ሚዲያ ውስጥ አጀንዳ ፍሬሚንግ ወሳኝ ዘርፍ ነው። የተነሳህለትን አላማ በሚገባ ወደ ተከታይህ ለማስረጽ ከቃላት ጀምሮ እስከ ርዕሰ ጉዳይ በጥንቃቄ የምትመርጥበት መንገድ ነው። በሀገራችን ቋንቋ ከሚሰራጩ ሚዲያዎች ውስጥ የቢቢሲን አላማና የትኩረት ነጥብ ብዙ ሰው ያውቀዋል። ከስሙ ጀምሮ ብዙም ከማይለዩ አፍቃሬ ጽዮናውያን ሚዲያዎች መካከል ግን አል አይንን የሚወዳደር ያለ አይመስለኝም።
በሙስሊሙ አለም ዙሪያ የኢማራት አቋምና አላማ የሚታወቅ ቢሆንም ብዙውን ጊዜ ለተዛቡት መረጃዎች ግን በየሀገሩ ያሉ የተቀጣሪ ሰራተኞችን የግል እምነትና አመለካከትን ምክንያት ማድረግ እመርጥ ነበር። ዜናዎችን የመምረጥ፣ አጀንዳዎችን ፍሬም ማድረግ፣ ለዘገባ የሚወሰነውን የቃላት አጠቃቀም ወዘተ የሚዲያው ፖሊስ እንዳለ ሁኖ የሰራተኞችም የግል ፍላጎት ሊንጸባረቅበት ይችላል።
የጋዛው ኹነት ግን ከብዙው ሚዲያ ጀርባ ያለውን ፍላጎትና ማንነት ፍንትው አድርጎ አሳይቶናል። ከግለሰቦቹ የግል አመለካከት በተጨማሪ እንደ ሚዲያ የቆመለትን አላማም ጭምር ይኸው መሆኑን ብዙ ሰው የተረዳ ይመስለኛል። ሚዲያዎቹ ሜንትስሪምና በብዙ በጀት የሚደጎሙ ቢሆንም እድሜ ለማኅበራዊ ሚዲያው በጥቂት አቅም የሚሰሩ ተኣማኒ ሚዲያዎች ተቀራራቢ ተደራሽነትን በመፍጠር እኩይ አላማቸውን ማሳየት ችለዋል። ዛሬ ትላንት አይደለም..!
⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe