ተመስጦ (meditation)
ብዙ ሰው ከራሱ ጋር የግል ጊዜ ስለማይወስድ ሂወቱ የተረጋጋ አይደለም!
የሰው ልጅ ዕለት ተዕለት በሚኖረው ኑሮ ውስጥ ሲደክመው ዕረፍት ማድረግን ፤ የሰውነት ክፍሎቹን ለማፍታታት መንጠራራትንና ማፍታታትን ፤ የድብርት ስሜት ሲሰማው ማፋሸግንና ሲጨንቀው ስሜቱን ለማረጋጋት ዓየር በደንብ ወደ ውስጥ አስገብቶና ወደ ውጭ በረጅሙ መተንፈስን በተፈጥሮ የታደላቸው ገጸ በረከቶች ናቸው፡፡ ከፍ ሲልም መንፈሱን ወደ ትልቁ ማማ ሰማየ ሰማይ በመውሰድና በመመሰጥ አእምሮውንና መንፈሱን ያድስበታል፡፡
ተመስጦ ሰዎች ከጥንት ጊዜ ጀምሮ አእምሯቸውንና ህይወታቸውን የሚቆጣጠሩበት እንዲሁም እራሳቸውን ፈልገው የሚያገኙበት የአእምሮ ፤የአካልና የመንፈስ እንቅስቃሴ ነው፡፡ በተጨማሪም ተመስጦ ሰዎች አእምሯቸውን እንደ ኤሌክትሪክ ማብሪያና ማጥፊያ ባሻቸው ሰዓት ማሰብ የሚፈልጉትን እንዲያስቡ ማሰብ የማይፈልጉትን ደግሞ ከአእምሮአቸው ውስጥ በቀላሉ የሚያጠፉበት ተፈጥሯዊ የአእምሮ ቁልፍ ነው፡፡
በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ በዓለም ላይ በሚገኙ ባህሎች ውስጥ ተመስጦና መመሰጥ አለ፡፡ ነገር ግን ተመስጦ በተደራጀና በተዋቀረ መልኩ የተጀመረው በሂንዱ ሸለቆ ውስጥ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ5000 እስከ 3500 ዓመተ ዓለም አካባቢ መሆንኑን የአርኪዮሎጂ ጥናቶችና ግኝቶች ያስረዳሉ፡፡ በሂንዱ ሸለቆች የተገኙ የግርግዳ ላይ ስዕሎች ከላይ ከተጠቀሰው ዓመተ ዓለም ጀምሮ ሰዎች ቁጭ ብለው እግራቸውን አመሳቀለው ተመስጦን ሲያከናውኑ እንደነበር ማስረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ እንዲሁም በህንድ መጻሕፍት ውስጥ ከ3000 ዓመታት በፊት የተመስጦና መመሰጥ ዘዴዎች ተመዝግበው እንደሚገኙ የታሪክ ድርሳናት ያሳያሉ፡፡
ሁሉም ሃይማኖታዊ ክንዋኔዎች በውስጣቻው ተመስጦን ይዘው ይገኛሉ፡፡ በሃይማኖታዊ ስርዓት ምዕመናን ሲጸልዩ ፤ ሲያመሰግኑና ሲሰግዱ ወደ አምላካቸው ይመሰጣሉ፡፡ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ ስለተመስጦና መመሰጥ ሲነሳ ሰዎች ወደ አእምሮአቸው የሚመጣው የቡድሃ ወይም የሂንዱ እምነት ነው፡፡ ምንም እንኳን እነኚህ ሃይማኖቶች በሃይማኖታዊ ክንዋኔአቸው ለተመስጦ ትልቅ ትኩረት ቢሰጡም በዘመናዊው እይታ ተመስጦና መመሰጥ ከየትኛውም ሃይማኖት ጋር አይያያዝም አልያም ዘውትር መመሰጥንና ተመስጦን ማከናወን የቡድሃ ወይም የሂንዱ እምነት ተከታይ መሆን ማለት አይደለም፡፡ ለመነሻ ያህል ይህን ካልን የመመሰጥና የተመስጦን ጥቅም ከብዙ በጥቂቱ እንመለከታለን
1.ውጥረትን ይቀንሳል
መመሰጥና ተመስጦ ከማንኛውም አካላዊ እንቅስቃሴ በላይ ውጥረትን የመቀነስ አቅሙ ከፍተኛ ነው፡፡ መመሰጥ ውጥረትን መቀነስ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በነርቭ ስርዓት ላይ ውጥረትን የሚያመጣውን ኮርቲሶል የሚባለውን ኬሚካል በመቀነስ በምትኩ ሰዎች ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው የሚያደርገውን ሴሮቶኒን የተባለውን ኬሚካል አንጎላችን እንዲያመነጭ ያነሳሳል፡፡
2.ጤናን ያሻሽላል
ተመስጦ የበሽታ መከላከል ኃይልን በማደርጀት፤ የደም ግፊትና የኮለስትሮል መጠንን በመቀነስ ጤናን ያሻሽላል፡፡ በተለይ በማይድን ጽኑ ህመም የሚሰቃዩ ሰዎች ህመማቸውን ለማስታገስና ለማገገም ከተመስጦ ብዙ ጥቅም ያገኛሉ፡፡ በእርግጥ ተመስጦን ለመጠቀም የግድ ጽኑ ህሙማን መሆን አይጠበቅብንም ከጉንፋንና እራስ ምታት ለመታቀብና ለመዳን ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡
3.ለእንቅልፍ
በስራ ጫና ብዛትና በውጥረት ምክንያት አንዳንድ ጊዜ ሰዎች እንቅልፍ ላይዛቸውና በቶሎ በመተኛት ከድካማቸው ፋታ ለማግኘት ይቸገራሉ፡፡ ይህ በሚሆንበት ወቅት መመሰጥት ችግራቸውን ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ በቀላል እንዲፈቱ ይረዳቸዋል፡፡
4.እርጅናን ይከላከላል
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት አዘውትረው የሚመሰጡ ሰዎች ከማይመሰጡት ጋር ሲወዳደሩ ቀናቸውን በተመስጦ የሚያሳልፉ ሰዎች ከዕድሜቸው አንጻር ቶሎ የማያረጁና ረጅም ዕድሜ የሚኖሩ ሆነው ተገኝተው፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት መመሰጥና ተመስጦ እርጅና የሚያስከትሉ ቲሹዎችንና በሽታዎችን መግታት በመቻሉ ነው፡፡
5. ለውስጠ ስሜት መረጋጋትና አወንታዊ አስተሳሰብ
መመሰጥ ጭንቀት ውስጥ ለገቡ፤ በቶሎ ለሚናደዱ፤ ስሜታቸውን መቆጣጠር ለሚቸገሩና ድብርት ለሚያጠቃቸው ሰዎች እንደ ተፈጥሯዊ መከላከያ መድኃኒት ተደርጎ በባለሙያዎች ይታዘዝላቸዋል፡፡ በተጨማሪም መመሰጥ የአሉታዊ አስተሳሰቦችንና ስሜቶችን ከሰዎች አእምሮና አካላት ውስጥ አጥርቶ በማውጣት በአወንታዊ አስተሳሰብ እንዲገነቡ ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡ በአጠቃላይ ከጭንቀትና ተያያዥ ጉዳዮች ባሻገር ተመስጦን የሚያዘወትሩ ሰዎች ጥሩ ስሜት የሚሰማቸውና ደስተኞች ናቸው፡፡
ለተመስጦ የሚረዱ ጥቆማዎች
.ዘውትርና በተመሳሳይ ሰዓት መመሰጥን ልምድ ማድረግ ይመከራል
.ከመመሰጥ በፊት የማነቃቃት ባህሪይ ያላቸውን ትኩስ ነገሮች አለመውሰድ
.ከምግብ በኋላ አለመመሰጥና በቀን ውስጥ ሙሉ ኃይል የለኝም ብለው በሚያስቡበት ሰዓት መመሰጥ
.መመሰጥ የሚፈልጉበትን ስፍራ ማዘጋጀትና በቂ ዓየር እንዲገባው መስኮት መክፈት
.በጣም ደማቅ ብርሃን የሌለውን ስፋራ መምረጥና ሰፋ ያለ ልብስ መልበስ
.ጸጥ ያለ አካባቢን መምረጥና በተመስጦ ጊዜ ሊረብሹ የሚችሉ ነገሮችን እንደ ስልክ ፤ ሬዲዮ ፤ ቴሌቪዥንና የመሳሰሉ ነገሮን ድምጽ ማጥፋት
.በረጅሙ ዓየር ወደ ውስጥ ማስገባት
.ያስገቡትን ዓየር ለጥቂት ሰከንዶች ሳይተነፍሱ ማቆየት
.ከዚያም በረጅሙ መተንፈስ
.በሚተነፍሱበት ወቅት ለሚሰማዎት ስሜት ትኩረት መስጠት፤ ዓየር በአፍንጫ ቀዳዳዎ ሲገባ ፤ ዓየሩን ለተወሰኑ ሰከንዶች ሲይዙት በመላ አካላቶ እየተሰራጨ እንደሆነና ሰውነቶን አዝናንቶ በአፍዎ እንደሚወጣ ማሰብ በቀላሉ የተረጋጋ ስሜትንና መዝናናትን አእምሮአችንና አካላችን እንዲሰማው ያደርጋል፡፡
@Zephilosophy