ከሸዋሮቢት ከተማ ወደ ደብረብርሃን አመራር አጅቦ ሲንቀሳቀስ የነበረ የአድማ ብተናና መከላከያ ሠራዊት ተደመሠሠ!
አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
የካቲት 2/2017 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ መሃመድ ቢሆነኝ ኮር አስቻለው ደሴ ክፋለጦር 4ኛ ሻለቃ ከሸዋሮቢት ወደ ደብረብርሃን የብልፅግና ከፍተኛ አመራሮችን አጅቦ ሲንቀሳቀስ በነበረ በጠላት ፓትሮል ላይ የደፈጣ እርምጃ በመውሰድ የጠላት ሀይልን ደምስሶታል። አመራሮቹን በ6 ፓትሮል አጅቦ ዲሽቃና ዙ-23 ያጠመደው የጠላት ሃይል ከሸዋሮቢት ከተማ ሳይርቅ ልዩ ቦታው ፍርፍር በተባለ ቦታ የአርበኛ መከታው ቀኝ እጆች በደፈጣ ጠብቀው አርግፈውታል።
በሌላ ግንባር የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአፄ አምደ ጽዮን ኮር 7ለ70 ክፍለ ጦር የኦሮሞ ብሄረሰብን ምሽግ አድርጎ ከሚነሳው የጠላት ሀይል ጋር ገጥሞ ከፍተኛ ድል ተቀዳጅቷል። የጠላት ቡድን ሀይሉን አሰባስቦ ውጊያ ቢክፍትም የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ስር የሚገኘው 7ለ70 ክፍለ ጦር በተለያየ አቅጣጫ የጠላትን ሃይል በመግጠም ከፍተኛ ኪሳራ አድርሶበታል። በዚህ ቀጠና በአውደ ውጊያ የተመታው የብልፅግና ሠራዊት በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ውስጥ ከተደበቀው ከሸኔ ጋር በጥምረት ውጊያ የከፈተ ቢሆንም በተባበረ ክንድ በአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አናብስቶችና የጦር ጠበብቶች እየተደቆሰ ይገኛል።
ድል ለአማራ ፋኖ
አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
@Showapress