ምን ትርፍ አለኝ
የኔስ ጌታ ያስደንቃል
በልቤ ላይ ቤቱን ሰርቷል
  አባት ና ንጉስ.........

    ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@Sebhwo_leamlakne
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊
ሀሳብ አስተያየት ካለ @kingo08bot


✞ #ተናገር_አለኝ ✞

ተናገር አለኝ መስክር
ተናገር አለኝ ዘምር
ለቀራንዮ ውለታ አርምሞ የለም ዝምታ
ለመድኃኔዓለም ውለታ አርምሞ የለም ዝምታ

ሰው አድርጎኝ ሞቶ በደሙ
ኑሮዬን ባርኮት ሕመሙ
ሰላም አውጥቶ ካስገባ
ልያዝ ለክብሩ ዘንባባ
ሆሳዕና ልበል መድኃኒት
ከፍ በልልኝ የኔ አባት
ተጠምተኸ እኔ ረካሁ
ስራህ ግሩም ነው ደነቀኝ

        /አዝ=====

እጆቹን እዩት በእምነት
ቆሰለ ሊሰጠኝ ሕይወት
በዚያ ታትሞ ውበቴ
እየሱስ ለኔ ብርታቴ
ከማንም በላይ ከምንም
ለኔ ልዩ ነው ዘላለም
ሕይወቴን ለእርሱ አስማርኬ
እኔስ በረታሁ በአምላኬ

        /አዝ=====

የእሾህ አክሊሉ በራሱ
ለእኔ ቤዛ ነው ሞገሱ
ሞቴን ገድሎታል አባቴ
ሰላሜ እርሱ ነው እረፍቴ
ሰው የመሆኔ ምስጢሩ
የማይለወጥ ነው ፍቅሩ
የገባኝ እውነት በምድር ላይ
ፍቅር ነው ጌታ ኤልሻዳይ

        /አዝ=====

ክብሩን ለማወጅ ተነሳሁ
ሲያድነኝ ከሞት እያየሁ
ገመና ሸፋኝ ኪዳኔ
ተራበ ውዴ መድኃኔ
ይሄ ነው የቆመኝ በፊቱ
ወሰን የሌለው ምሕረቱ
ለዚህ ደግነት ውለታ
ምን ይከፈላል ለጌታ


ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ



እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@Sebhwo_leamlakne
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊
ሀሳብ አስተያየት ካለ @kingo08bot


#ቅዱስ_እግዚአብሔር

የማይሞት የማይለወጥ
ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደ
ከሥጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ የተዋሃደ
የሰው ልጅ ነዉ በምድር የተመላለሰ
አምላክም ነዉ በደልን የደመሰሰ

ቅዱስ እግዚአብሔር
ቅዱስ ሃያል
ቅዱስ ሕያው ዘይመውት


የማይሞት የማይለወጥ
በማዕዶተ ዮርዳኖስ የተጠመቀ
የተቀበረውን የዕዳ ደብዳቤ ወዶ የፋቀ
በእፀ መስቀል ቤዛ መድሃኒት የሆነ
በይቅርታ በምህረት የተለመነ

ቅዱስ እግዚአብሔር
ቅዱስ ሃያል
ቅዱስ ሕያው ዘይመውት
የማይሞት የማይለወጥ
በሶስተኛው ቀን ተነስቶ ሞትን የሻረ
ወደ አባቱ ቀኝ በኃይል ያረገ የተከበረ
በምስጋና ዳግም ለፍርድ የሚመጣው
አምላካችን ከሃሊ ስሙም ቅዱስ ነዉ

ቅዱስ እግዚአብሔር
ቅዱስ ሃያል
ቅዱስ ሕያው ዘይመውት

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@Sebhwo_leamlakne
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊
ሀሳብ አስተያየት ካለ @kingo08bot


የትምህርት ቀን
በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪።


ማክሰኞ(የትምህርት እና የጥያቄ ቀን)

በመ/ር ኃይለ ማርያም ላቀው

-በማቴዎስ ወንጌል ፳፩፥፳፰፤ ፳፭፥፵፮፤
-በማርቆስ ወንጌል ፲፪፥፲፪፤ ፲፫፥፴፯፤
-በሉቃስ ወንጌል ፳፥፱፤ ፳፩፥፴፰ የሚገኙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ማክሰኞ ዕለት የሚነገሩ ትምህርቶችን ይዘዋል፡፡ በዚህ ዕለት ጌታችን በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ ዕለቱ የትምህርት ቀን› ይባላል፡፡ ክርስቲያን የኾነ ዅሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ በዚህ ሰሞን የሃይማኖት ትምህርት ሲማር፣ ሲጠይቅ መሰንበቱ መጽሐፋዊ ሥርዓት ነው፡፡

በዚህ ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሥልጣኑ ተጠይቋል፡፡ ጠያቂዎቹ የካህናት አለቆችና የሕዝብ አለቆች ሲኾኑ፣ ጥያቄውም፡-

‹‹በማን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን የሰጠህ ማነው?›› የሚል ነበር፡፡ ይህ ጥያቄ ጌታችን ሰኞ ዕለት ሁለት ነገሮችን ማከናወኑን ተከትሎ የተነሣ ጥያቄ ነው፡፡ ይኸውም ጌታችን ሲያደርጋቸው የነበሩ ተአምራትና ድንቅ ድንቅ ሥራዎች የካህናት አለቆችን ስላስቀኗቸው ጌታችንን ከሮማ መንግሥት ባለ ሥልጣናት ጋር ለማጋጨት የቀየሱት ስልት ነው፡፡ ጌታችን በቤተ መቅደስ የነበሩትን ነጋዴዎችን አባሯል፤ መደባቸውን ገለባብጧል፡፡ ነጋዴን ማባረርና መደብን ማስለቀቅ መንግሥታዊ ሥራ ነው፡፡ ጌታችን ‹‹በራሴ ሥልጣን›› ቢላቸው ፀረ መንግሥት አቋም አለው በማለት ከሮማ መንግሥት ዘንድ ለማሳጣት ነበር ዕቅዳቸው፡፡
ጌታችን ግን የፈሪሳውያንን ጠማማ አሳብ ስለሚያውቅ ‹‹የዮሐንስ ጥምቀት ከየት ነው? ከሰማይ ነው ወይስ ከምድር?›› ሲል ጠይቋቸዋል፡፡ ጌታችን ፈሪሳውያን ላቀረቡለት ጥያቄ ቀጥተኛ ምላሽ አልሰጠም፡፡ ምክንያቱም ጥያቄው ለከሳሾቹ ዓላማ መሳካት አመቺ ኹኔታን ስለሚፈጥር ጥያቄውን በጥያቄ መልሶላቸዋል፡፡

እነርሱም ‹‹ከሰማይ ነው›› ቢሉት ‹‹ለምን አላመናችሁበትም?›› እንዳይላቸው፤ ‹‹ከሰው ነው›› ቢሉት ደግሞ ሕዝቡ ዮሐንስን እንደ አባት ይፈሩት፣ እንደ መምህር ያከብሩት ነበርና ሕዝቡ እንዳይጣሏቸው ስለፈሩ ‹‹ከወዴት እንደ ኾነ አናውቅም›› ብለው መለሱለት፡፡ እርሱም ‹‹እኔም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ አልነግራችሁም›› አላቸው፡፡ ይህን ጥያቄ መጠየቃቸውም እርሱ የሚያደርጋቸውን ተግባራት ዅሉ በራሱ ሥልጣን እንዲያደርግ አጥተውት አልነበረም፤ ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ ነበር እንጂ፡፡
ዛሬም ቢኾን መልካም ሥራን በሠራን ጊዜ ከልዩ ልዩ ወገኖች የሚመጡ ፈተናዎች ለመልካም ሥራችን እንቅፋት ሊኾኑ እንደሚችሉ መገንዘብ አለብን ብዙ ወገኖች ‹‹ለቅን አሳባችን ለምን ሰዎች ክፉ ነገር ይመልሱልናል?›› በማለት ሲጠይቁ ይሰማል፡፡ ለቅን አሳባችን ከዓለም ዘንድ ተቃራኒ ነገር እንደሚጠብቀን ለመረዳት ‹‹ዓለም የሚወደው የገዛ ወገኑን ነው›› የሚለውን የጌታችንን ትምህርት ልብ ይሏል፡፡ በዘመናችን አሳልፈው ሊሰጡን የሚፈልጉ ሰዎች ፈታኝ ጥያቄ እንደሚያቀርቡልንም ከወዲሁ ልንገነዘብ ይገባል፡፡


ይማሩበት ዘንድ ለተዋህዶ ልጆች #ሼር ያድርጉ
          ወስብሐት ለእግዚአብሔር
          ✝✝


ሕማማት ሰኞ [ መርገመ በለስ ]

"እንበለ ደዌ ወሕማም እንበላ ጻማ ወድካም ያብጸሐነ ያብጻሐይክሙ ለብርሐነ ትንሳኤ በፍስሐ ወበሠላም"

በዚህ ዕለት ስለ ተፈጸመው ታሪክ ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ሲናገር ፡- "በነጋም ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ወደ ከተማ ሲመለስ ተራበ። በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ፤ ነገር ግን ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና፦ ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች።" /ማቴ 21÷18-20/ በማለት ጽፏል። በዚህ ክፍል ላይ "በለስ" የተባለችው ኃጢአት ናት። ኃጢአት እንደ በለስ ቅጠል ሰፍታ በዚህ ዓለም ላይ ሞላታ አገኛት አይቶም ረገማት ማለቱ ነው።

በለስ በኃጢአት መመሰሏ ስለ ሦስት ነገር ነው

1, አዳም ከገነት እንዲወጣ ምክንያት የሆነችሁ ዕፀ በለስ ናትና በኃጢአት ትመሰላለች።
2,የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነ የኃጢአት መንገድም ለመራመድ የተመቸና ሰፊ ነው መጨረሻው ግን ጥፋት ነው።
3, በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል ቆይቶ ግን ይመራል። ኃጢአትም ሲፈጽሙት ለጊዜው ስሜትን ያረካል ደስም ያሰኛል ፍጻሜው ግን ሞትና መከራ ያለበት መራራ ሕይወት ነው።

ጌታችን ስለ ናትናኤል ሲናገር "ፊልጶስ ሳይጠራህ በፊት ከበለስ በታች ሳለህ አውቅኸለው" /ዮሐ 1÷47/ ያለውን በማሰብ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን "ኃጢአት ሰርተህ ከበለስ ስር ተሸሽገህ ሳለህ አውቅሀለው" ማለቱ ነው ብለው ያሰተምራሉ። ናትናኤል ሰው ገድሎ በበለስ ስር ደብቆ ነበርና። ስለዚህ በለስን መርገሙ ኃጢአትን መርገሙ ነው ተብሎ ይፈታል።

የዕለቱ ምስባክ


📖 አንድ ሰዓት መዝ 72÷18
📖 ሦስት ሰዓት መዝ 122÷1
📖 ስድስት ሰዓት መዝ 121÷4
📖 ዘጠኝ ሰዓት መዝ 13÷2
📖 አሥራ አንድ ሰዓት መዝ 13÷2


እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@Sebhwo_leamlakne
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊
ሀሳብ አስተያየት ካለ @kingo08bot


🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁

እንኳን #ለክርቲያናዊ_ነጋዴ ሲያርፋ ሁለት አንበሶች የቀበሩትና የላከው አርባ ልጥረ ወርቅ መብዓ ከሰማይ በክብር ወርዶ ራሱ ጌታችን በእጁ ለተቀበለው #ለቅዱስ_መርቄ ለዕረፍት በዓል፣ ለኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ #ለአባ_ዮሐንስ ለዕረፍት በዓልና #ለእስክንድርያ_ሰባ_አንደኛ_ሊቀ_ጳጳሳት_ለአባ_ሚካኤል ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር በሰላምና በጤና አደረሰን።

@sebhwo_leamlakne

🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁


ሚያዝያ ፫ /3/


በዚች ቀን የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ የከበረ አባት አባ ዮሐንስ አረፈ።የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ የኦሪት ምሁራን የሆኑ አዋቂዎች ነበሩ የኦሪትን ሕግ ትምህርቶችንም እያስተማሩት አሳደጉት።

ክርስቲያኖችን በጸና ልቡና የሚከራከራቸውና የሚጣላቸው ነበር መጻሕፍትን አዘውትሮ ከመመርመሩ የተነሣ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዓለም እንደመጣና ሰውም እንደሆነ በሞቱም ዓለምን እንደአደነ አመነ።

እርሱም የባሕርይ አምላክ እንደሆነ አምኖ በኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ በአባ ዮስጦስ እጅ ተጠመቀ ዲቁናም ሾመው ከዚያም በኢየሩሳሌም ሀገር ኤጲስቆጶስነት ለመሾም እስቲገባው ድረስ በበጎ ሥራና በዕውቀት አደገ።

በዚህም አባት ላይ ከአሕዛብ ታላቅ መከራና በምድር ላይም ጐትተውታልና አጐሳቁለውታልና እርሱም ነፍሱን ወደርሱ ይቀበል ዘንድ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመነው ጌታም ልመናውን ሰምቶ በሰላም አረፈ ። በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@sebhwo_leamlakne

🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋


#አንተ_ብቻ_ንጉስ

አንተ ብቻ ንጉስ አንተ ብቻ ዳኛ (2)
ተመስገን ኢየሱስ የነብሴ መጽናኛ

አዝ
ሰለ ፍቅር ሁሌ ባነባ
ላፈስልህ የቅኔ መባ
ላንተ ቅኔ አይሁንም ካሳ
እስከ ሽበት ስምክን ባነሳ
ላንተ ቅኔ አይሁንም ካሳ
እስከ እድሜ ልኬ ስምክን ባነሳ

አዝ

ያሰተማረከኝ የውዴን ፊደል
የተከልከው የልቤን ወደል
እያነቃኝ አመልክሃለሁ
ካንተ ወዲያ ማንን አውቃለሁ (2)

አዝ
ሰውነቴ  ከግፍ እንዲጸዳ
ህሊናዬን አንተን ቢረዳ
ተጸየፈ የሰውን ምኩዝ
ስታበራ በልቤ መቅረዝ(2)

አዝ

ከእንቅብ በታች እጄን አፀናሁ
በተራራ እግሬን አፀናሁ
መገዛቴ ለፍቅር ቀንበር
ሰው አረገኝ አንስቶ ከአፈር

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@Sebhwo_leamlakne
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊
ሀሳብ አስተያየት ካለ @kingo08bot

20 last posts shown.