ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ፍልስፍና  እውነትን በመፈለግ- ሀሳዊ እምነቶችን በማጋለጥ እና ጭፍን አመለካከቶችን በጥበብ በመመርመር ወደ ላቀ አሰተሳሰብ ያሻግራል።
በዚህ ቻናል አለም ላይ ያሉ ፍልስፍናዎች ፤ ርዕዮት አለሞች ፤  ሀይማኖቶች እና አስተሳሰቦች በነፃነት ይዳሰሳሉ።

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


የመጀመሪያዋ ሴት "ሊልዝ"

የሔዋንን የሴት ቀዳሚነትነትን የማይቀበሉ ግለሰቦች ሊልዝ የሚልን ስም ሲያነሱ ይሰማል፡፡ ሊልዝ ከሔዋን በፊት የተፈጠረች ሴት ስትሆን፤ የአዳም የመጀመሪያዋ ሚስት ናትም ይሏታል፡፡ ሊልዝ ከሔዋን መቅደሟን በተመለከተ ከሚቀርቡት መከራከርያዎች መካከል ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር የሚነሳውን ለማንሳት ያህል፡ አንደኛው በዘፍጥረት መጽሐፍ 1፡27 ላይ የተቀመጠውን ትረካ የሚመለከት ነው፤ ይህ ክፍል ፈጣሪ ወንድ እና ሴትን በአንድ ጊዜ እንደፈጠረ የሚናገር ሲሆን በዚህ ክፍል ላይ ከአዳም ጋር በተመሳሳይ ጊዜ የተፈጠረቸዋ ሴት ሔዋን ሳትሆን ሊልዝ ናት የሚል ድምዳሜ ይነሳል፡፡ ሌላኛው የኢሳያስ መጽሐፍ 34፡14” ነው፤ በዚህ ላይም የተገለጸቹ ሊልዝ መሆኗ አከራካሪ ኢይደለም ይሉናል የሔዋን ቀዳሚት ሴትነትን የማይቀበሉት፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ባሻገር “Talmud”፣ “Kabbalah” እና “Alphabet of Ben Sira" ተብለው በሚጠሩ የሂብሪው መጽሐፍት ላይ ሊልዝ ስሟ በግልጽ ሰፍሮ ይገኛል፡፡እነዚህ መፅሀፎች የአዳም የመጀመሪያ ሚስት ሊሊዝ እንደሆነች፣ ኾኖም ከአዳም ጋር እኩል ነን አይደለንም በሚል ጭቅጭቅ ምክንያት እንደተለየችው ይተረካሉ፡፡

ሊልዝ ከገነት ከወጣች በኃላ የክፉ መናፍስት እናት በመሆን በሌሊት ህጻናት ገዳይ እና የሴሰኝነት ምንጭ ተደርጋ በአይሁዶች ዘንድ ዛሬም ድረስ ትወሰዳለች፡፡ በሌላ በኩል ስለ ሴቶች መብት እና እኩልነት አጥበቀው የሚከራከሩን ፌሚኒስቶች ሊልዝን የነጻነት እና የእኩልነት ምልክት አድርገው ይወስዷታል፡፡ ለዚህ ማሳያ በእስራኤል በሴቶች መብት እና እኩልነት ላይ ያተኮረ “Lilith” የሚል መጽሔት እንደሚገኝ መጥቀስ ይችላል፡፡ እንዲሁም ፌሚኒስት የሆኑ ጸሓፍት በዘፍጥረት መጽሐፍ ላይ ያለው የሰው አፈጣጠር ትረካ ዳግም መከለስ አለበት በማለት የተለያዩ ድርሳናትን ጽፈዋል፡፡ አብዛኞቹ መጽሐፍት የመጀመሪያዎቹ ሰዎች አፈጣጠር ትረካ መምስል ያለበት የሚሉት፦
"በመጀመሪያ እግዚአብሔር አዳም እና ሊልዝን ከአፈር አበጃቸው፡፡ የሕይወት እስትንፋስንም በአፍንጫቸው ተነፈሰባቸው፡፡ ሁለቱም ከተመሳሳይ ነገር ተፈጥረዋልና እኩል እና አቻ ነበሩ፡፡ እኩልነታቸውን ያልወደደው አዳም ታዲያ ወደ ፈጣሪ ቀርቦ ቅሬታውን አቀረበ፡፡ ፈጣሪም አዳምን ሰምቶ ሊልዝ አዳም እንደፈለገው የበታቹ እንድትሆን፣ ካለዚያ ከገነት እንደምትወጣ ነገራት፡፡ ሊልዝም ከአዳም በታች ከምትሆን ይልቅ  ከገነት መውጣትን መረጠች:: ፈጣሪም ይህን ባየ ጊዜ ለአዳም ሌላ ሴት መፍጠርን ወሰነ፡፡ ከአዳም ግራ ጎንም ሔዋንን ፈጠረ "
የሚል መልክ ያለው ነው::

@Zephilosophy

3.3k 0 46 109 78

በወንዶች አለም ውስጥ አንዲት ሴት

ዓለማየሁ ገላጋይ “መለያየት ሞት ነው”
በሚለው መፅሀፉ እንዲህ ይለናል

 "የአዲስ አበባ ወንድ የመልበሻ ቤት መስተዋት ሆኗል፡፡ ሴቶቹ በሱ ፊት ላይ አለባበሳቸውን ያያሉ፤ የአዲስ አበባ መንገዶች፣ ካፌዎች፣ ባሮች፣ ቢሮዎች፣ ሆቴሎች፣ የፀሎት ቤቶች … አለባበስ ማሳያ መድረኮች ሆነዋል፡፡
ወንዱ የጥሞና ጊዜ ተነፍጓል፡፡ ሲበላ፣ ሲጠጣ፣ ሲሰራ፣ ሲፀልይ፣ ታክሲ ሲጠብቅ … በሞዴሎች ተከቦ ነው፡፡ ህይወቱ የናይት ክለብ ውስጥ እስረኛ ሆናለች፡፡ ሲወለድ ሳውና ባዝ የገባ ሲሞት ይወጣል፡፡ ኑሮው በላብ መጠመቂያ ስፍራው ሆናለች፡፡ አይኑ ሸሽቶ የትም አይደርስም፡፡ እድሜ ልኩን መስክ መካከል እንደቆመ ሁሉ በአበባ ተሰላችቷል፡፡ …ትቢያ… ናፍቆታል፡፡
ሴቶች፤ የወንዶች አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት ሆነዋል፡፡ አይኑን ያገለግላሉ፣ ልቡን ያገለግላሉ፣ ስሜቱን ያገለግላሉ … የሴቶች የመጨረሻ አማራጭ … የወንዶች ገበያ .. እንደሚፈልገው ሆኖ መገኘት ነው። ህይወታቸው በወንዶች ህልም የተፈበረከ ነው፡፡ ከሰው የሚጠበቀው ከዘንድሮ ሴቶች አይገኝም፡፡ ወንድ የሚፈልገውን ግን አያጣም። አይኑ፣ ጆሮው፣ አፍንጫው፣ ምላሱ … በሴቶች ትጋት ሥር ተጠምዶ ተደናቅፏል፡፡ አንዲት ሴት ከአንዲት አበባ ጋር በንፅፅር ቆማለች፡፡ የወንድ ቀልብ እንደ ንብ ሲጠመድላት ከማየት ውጭ ሌላ ህልም የላትም፡፡
እንግሊዛዊው ደራሲ ዲ.ኤች ላውረንስ ይሄንን ታዝቦ አንዲት የመረረች መጣጥፍ አቅርቦ ነበር፡፡ “Give her a pattern” ይላል ርእሱ “The real trouble about women is that they must always go on trying to adapt themselves to men’s theories of women, as they always have done.” ብሏል፡፡ (የሴቶች ዋነኛ ችግር ወንዶች ስለሴቶች የሚኖራቸውን ፅንሰ ሃሳብ አሟልተው ለመገኘት ሁልጊዜም መጣራቸው ነው)
የዘንድሮ ሴቶች ሴት የመሆን መብት የላቸውም፤ ወንድ የሚፈልገው አይነት ሴት እንጂ፡፡ ሴቶች የወንዶችን ህልም ለመተርጎም ህይወታቸውን የሚሰዉ ጭዳዎች ናቸው። በመሰልጠን ስም እራሳቸውን ለፆታ ባርነት አጋልጠዋል፡፡ ኧረ እንዳውም ከባርነት ወርደው ለአሻንጉሊትነት ተዳርገዋል፡፡ ሁኔታውን “Living Doll” ይለዋል Cliff Richard የተባለ አቀንቀቃኝ፡፡ … ህያው አሻንጉሊት … እንደማለት ነው፡፡ “I got myself a sleeping, walking, crying, talking Doll” (እራሴን የምትተኛ፣ የምትሄድ፣ የምታለቅስ፣ የምታወራ አሻንጉሊት ሆኜ አገኘሁት) የዘንድሮ ሴቶች ሰው መሆናቸው የሚረጋገጠው ስለሚተኙ፣ ስለሚሄዱ፣ ስለሚያለቅሱና ስለሚያወሩ ብቻ ነው፡፡ እንደ አበባ … ንብ.. መጥራት የህይወት ትርጉማቸው ሆኗል፡፡  "

@Zephilosophy

4.9k 1 65 18 104

አስተዋይ መሪ ኋላ በአጠቃላይ ሕዝቡን ወይም ሀገሩን ሁሉ አጣብቂኝ ውስጥ ሊከትቱ የሚችሉ መዘዞችን ሁልጊዜ ገና ከመነሻቸው አሽትቶ ማወቅ የሚችል ነው። ይህ መዘዞችን አስቀድሞ የማስተዋል ጸጋ የሌለው መሪ ለመሪነት የተሰጠ ሰው አይደለም። መሪው ይህ ጸጋ ኖረውም አልኖረውም ግን ሁልጊዜም ቢሆን ራሱን ልምድ ባላቸው ሙሁራኖችና አማካሪዎች መክበብ አለበት። ትክክለኛ መሪ የሁሉንም የካበተ ልምድ ያላቸው አዋቂዎች ምክርና አስተያየትን የሚጠይቅ፥ ነገር ግን ለማንም ሳይገዛ የራሱን የመጨረሻ ውሳኔ ማሳለፍ የሚችል የገዛ ራሱ ቆፍጣና ጌታ ሆኖ መገኘት አለበት፡፡

ኒኮሎ ማኪያቬሊ
@zephilosophy


የማያኬቬሊ የተመረጡ አባባሎች

1.የአንድን መሪ ወይም ገዢ ብቃትና ችሎታ ለመገመት የመጀመሪያው መላ በዙሪያው ያሉ ሰዎችን መመልከት ነው።

2.አብዛኛው ሰው የሚያየው አለባበስህን ነው፡፡ ጥቂቶች ግን ትክክለኛ ማንነትህን ለማየት ልምድ አካብተዋል፡፡

3.ማዕረግ አይደለም ሰውን የሚያስከብረው፡፡ ሰው ነው ማዕረግን ማክበር ያለበት፡፡

4.የትኛውም ታላቅ ውጤት ያለምንም አደጋ ወይም ችግር ተሠርቶ አያውቅም፡፡

5.ከፍተኛ ፍላጎትና ፈቃደኝነት ባለበት ቦታ ሁሉ ችግሮች ትላልቅ መሆን አይችሉም።

6.ነፍስን ማንቀሳቀስ የሚችል ኃይል የሌለው ትንሽ እቅድ አታቅድ።

7.ሰዎች በሁለት መሠረታዊ ግፊቶች ይናጣሉ፡፡ ወይ በፍቅር አልያም በፍርሃት፡፡

8.ሰው መፈራትንም ሆነ መፈቀርን ሁለቱንም ማሳካት ካልቻለ መፈራት ከመፈቀር ይልቅ የተሻለ ስለሆነ እሱን ይምረጡ።

9.ይቅርታ የሚወጣው ደግነት ከተሞላው ነፍስ ነው፡፡

10.ሰዎች ምንም ዓይነት እርምጃ ለመውሰድ ከመወሰናቸው በፊት የሚጠብቃቸውን ፈተና እና አደጋ መመርመር አለባቸው ።ውሳኔያቸው ከመጀመሪያ ፍላጎታቸው ጋር የሚጣጣም ቢሆንም እንኳ ጉዳቱ ከጠቀሜታው ከበለጠ ሊተዉት ይገባል፡፡

@zephilosophy


የአለማችን ታላቁ ተጓዥ
ኢብን ባጡጣ
ከሞሮኮ-ቱርክ
ክፍል-1
@zephilosophy


ከምነቴ ጋር ቀረሁ

አውቃለሁ!
አታምኝም በማምነው
ያንደኛው ሰው መንገድ፣ ለሌላው ገደል ነው።
ቢቀና ጎዳናው፣ ቢወለወል አስፋልት
አብሮ ከማያልም፣ አብሮ መሄድ ልፋት
ያንደኛው ሰው እግር፣ ለሌላው እንቅፋት።

ባልጮህ ባደባባይ
ምኩራብ ባልገነባ፣ መዝሙር ባላሰማ
ከጥላየ በቀር፣ ባይኖረኝ ተከታይ
በቃል ወይ በዜማ
ተገልጦ ባይታይ
በልብ ተጠንስሶ፣ ባይን የሚገነፍል
እኔም እምነት አለኝ፣ ዋጋ የሚያስከፍል።

እምነት - ተስፋ - ፍቅር
መች ባንድ ላይ ሁኖ
ለሰው ልጅ ይሰጣል
በምነቱ የፀና፣ ድንገት ፍቅሩን ያጣል
ፍቅርሽን ሸኝቼው፣ ተስፋየን አባረርሁ
ከምነቴ ጋር ቀረሁ፡፡

በእውቀቱ ስዩም
📚አዳምኤል

@zephilosophy


እመ መከራ

ኢትዮጵያ እመ መከራ
የግዜር መመራመሪያው
የስቃይ ቤተ-ሙከራ
መውደቅማ ነበር ያባት
እንደ ያሬድ እስከ ሰባት
እንደ በላ ብላቴና
የእንክርዳድ ሙልሙል እንጎቻ
የትውልዴ እጣ ፋንታ
መውድቅ፥ መውድቅ፥ መውድቅ ብቻ!

በእውቀቱ ስዩም
📚የማለዳ ድባብ

@zephilosophy


"ሥልጣን ያባልጋል፤ እውነት ነው፤ ፍጹማዊ ሥልጣን ደግሞ የባለጌ ባለጌ እንደሚያደርግ የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ጎርጎሪያ ሶስተኛ የተናገሩት ሀሳብ ግሩም ምስክር ይሆናል᎓᎓ ነገር ግን፣ ይህም ታውቆ እንኳን ዛሬም እንደ ትላንቱ ሥልጣን የአያሌዎችን ልብ እያጓጓች፤ ልክፍት በሚመስል አስፈሪ ፍቅሯ እንደማግኔት ትስባቸዋለች:: ድሮም ሆነ ዘንድሮ የመንበር ጥማት ያው የመንበር ጥማት ነው፤ ከብዙዎች ልብ ተፍቆ አልወጣም:: ሥልጣን፣ ቢሰሩባትም ባይሰሩባትም እርካቧን የረገጠ፣ ኮርቻውን የተቆናጠጠ፣ መንበሯ ላይ የተደላደለ ሁሉ (ቢያንስ አብዛኛው) በሞቱ እንጂ በፈቃዱ ሊለያት የማይሻ ጦሰኛ ፍቅሯ ተቀፍድዶ ይኖራል፡፡ አፍቃሪዋም ዘመኑን ሁሉ ሲጨነቅና ሲጠበብ ዕድሜውን የሚገብርላት፣ የክብሩ ዘውድ፣ ወይም የመራራ ውርደቱ ፅዋ ትሆናለች።"

(ዲራአዝ፤ እርካብና መንበር)

@zephilosophy


እጅግ ተጠራጣሪዎች፣ አማኝ የምንመስል እጅግ ኢ-አማኞች፣ አስመሳዮችም ሆነናል። እኛ ኢትዮጵያውያን በአገዛዞች ጭካኔና ያንን አሜን ብሎ በሚቀበለው ባህላችን የተነሳ በጊዜ ሃ ሂደት አውቀንም ይሁን ሳናውቀው፣ የእስስትነት ባህርይን ተላብሰናል።

በመልታይፖላር ፐርሰናሊቲ ዲስኦርደር የተጠቃ ትውልድ ታቅፈን ነው የቀረነው። ኢትዮጵያዊ በቤተክርስትያንና መስጊድ ሌላ ሰው ነው። በሥራ ቦታ ሌላ። በአደባባይ ሌላ። በጓዳ ሌላ። ብቻውን ሌላ። ከወዳጆቹ ጋር ሌላ። ከትዳር አጋሩ ጋር ሌላ። ...

በኛ ማኅበረሰብ አንድ ሰው አንድ ብቻ አይደለም። የማይጨበጥና እርስበርሱ የሚቃረን ብዙ ሰው ነው! ከአንበሣነት ወደ እስስትነት ራሳችንን በአዝጋሚ ለውጥ የቀየርን ሕዝቦች ነን ቢባል ማጋነን አይሆንም።

ይህ ሁሉ የእኛ ኢትዮጵያውያን የወል መለያ ባህርይ፣ በመንግሥት ሥልጣን ላይ ለወጡ አፈሙዝ ለጨበጡ ኃይሎች ሁሉ፣ አመቺ ሆኖላቸዋል።

ለመጋለብ ያመቸ፣ ለመግዛት የተመቸ፣ ለመረገጥ የተዘጋጀ፣ ለመገረፍ ጀርባውን፣ ለመጫን ጫንቃውን ያደነደነ ህዝብ መሆኑን አገዛዞቹ አሳምረው ያውቃሉ። ጥቂቱን ጥቅም እያንጠባጠቡ፣ ሌላውን ጅራፍ እያወዛወዙ ይገዙታል።

ህዝቡም አንድ ገዢ አካል የመጨረሻ የማማረር ደረጃ ላይ ደርሶ ሆ ብሎ ካልተነሳ በቀር ይህ የመረገጥ እውነት፣ የአገዛዞች ሀሉ ባህርይ ነው ብሎ ተቀብሎታል።

የሐመር ሚስት ለአዲሷ ሚስት ባሏ የገረፋትን የጀርባዋን ጠባሳ እያሳየች፣ ባሌ ከአንቺ ይልቅ እኔን ነው የበለጠ የሚወደኝ እንደምትላት የመሠለ ነው!

ሚስቱን የሚማታው ቅናተኛ ባል ሚስቱን የሚወድ ነው! ይወደዳልም! መረገጥ ባህል ሲሆን በሁሉም የህይወት ዘርፍ ይንፀባረቃል!

ይህ ሁሉ አልበቃ ብሎ ደግሞ፣ በ20ኛው ክፍለዘመን በሀገራችን ሥልጣን ላይ የወጡ መንግሥቶች ራሳቸውን በህግ ሀገሩን ወደሚያስገብር አምባገነንነት ቀይረውታል።

ህጎች ሁሉ በሲስተም ዲዛይን የሚደረጉት የዜጎችን መብት ለመጠበቅ ሳይሆን፣ በይስሙላ የተረጋገጡ መብቶችን በሌላ ስልታዊ መንገድ ከዜጎች ላይ መቀማት የሚቻልበትን ሥርዓት በመዘርጋት ነው።

ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሁለት ጊዜ ህገመንግሥት አሻሽለዋል። ሶስተኛው ጅምር ረቂቅ ሆኖ ቀርቷል፣ በለውጡ ተቀድሞ ቀረ። በእነዚህ ሁሉ ውስጥ አንድም ጊዜ፣ ዜጎች ለፖለቲካ ዓላማ ተሰባስበው የፖለቲካ ፓርቲ የመመሥረትና በረላማዊ መንገድ የመንቀሳቀስ መብት አላቸው የሚል አንዲት ሰባራ አንቀፅ አልደነገጉም!

የሕዝብን መብት አስከብራለሁ ብሎ የመጣው የደርጉ ወታደራዊ መንግሥት፣ ለጊዜው በለውጡ ሰሞን አቅሙን እስኪያደራጅ በዝምታ ይመለከታቸው የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሁሉ በሚዘገንን አብዮታዊ በትር አንድ በአንድ ድራሻቸውን አጥፍቶታል።

በቀኃሥና በደርግ (በኢህዲሪ) ዘመን ለስሙም ቢሆን በኢትዮጵያችን በህገመንግሥት ለስሙ እንኳን የተረጋገጠው የዜጎች የመደራጀት መብት ለኢኮኖሚ ዓላማ ብቻ እስከሆነ ድረስ ነበር።

የሙያ ማኅበራትን (trade unionsን) መመሥረት ብቻ ለዜጎች ተፈቅዶ፣ ለፖለቲካ ዓላማ መደራጀት ግን ለገዢ መንግሥት ብቻ የተፈቀደ ነበር።

ንጉሡም በሞናርክ ርዕዮት ተመራሁ በማለት፣ ንጉሡን ገረሰስን ያሉትም አብዮተኞች በማርክሲዝም ተመራን በማለት - ሁለቱም የሕዝብን የተደራጀ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለማፈን ቆርጠው የተነሱ በህግ የሚያስገብሩ አምባገነኖች ነበሩ!

ይሄ ታሪካችን ይገርማል! ምክንያቱም በጠባይና በርዕዮተዓለም፣ በሕዝባዊ መሠረትና በአባሎቻቸው ዓይነች ፍፁም የሚለያዩ አገዛዞች፣ ነገር ግን የሕዝብን የፖለቲካ ተቃውሞ በማፈን ላይ አንድ ሆነው መገኘታቸው ይገርማል። የኛን የኢትዮጵያውያንን የረግጠህ-ግዛው ውርዴ በዘመን ለውጥ አለመፈወስ የሚያረጋግጥም ነው!

በኢትዮጵያ 3ሺህ ዓመት የሀገረመንግሥት ታሪክ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያችን፣ ለይስሙላም ቢሆን ለፖለቲካ ዓላማ ተሰባስቦ ማኅበር የመመሥረትን፣ በሠላማዊ መንገድ የፖለቲካ ፓርቲ መሥርቶ የመንቀሳቀስን የዜጎች መብት በመጀመሪያ በሽግግር ወቅት ቻርተር፣ ቀጥሎም በህገመንግሥት ያሰፈረው የወያኔ-ኢህአዴግ መንግሥት ነው!

ለዚህ ታሪካዊ ተግባሩ ሊመሠገን ቢገባውም፣ በተግባር ግን ሥጋውን ሰጥቶ ቢላዋውን የመንሣት የተለመደ ጨዋታውን ይጫወት የነበረ አገዛዝ ነው። ከሌሎቹ ብዙም የተለየ የሚመሠገን ባህርይ አልነበረውም።

የመግዣ ሥልቱን አራቀቀው፣ እና ትያትራዊነቱን ጨመረው እንጂ፣ የዜጎችን የልዩነት የፖለቲካ ሃሳብን የመግለፅ መብት በህጎቹም ሎነ፣ በአፈና ተቋሞቹ በተግባር ሲጨፈልቅ የኖረ - እናም ለምሥጋና የማይመች - አምባገነን መንግሥት ሆኖ አልፏል! (አልፏል ስንል አርፏል እንዳይመስል፣ ስሙንና መልኩን ቀይሮ አሁንም አለ!)

ፅሑፌን ስደመድም፣ የአትዮጵያ ሕዝብ የመብት ጥያቄውን በተደራጀ መልክ እንዳያቀርብ፣ በመብት ጥያቄው እንዳይገፋበት፣  ዋናው አስሮ ያስቀመጠው ነገር፣ ባጠቃላይ፣ በመሠረታዊነት፣ ከሌላ የውጭ አካል የሚመጣ ነገር ሳይሆን፣ ሕዝቡ ራሱ ለመገዛት የተመቸ ሕዝብ ስለሆነ ነው!

የመንግሥቶቹ አፋኝነት በሁለተኛ ደረጃ የሚመጣ ጉዳይ ነው። አመቺ ለም መሬት ያገኘ ዘር በቀላሉ ይበቅላል። አመቺ ተገዢ ህዝብ ያገኘ መንግሥትም፣ በቀላሉ የተቃወሙትን የመውጊያ ቀንድ ያበቅላል።

በዚያም ላይ ገዢ ሆነው የሚመጡትም ከጃፓን ወይ ከፓፓዋ ጊኒ የመጡ ሰዎች አይደሉም። ከኛው መሐል የወጡ፣ በአስተሳሰብም፣ በስነልቦናም፣ በባህርይም እኛኑ የመሠሉ ሰዎች ናቸው! ገዢነትንና ተገዢነትን የሣሉበት መንገድ ከሌሎቻችን የተለየ አይደለም። ሥልጣን ላይ ሲወጡም የሚያሳዩት ባህርይ ያንኑ እኛ ውስጥ ያለውን ቢሆን የሚገርም ነገር የለውም!

ለማንኛውም ይህን ለዘመናት የተጣባንን የተገዢነት ስነልቦና በምንድነው መስበር የምንችለው? ምን ብናደርግ ከአፈና ቀንበር መውጣት እንችላለን? የሚለው ላይ መነጋገር፣ መወያየት፣ ራሳችንን መፈተሽና መቀበል፣ ....

ራሳችንን ለመለወጥ የግልና የጋራ እንቅስቃሴዎችን መጀመር፣ በህግ የታሠረ መንግሥትን ለመፍጠር መታገል፣ እኛ ባይኖረኅ ልጆቻችን ዘመናዊ ዕውቀት እንዲኖራቸው የቻልነውን ሁሉ መጣር... ለነገዬ የሚባሉ የቤትሥራዎች አይመስሉኝም!

ሕዝቡን የሚያስፈራራ ሳይሆን፣ ሕዝቡን የሚፈራ መንግሥት ለማምጣት የተገዢነት ቀንበራችንን ሰብረን ለመብቶቻችን በጋራ መነሳት ብንችል፣ ከዘር የወረደ የፖለቲካ ውርዴያችን ቢያንስ በኛ ላይ ማብቃት ይችላል!

በነገራችን ላይ፣ እኛ ነፃ ነን የምንለው ኢትዮጵያውያን ለአገዛዞች የመገዛት ስነልቦናችን፣ ከተቀሩት በቅኝግዛት ባርነት ሥር ከማቀቁት ሌሎች ሕዝቦች የተለየ አይደለም! እጅጉን ይመሳሰላል ብቻ ሳይሆን፣ almost አንድ ዓይነት symptoms ናቸው ያሉብን!

ታዲያ ብዙዎች ከቅኝተገዢነት ነፃ ከወጡ እኛም ከአፋኝ አገዛዞች የመብት አፈና ነፃ መውጣት እንችላለን ማለት ይመስለኛል።

በርግጥ ከቅኝገዢዎች መላቀቅ ቀላል ነው። ከቅኝተገዢነት አስተሳሰብ መላቀቅ ነው ከባድ ሆኖ የተገኘው። ብዙዎች ዛሬ ነፃ ወጥተው፣ ግን አሁንም ነፃ አልወጡም። አሁንም ሥሪታቸው የተቀረፀው ከተገዢነት ቁስ ውስጥ ነው።  እስካሁን ነፃ ወጣን የሚሉት ጨርሰው በመንፈስ ነፃ መውጣት ፈተና ሆኖባቸዋል!

እኛ ኢትዮጵያውያን ሙሉ መብት የተጎናፀፍን ዜጎች እንዳንሆን ጠፍሮ የያዘንን፣ የአካልም የመንፈስም እሥራት በጣጥሰን፣ እስስትነታችንን አውልቀን፣ ሙሉ ሰው፣ ሙሉ ዜጋ፣ ሙሉ አትዮጵያዊ፣ ሙሉ ጌቶች የምንሆንበትን ዘመን እናፍቃለሁ!

ተነሣ፣ ተራመድ፣ ክንድህን አበርታ!

ሰናይ ጊዜ!!

@zephilosophy


እኛን ኢትዮጵያውያንን ጠፍሮ የያዘን ምንድነው?
____
(የባህል አብዮትና መፈንቅለ-አስተሳሰብ እንደ መፍትሄ)

ፀሀፊ -አሰፋ ሀይሉ

ከሃያ ምናምን ዓመታት በፊት ከዩኒቨርሲቲ የመመረቂያ ጥናቴን የሠራሁት በFreedom of Association ላይ ነበረ።

ያ ጥናት በተለይ ሰዎች ፖለቲካዊ ማኅበሮችን የሚፈጥሩበትን ሂደትና በፓርቲ ምሥረታና እንቅስቃሴዎች ላይ ያሏቸውን ነፃነቶችና ገደቦች በዓለም ዙሪያና ባገራችንም across centuries ያሉትን አንኳር እውነቶች ለመዳሰስ የሞከርኩበት ጥናት ነበረ።

የኢትዮጵያችንን በተመለከተ ከእኔ በፊት ጉዳዩን ያጠኑ ጥቂት የውጭና ያገርውስጥ ምሁራን ነበሩ። የሚገርመኝ አንድ ነገር፣ የጥናቶቹ ሁሉ ግኝትና ድምዳሜ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በንጉሡም ዘመን፣ በወታደራዊው ደርግ ዘመንም ሆነ በኢህአዴግ ዘመን፣ (ሌላ ቀርቶ አሁንም ላይ) በአንድ ዓይነት ባህርይ የተቃኘ መሆኑ ነው።

በኢትዮጵያችን ለምን የmultiparty አስተሳሰብ አልዳበረም? ለምን የተቃውሞ ድምፅን ሰብሰብ ብሎ በማኅበር ተደራጅቶ ማሰማት፣ ለጋራ መብት በጋራ መቆም ለምንድነው ኢትዮጵያውያንን የሚያስፈራቸው? ምንድነው የያዘን? የሁሉም፣ የሁላችንም ጥያቄ ነው።

ዋና ታሪካዊ ምንጩ የእኛ የኢትዮጵያውያን አስተሳሰብ ወይም አመለካከት ነው የሚል ነው።

እኛ ኢትዮጵያውያን ሥር-የሰደደ የተገዢነት ስነልቦና ያለን ሕዝቦች ነን! አብረን በጋራ ተደራጅተን መብታችንን ከመጠየቅ የያዘን ነገሬ ጥልቅ የሆነ ሌላን ሰው የሚጠራጠር የወል ሰብዕናችን ነው።

ሥልጣን ካለው ኃይለኛ አካልና ከባለጊዜ ጋር ጫን አድርጎ አፍ መከፋፈት ለቅስፈት ይያርጋል የሚለው ዘመን ያፈጀ የፍርሃት ባህርያችን ነው። እጅግ ጥልቅ መሠረት ያለውና ከዘር ማንዘር የወረደ የአድርባይነት በሽታችን (ባህላችንም) ነው።

የራሳችንን መብት ለመጠየቅ መፍራት ብቻ አይደለም! ሌላውም ከኛ በአቅም ያነሰ ነው የምንለውን ሰውም መብቱን እንዲጠይቀን፣ አሊያም ተቃውሞውን እንዲተነፍስ አንፈቅድለትም።

በድሮ ዘመን ባርያና አሽከር፣ ወይ ጢሰኛ፣ ወይ የቤት ሠራተኛ፣ ወይም የበታች ሠራተኛ መብቴ ነው የሚለውን ወይም ቅር ያለውንና እንዲስተካከልለት የሚሻውን ነገር ከጠየቀን፣ እኛ ኢትዮጵያውያን በመጀመሪያ የሚመጣልን ሃሳብ፣ ጥጋብ ይዞት ነው የሚል ነው።

ተረቶቻችን፣ ምሣሌዎቻችን እና ስነልቦናችን ሁሉ ጥጋበኛን ያወግዛል። የመብት ጥያቄ ሁሉ ከትዕቢት የመነጨ፣ ከመታበይ የመጣ ይመስለናል። ጥጋቡን ሳላስተነፍስለት የቀረሁ እንደሆነ እኔን አያርገኝ እየተባለ ይዛታል! እውር ቢሸፍት እስከ ጓሮ ነው እየተባለ ይዘበታል።

በቅሎ ገመዷን በጠሰች በራሷ አሳጠረች እየተባለ ይሰለቃል። ይቺ ባቄላ ያደረች እንደሆን አትቆረጠምም ይባላል። ለአኩራፊ ቁርሱ ራቱ ይሆናል ይባልለታል።

አጓጉል የረዘመች የማሽላ ዛፍ፣ አንድም ለወፍ አሊያም ለወንጭፍ - እየተባለ ከሰው ተነጥሎ አጉል መንጠራራት ለመቀሰፍ እንደሚዳርግ ይሰበካል። አጉል መንፈራገጥ ለመላላጥ ይባላል፣ ቆማ* ሲጠግብ በትሩን ይወረውራል እየተባለ "ጥጋቡ" መሣለቂያ ይደረጋል።

ንጉሥ አይከሰስ፣ ሠማይ አይታረስ እንላለን። ወንዝ ቁልቁል እንጂ ሽቅብ አይፈስም እንላለን። ወደላይ አንጋጠህ ለበላዮችህ ምን ማድረግ እንዳለባቸው መንገር ድፍረት ነው። ብልግና ነው። ጥጋብ ነው።

እና ዝምታ ወርቅ መሆኑን እንሰበካለን። ዝም ባለ አፍ ዝንብ የማይገባ መሆኑን እንማራለን። በአፍ ይጠፉ በለፈለፉ እየተባለ ይተረታል። ሰው ያመነበትን አውጥቶ እንዳይናገር የሚያሠለጥን የዝጎች ባህል ነው ያለን። መከበር በከንፈር መሆኑን እናምናለን። ኢፍትሃዊነትን ከመጋፈጥ ይልቅ በአድርባይነት የምናገኛት ሽልማት ትናፍቀናለች!

በእነዚህ ከዘር ማንዘር ከወረስናቸው የፖለቲካ ውርዴዎች ይባብሎ ደግሞ፣ በኢትዮጵያችን የመንግሥትነት ሥልጣንን የያዙ ገዢዎች ሁሉ ደግሞ - እስካሁንም ድረስ -  በሥልጣናቸው ላይ ጥያቄ ያነሳባቸውን ማናቸውንም አካል የሚያስተናግዱት - እጅግ አስከፊውን ቅጣት በማከናነብ ነው!

ደፍሮ ሥልጣንን የተቃወመን ሰው ወይም የሰዎች ስብስብ፣ አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ ሌሎች እንዳይነሱ መቀጣጫ ማድረግ ነው ለዘመናት የኖረና ያልለቀቀን ባህላችን። የተቃወመ ሰው የሚቀጣው የራሱን ፋንታ ብቻ አይደለም፣ የሌሎችንም ድርሻ ነው! ሌሎች እሱን አይተው አደብ ገዝተው መቀመጥ አለባቸው።

አፄ ዮሐንስ ያመፁባቸውን ወሎዬዎችና ጎጃሜዎች ወርረው፣ ጨፍጭፈው፣ ዘርፈው፣ አልበቃ ብሏቸው የየሰዉን እጅ ቆራርጠው ይመለሱ ነበር።

አፀ ቴዎድሮስ ሸዋ፣ ጎጃም፣ ወሎ፣ ራሱ ጎንደር ላይ ዘምተው ዘርፈው፣ አቃጥለው፣ ገድለው አላረካ ሲላቸው የሰውን እጅ ሁሉ ቆርጠው ጥለው ይመለሱ ነበረ።

ጎንደር ከተማዋ ሙሉዋን በታሪኳ ሶስት አራት ጊዜ ስትቃጠል፣ አንዴ ዮዲት ጉዲት፣ ግራኝ አህመድ፣ ደርቡሽ፣ እያለ በመጨረሻ ራሳቸው አፄ ቴዎድሮስ ናቸው ሌላ ቦታ ዘምቼ ስመለስ ከድታችሁ ጠበቃችሁኝ ብለው ከተማዋን ያቃጠሏት። ሌላ ቀርቶ እሳቸውን ለመቀበል አበባ ይዘው የወጡ ሴቶች አልቀሯቸውም!

በሃገራችን ሥልጣንን በተቃወሙ ላይ ከሠማይ የአውሮፕላን ጥቃት ማዝነብ የጀመሩት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ናቸው! ደርግ ቀጠለበት! ኢህአዴግ በሄሊኮፕተሮች ያጭድ ነበር ሶማሌ ድረስ ሄዶ።

ይሄኛው የብልፅግናው መንግሥትም በሥልጣኑ ላይ የተነሱበትን የገዛ ወገኖቹን በድሮንና ሔሊኮፕተር ያጭዳል! የዘር ውርስ ነው። የማይለቅ ውርዴያችን ነው የተቃወሙንን ያለምህረት መቅጣት!

ይህ ነገር የሚጀምረው በቤት ውስጥ ከህፃናት አስተዳደግ ጀምሮ ነው! በእኛ ሀገር እስከቅርብ ጊዜ ህፃን ልጅ ከነስሙ አሽከር ነው። ጩሎ ነው። ከቁምነገር የማይጣፍ ነው። እንዲከበር የሆነ ነገር ይዞ ወይ ሠርቶ ማሳየት አለበት። ...

አለበለዚያ በሌላ ሰው ቁጥጥር ስር ነው። የሚቸረው እንጂ የሚጠይቀው መብት የለውም። አለዚያ አይቀጡ ቅጣት ይጠብቀዋል። ሰጥ ለጥ ብሎ ለauthority መገዛትን የምንለማመደው በህፃንነታችን ነው። የታዛዥነት ዓመል የሚያሸልምበት፣ ማጉረምረም የሚያስኮረኩምበት አስተዳደግ ነው ያለን!

ልጅ ፊቱን አይበርደውም፣ ደሃ ሕዝብም አይርበውም! አሽከር መረገጥ አይቆረቁረውም! የምንኖረው በአገዛዞች መልካም ፈቃድ ነው እንጂ፣ እኛ የተገባን ባለመብቶች ሆነን አይደለም!...

እነዚህንና እነዚህን የመሠሉ ሥር የሰደዱ አስተሳሰቦቻችን ናቸው፣ ቢያንስ ያለፈውን በዓለም ሁሉ ንቃት ያላቸው ሕዝቦች በምድራቸው ማንበር የቻሉትን የመናገር፣ የመቃወም፣ የመፃፍ፣ የመሰብሰብ፣ ሠላማዊ ተቃውሞ የማድረግና ለፖለቲካ ወይም ለሥልጣን መያዝ ዓላማ ተሰባስቦ የመደራጀት መብታችንን ማስከበር እንዳንችል ቀፍድደው የያዙን።

በእነዚህ ሁሉ ላይ ደግሞ፣ ህዝቡ ራሱን censor እንዲያደርግ፣ ጥላውን እንኳ እንዳያምን፣ እርስበርሱ እንዳይተማመን የሚያደርጉ የመንግሥት የምሥጢር ወሬ አቀባዮችና ሠላዮች ደግሞ ተመድበውበታል።

ዛሬ አፍህን ከፍተህ በማግሥቱ የለህም! ሃሳቡን ሊያወያይህ የቀረበህ፣ ተናግሮ አናጋሪ ነው። ማንንም አታምንም። ስለሆነም ግፋ ቢል በዘመድ አዝማድና በቅርብ ቤተሰብ ትደራጃለህ።

ለዚህም ነው ባገራችን በ1900ዎቹ የታዩ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች በአብዛኛው በአንድ ቤተሰብ አባላት፣ በአንድ ወገን፣ በአንድ ብሔር፣ በአንድ ካዴት ሁሉ ሊሆኑ የበቁት። ማንም ስለማይታመንም፣ ባልንጀራ በየወንዙ ይማማላል። ሲጀመር እንጂ ሲጨረስ የሚታይ ህብረት የለም!


አባ ይፍቱኝ
(በእወቀቱ ስዩም)

ሲኦል አለ ሲሉኝ፥ የለም ብየ ክጀ
የባልቴት ተረት ነው፥ በማለት ቀልጀ
አውቄ በድፍረት፥ በድያለሁና
ያንጹኝ በንስሐ፥ ያንሱኝ በቀኖና
ሲኦል ከነጭፍራው፥ በጉም ተሸፍኖ
እንዴት ሳላየው ኖርኩ፥ ካጠገቤ ሆኖ?

አባ ይፍቱኝ
ሰይጣን ብሎ ነገር፥ የተጭበረበረ
ዋዛ ነው ቧልት ነው፥ ብየ አስብ ነበረ
ይሄው እውነት ሆኖ፥ ዋዛና ተረቱ
ባይኔ በብረቱ
ዲያብሎስን አየሁት፥ በሸሚዝ ዘንጦ
እልፍ ግዳይ ጥሎ፥ ቸብቸቦ ጨብጦ

አባ
ልክ እንደ ብርሌ፥ አጥንት ሲከሰከስ
አባይን አዋሽን፥ የሚያስንቅ ደም ሲፈስ
ለምለም ፍጥረት ሁላ፥ ወደ አመድ ሲመለስ
ልክ እንደ ጧፍ ሐውልት፥ ምስኪኖች ሲጋዩ
ምድጃው ዳር ሆነው፥ ይሄንን እያዩ
ገሃነም ከላይ ነው፥ ብለው መሳትዎ
እርስዎ እንደፈቱኝ፥ እግዚሃር ይፍታዎ፡፡

@zephilosophy

8k 0 53 86 110

ግንቦት የእምዬ ማርያም ወር
ደራሲ- ስብሀት ገ/እግዚሀብሔር
መፅሀፍ-ሽፍቶችና መሪዎች
በአፈ-ታሪክ ላይ የተመረኮዘ ጥናታዊ ፅሁፍ

ያገራችን ሴት በስጋ የሄዋን ልጅ፡ በመንፈስ የማርያም ልጅ ናት ብለን እናምናለን። ይህን ፅሁፍ ለሴት ልጅ ሁሏ በከበሬታ እንደ ገፀ-በረከት እናቀርባለን - ወላዲታችን ናትና። እንኳን ማርያም ማረችሽ፡ ማርያም በሽልም ታውጣሽ፣ እንላታለን የማርያምን አራስ።

የአባ ኪዳነ ማርያምን፣ ቅኝት እንከተላለን።

የአለም መድኃኒት እመሀላቸው ተወልዶ ቢሰቀልላቸው፣ ካዱት። እኛ ግን አመንን!!

“ኢትዮጵያ ታበፅህ እደዊሀ ሀበ እግዚአብሄር” ብሏል ነብዩ ዳዊት። “ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች”

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተነስቶ፣ ከደቀ መዛሙርቱና ከሌሎቹ አማኞቹና ተከታዮቹ ጋር ሰነባብቶ ወደ አባቱ ሊያርግ ሆነ።

ድንግል እናቱን ሲሰናበት፣ እንዲህ አላት
“የኢትዮጵያን ምድር ለርስት ጉልትሽ ሰጥቼሻለሁ”
እንግዲህ እቺ ሀገር ድንግል በክልኤ ማርያምን አጥብቃ የምትወዳት ያለምክንያት አይደለም። የአስራት ሀገሯ ስለሆነች!!

ቤተ ክህነት የቅዱሳንን በአላት በሙሉ ከነደባሎቹ ታቦት! ታውቅ እና ታክብር እንጂ፣ ምድረ ሀበሻ ግን በወሩ በአንድ ልደታ፣ በሦስት በአታ፣ በአስራ ስድስት ኪዳነምህረት ፣ በሀያ አንድ ማርያም እያለ ነው ሄዶ የሚያስቀድሰው።

ምእመናን ከቤተ ክርስቲያን ሲወጡ ብናስተውል፣ አብዛኛዎቹ ነጭ ያገር ልብስ የለበሱ ሴቶች ናቸው። ወንዶቹ በቁጥር ቢበዛ አንድ አስረኛ ሲሆኑ፣ ለዚያውም አብዛኛዎቹ የፈረንጅ ኮትና ሱሪ የለበሱ ናቸው።

አራስ ልጅ ሆነንም  ቋንቋችንን እና ባህላችንን የምታስተምረን እናታችን ናት።ልጅ ሆነንም አንጥልጥላን ቤተ ክርስትያን የምትወሰደን እናታችን ናት ።ህዝብ ሆነንም ዝማሬም ሽብሸባም ለእምነትም ለእንጀራም እንቀጥላለን እንጂ፣ ቤተ ክርስትያኑን የምትሞላው ግን ሴት ልጅ ናት።

ግንቦት የእምዬ ማርያም ወር ነች
በግንቦት አንድ ፣ ሶስት ፣አስራ ስድስት ፣ሀያ አንድ  በቅደመ ተከል -ልደታ፣ ባእታ ፣ኪዳነ ምህረት ፣ማርያም እያለን በብዙ ድምቀት እናከብራታለን።

(በጥቂቱ አጥሮና ታርሞ የቀረበ)

@zephilosophy

8.9k 0 21 34 73

አስደናቂ ውብ ታሪኮች ከመላው አለም

ተራኪ- ግሩም ተበጀ
@zephilosophy




መኖርህን ሰዎች ይሻሉ

ብትወድቅ ብትከፋ የያዘችህ ቤትህ አለም
ሳታሰናብት መሰናበት በራስ የለም

መች መብቴ ብለህ ወደህ መርጠህ መጣህባት
መብቴ ነው ብላለች አንተን ማኖር መች ጠበባት
!!


ራስን ማጥፋት መብት ወይስ ጥፋት
ፍሬው ማሩፍ

ፈላስፋ ለመሞት ሁሌም ዝግጁ ቢኾንም በምንም መልኩ ግን ራሱን ሊያጠፋ አይገባም  አማልዕክቶቹ እሰከአልጠሩን ድረሰ በራስችን ፍቃድማ ህይወታችንን አንነጥቅም ይላል ሶቅራጦስ።

ራሱን ማጥፋት የደካማነት ማሳያ ሲሆን፤ አንድ ሰው ራሱን ካጠፋ ጨካኝ እና ለመኖር ብቁ ያልሆነ በመሆኑ ነው የሚለን ደግሞ አርስቶትል ነው፡፡ ለዚህ ፈላስፋ ራስን የማጥፋት ድርጊት ሊወገዝ የሚገባው ድርጊቱን ስለሚፈጽመው ግለሰብ ተብሎ ሳይሆን በማኅበረሰቡ ላይ ከሚፈጥረው ጉዳት አንፃር ነው፡፡ የዚህ ምክንያትም ይህ ድርጊት በማኅበረሰቡ ላይ የሚፈጥረው መልካም ያልሆነ ተጽዕኖ መፍጠሩ አይቀሬ በመሆኑ ነው፡፡ በተጨማሪም የማኅበረሰቡ አካል የሆነ ግለሰብ የማኅበረሰቡን ሕግና መመሪያ ሊያከብር ይገባል፤ ማኅበረሰቡ ደግሞ ራስን የማጥፋት ድርጊትን የሚከለክል በመሆኑ ድርጊቱ የሚፈጸም ግለሰብም የቀብር ሥርዓቱ በክብር ሊደረግ አይገባም ይላል አርስቶትል፡፡

ከጥንታውያኑ የግሪክ ፈላስፎች(ከላይ ከተመለከትናቸው) በተቃራኒ የሮማን እና የግሪክ ጸሐፍት እና ፈላስፎች ራስን የማጥፋት ድርጊትን ደግፈው ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል ሉክራተስ ሕይወት በእጃችን ለመጥፋት ካሻት ለምን እንከልክላት ይለናል፡፡ ይህ ፈላስፋ ነፍስያው ራሱን ያጠፋ ዘንድ ሽታም ራሱን አጥፍቷል ይባላል። ሌላኛው የሮማን ዜጋ የነበረው ሲስሮ በበኩሉ ሰው በኑሮ ደስተኛ ካልሆነ እና ከምቾት ከተራራቀ ለምን ይኖራል የሚል እሳቤ ነበረው። የግሪኩ ፈላስፋ ኢፕክረስ ደግሞ ማናችንም ከስቃይ የሚገላግልንን የትኛውም ተግባር የመፈፀም መብት እስካለን ድረስ እና ከመፍተሄዎቹ መካከል አንዱ ራስን ማጥፋት ከሆነ፣ ማንም ሰው ራሱን በማጥፋቱ ሊወገዝ አይገባም ይለናል፡፡

አብዛኞቹ የሊብራል (ibertarian) የፓሊቲካ ፍልስፍና አራማጆች በበኩላቸው ሰው ራሱን የመግደል ሞራላዊ መብት አለው ይላሉ።የዚህ ፍልስፍና አራማጆች አንድም የአካላችን ባለቤት ከኛ ውጪ ማንም ስላልሆነ ባሻን ኹኔታ የማስወገድ መብት ስላለን፣ በሌላ በኩል የትኛውም ግለሰብ በሞቴ ደህንነትን አገኛለው ካለ ሊከለከል ስለማይገባ  የሚሉ መከራከርያዎችን በማንሳት ራስን ማጥፋት በሕግ ሊደገፍ የሚገባ ድርጊት ነውም ይላሉ።

ራስን መግደል በተፈጥሮ ራሳችንን የመንከባከብ እና የመውደድ ተገቢነትን የሚቃረን ነው የሚለን ደግሞ አኪውናስ ነው። “ራስን መግድል ግለሰቡ አባል የሆነበትን ማኅበረሰብ ላይ ጉዳት ከማድረሱ ባሻገር ህይወታችን የፈጣሪ ስጦታ የመሆኗን ሃቅ ይቃረናል፤ እንዲሁም የምድር ቆይታችንን በእሱ ፍቃድ ላይ መመርኮዙን የሚክድ ድርጊት በመሆኑ ራስን የማጥፋት ድርጊትን እቃወማለሁ" ይለናል የሥነ መለኮት መምህሩ።

የተፈጥሮ ሕግ ጽንስ ሓሳቦች አራማጆችም እንደሚሉት ራስን የማጥፋት ድርጊት የተፈጥሮ ሕግ ከሆነው የመንስዔ-ውጤት ግንኙነት ጋር የሚጋጭ ሲሆን፤ በተጨማሪም ራስን ማጥፋት የትኛውም ፍጡር ራሱን ከአደጋ ሊከላከል እንጂ ጉዳት ሊያደርስ አይችልም ከሚል የሥነ ኑባሬ ሥርዓት ጋር የሚጣረስ ድርጊት ነው የሚል ክርክርን ያነሳሉ።

ከተፈጥሮ ሕግ አንጻር የሚነሳውን መከራከርያ የሚቃወመው ዲቪድ ሁም “Of Suicide” በሚለው ጽሑፉ ላይ እንደሚለው ሰዎች በስቃይ ላይ ሆነው ሞት ብቻ ማምለጫቸው ኾኖ በተገኘ ጊዜ ራስን ማጥፋት ፈጣሪ አይፈቀድም ብሎ መከራከር አስገራሚ ነው፡፡ ይህ እምነት እና አስተሳሰብ የሰው ልጅ በሕይወቱ ላይ ምንም የማድረግ መብት የለውም እንደማለት ነው፡፡"

ከዴቪድ ሁም በተቃራኒ ቆሞ ኢማኑኤል ካንትን እናገኝዋለን። “The Metaphysics of Morals" በሚለው ስራው ላይ ካንት ራስን ማጥፋት ከአውሬነት ለይቼ አላይውም ይላል። አንድ ሰው ራሱን ለመግደል ሞክሮ ካልተሳካለት እንደ አውሬ አሊያም እንደ ቁስ ነገር ነው ልንመለከተው የሚገባው የሚል እሳቤም አለው፤ እንደ ውሻ አሊያም እንደ ፈረስ ለስፖርታዊ ጨዋት ልንገልገልበትም እንችላለን ይለናል። እንዴት ብትሉት “ሰውዬው ራሱን ለማጥፋት አቅዶና ወጥኖ ከሞከረው ሰው የመሆን ክብርን በራሱ ፍቃድ ነስቷል” የሚል ምላሽ ይሰጣችዋል።

ራስ የማጥፋት ድርጊትን በተመለከተ ከተነሳ የኢሜል ዱርካይም ስም እና “Le Suicide” የሚል ስራው ሳይጠቀስ ሊታለፍ አይችልም፡፡ ዱርካይም እንደሚለው ራስን የማጥፋት ድርጊት ስለሚፈጽሙ ግለሰቦች ጥናት እና ምርምር ሊደረግ ከተፈለገ መሰረታችንን የግለሰቡን ግላዊ ጠባያት ብቻ ላይ ካደረገን ትክክል አይደለም የሚለው ዱርካይም፤ ባይሆን ትኩረት ማድረግ ያለብን ግለሰቡ የሚገኝበት ማኅበረሰብ ላይ ነው የሚል ድምዳሜ ነበረው፡፡ የዚህም ምክንያት ራስን የማጥፋት ድርጊት የሚፈጸምበት ምክንያት ድርጊቱን በሚፈጽመው ግለሰብ እና አባል የሆነበት ማኅበረሰብ መካከል ያለው መሰተጋብር ጋር የተያያዘ በመሆኑ ነው፡፡

ለምሳሌ በእኔ ጥናት መሰረት ብሎ ዱርካይም እንደሚያስቀምጠው ከካቶሊኮች ይልቅ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታዮዎች ራሳቸውን ያጠፋሉ፡፡ የዚህም ምክንያት ካቶሊኮቹ ዓማኞቻቸውን የሚቆጣጠሩበት መንገድ ጥብቅ በመሆኑ ነው ይለናል። እንዲሁም ከሴቶቹ ይልቅ ወንዶች፣ ካጋቡትም ላጤዎቹ፣ ከወለዱት ያልወለዱት በይበልጥ ራስን የመግደል ድርጊትን ይፈጽማሉ።

እንዲሁም ከሰላሙ ይልቅ በጦርነት ወቅት ይበልጥ ድርጊቱ ይባብሳል። ይህ የዱርካይም ጥናት ራስን የማጥፋት ድርጊትን ከግላዊ ችግር ብቻ ተያይዞ ብቻ ሲታይ የነበረውን እሳቤ በብዙ መንገድ ለውጧል፤ እንዲሁም አዲስ የሥነ ማኅበረሰብ የጥናት መስክን በተለይም ከሥነ አእምሮ ጥናት በመነጠል የራሱን መሰረት እንዲኖረው አድርጎታል ይባላል፡፡

ዱርካይም ራስን የማጥፋት ድርጊትን ከድርጊቱ ፈጻሚ እና አባል ከሆነበት ማኅበረሰብ ጋር ካስተሳሰረ በኃላ፣ በመቀጠል ድርጊቱ የሚፈጸምበትን አራት ምክንያቶች ያስቀምጣል፡፡ እነሱም ከመነጠል የተነሳ (egostic suicide) ፣ “ለመሰዋትነት' (Altruistic suicide) ፣ “በመቃዋስ ምክንያት (Anomic suicide) እና “በመወጠር (Fatalistic suicide) በሚል ይከፈላሉ።

በኢትዮጵያ ውስጥ በቅርብ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በየአመቱ ከ8000 በላይ ኢትዮጵያዋን ራሳቸውን ያጠፋሉ፡፡ የዓለም የጤና ድርጅት በ2018 ባወጣው ጥናት መሰረት በኢትዮጵያ የሞት ምክንያት ከሆኑት መካከል ራስን የማጥፋት ድርጊት 1.2% የሚሽፈን ሲሆን፤ ይኽም ማለት ከ100,000 ኢትዮጵያን መካከል 1.38 የሚሆኑት ድርጊቱን ይፈጽማሉ፡፡ አሁን አሁን ደግሞ ተባብሶ ቀጥሏል እገሌ ራሱን አጠፋ የሚል ወሬ ጆሯችን እየለመደው መጥተዋል፡፡ ትኩረት ቢደረግበትና መፍትሄ ቢሰጠው አይበጅም ትላለቹሁን!

የሙዚቃ አቀናባሪ፣ የግጥም እና ዜማ ደራሲ እንዲሁም ፈላስፋ የሆነው ኤልያስ መልካ ራስን የማጥፋት ድርጊት ልክ አለመሆኑን የገለጸበትና በዘሪቱ ከበደ፣ በአብነት አጎናፍር እና በጆኒ ራጋ ድምጽ "መኖርህን ሰዎች ይሻሉ” በሚል ርዕሰ የተቀነቀውን ሙዚቃ  በመጋበዝ እናብቃ።

@zephilosophy


በሀገራችን ኢትዮጵያ ራሳቸውን የሚያጠፉ ወጣቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ ነው ...ምክንያቱ ምንድን ነው ትላላችሁ?

Edited


"የላባቸው ዋጋ ይከፈላቸው!!"

የፍልስፍና ቻናላችን የጤና ባለሙያዎች ብሔርና ሀይማኖት ሳይለያያቸው ለመብታቸው መከበር በአንድነት ሆነው ያነሱትን የመብት ጥያቄ እና ትግል ይደግፋል።

የጤና ባለሙያዎች የመንግስት ውክቢያ እና እስር ሳይስፈራቸው ለመብታቸው በድፍረት ና በፅናት መቆማቸው መብቱ ቢጣስም በፍርሀት ለደነዘዘው የህብረተሰብ ክፍል ምሳሌ በመሆን መነሳሳትን ፈጥረዋል።

ሆኖም ግን ህዝቡ ተገቢውን እውቅናና ድጋፍ ባለመስጠቱ ምክንያት የመብት ጥያቄው በሀይል የመዳፈን ጥላ አጥልቶበታል። መንግስት በሚያደርገው  የጭካኔ ድርጊት ምክንያት ከዶክተሩ የባሰ ችግር ያለበት የህብረተሰብ ክፍል የመብት ትግሉን እንዳይቀላቀል "ስራዬን አጣለሁ" የሚል ስጋት አድሮበታል።

ይህ ጥያቄ የጤና ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን የአብዛኛው የመንግስት እና የግል ዘርፍ ሰራተኞች ጥያቄ ነው።መምህራኖች፣ የፍትህ ባለሙያዎች፣ ኢንጂነሮች ተገቢውን ደሞዝ እያገኙ አይደለም።

በ6 አመት ውስጥ ነዳጅን ጨምሮ አብዛኛው ምግብ እና መሰረታዊ ፍጆታ  በሶስት እጥፍ(300%) ጨምሯል ለሰራተኛው የደሞዝ ጭማሪ የተደረገው ግን ከ30% በታች  ነው።በዚህም ቤተሰቡን ለማስተዳደር ይቅርና የራሱን የእለት-ጉርስ እንኳን ለመሸፈን በቂ አይደለም።

ለልጆቹ  የተሻለ ትምህርት የሚፈልግ ህዝብ መምህራኖች የተሻለ ደምወዝ እንዲያገኙ ማድረግ አለበት። ይህ ካልሆነ ፈፅሞ የትምህርት ጥራትን ሊጠብቅ አይገባውም መምህሩም ስራውን እንደተከበረ ስራ (profession) ሳይሆን  እንደመጠባበቂያ (ጊዜ ማሳለፊያ) ስራ ሊቆጥረው ይገደዳል።

ከሙስና የፀዳ እውነተኛ ፍትህ ለማግኘት የሚፈልግ ህዝብ መጀመሪያ  የዳኛ፣ የአቃቢ-ህግ ፣የፖሊስ ደሞዝ በቂ አይደለም  ብሎ ሊታገል ይገባል።

ስርዓተ -አልበኝነት እንዲኖር የማይፈልግ ህዝብ ሰራተኛው ተገቢውን የላቡን ዋጋ እንዲከፈለው  ማገዝ ይኖርበታል።አለበለዚያ ነጥቆ እና አጭበርብሮ  የሚበላን ሰው እያበረታታ ነው ማለት ነው።

የዜጎች የመብት ጥያቄ የሚመለሰው ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል አንድ ሆኖ በመተባበር ድምፁን ሲያሰማ ነው።በተናጠል የሚደረግ ትግል ነጥሎ ለመምታት ያመቻልና ...

የህዝብን ሀብት ጠንካራ ገቢ በሚያሰገኙ ፕሮጀክቶች ላይ ከማዋል ይልቅ የሀገሩ ህዝብ እንኳን በነፃነት የማይንቀሳቅስበት አገር ላይ ለቱሪዝም ገቢ ብሎ ቢሊዮን ብሮችን በማውጣት የቅንጦት ሪዞርቶችና መናፈሻዎች መስራት ትክክል አይደለም።

በጦርነት የተጎዳውን ኢኮኖሚ መልሶ እንዲያገግም ከማድረግ ይልቅ ቢሊዮን ዶላሮችን አውጥቶ በአንድ አገር ሁለት ቤተ-መንግስት የሚሰራ መንግስት ህዝባዊ ተቃውሞ ካልገጠመው በስተቀር ይህን ስራውን ይቀጥላል።

በማጭበርበር እና በሙስና በአንድ ጀንበር ሚሊዮን ብሮችን በማጋበስ ሀገርቱ ላይ በነፃነት የሚርመሰመሱ ሰዎችን ከማሰር ይልቅ መብቱን በሰላማዊ መንገድ የጠየቀውን ዜጋ ማሰር እና ከስራ ማፈናቀል ፍትሀዊ አይደለም።

@zephilosophy


ከዚህ በተጨማራ መንግስት የጤና ባለሙያውን ላይሰንስ እቀማሃለሁ፣ ከሥራ አሰናብትሃለሁ፣ እያለ እያስፈራራ ይገኛል ምን ትላላችሁ።


.....✍ካለፈው የቀጠለ

ዘመናዊነት እና ድህረ ዘመናዊነት (modernity and postmodernity)

የዘመናዊነት እሳቤዎች

ከመካከለኛው ዘመን ተነስተን፣ በዘመነ ትንሳኤና በአብርሆት በኩል አልፈን ዘመናዊነት ላይ ደርሰናል፡፡ ይሄም ባጠቃላይ የአውሮፓ የ1500 ዓመታት የሐሳብ ታሪክ (History of Ideas) ነው፡፡ እነዚህ ዘመናት ሲመሩበት የነበረውን ዋነኛ ጭብጥ መግለፅ ካስፈለገ፣ እንዲህ በማለት ማስቀመጥ ይቻላል፤

👉መካከለኛው ዘመን - የክርስትና አስተምህሮ የበላይነት የነበረበት፣

👉ዘመነ ትንሳኤ – የጥንት ግሪክና ሮማውያን ሥነ ፅሁፍ ንቅናቄ፣
👉ዘመነ አብርሆት - ነፃነት (ከውጫዊ ስልጣኖች - ባህል፣ አጉል እምነትና ዘውድ ነፃ መሆን)፣

👉ዘመናዊነት - ምክንያታዊ ማህበረሰብ ግንባታ፣ ምክንያታዊነት እያደገ ሲሄድ ደግሞ የህዝቡ የኑሮ ሁኔታ እየተሻሻለ ይሄዳል የሚል ተስፋ፤

‹‹ዘመናዊነት›› ምክንያታዊ የሆነ የማህበረሰብ ግንባታ ከሆነ ሂደቱ የጀመረው ቀደም ብሎ ነው ማለት ነው፡፡ አንዳንድ ምሁራን ይሄንን ሂደት ‹‹ከዘመነ ትንሳኤ ጀምሮ የመጣ ነው›› ይሉታል፡፡ ሌሎች ምሁራን ደግሞ ‹‹ዘመናዊነት ‹‹የጥንቱን ባህል ማንሰራራት›› የሚለው የዘመነ ትንሳኤ ርዕይ ከተሳካ በኋላ የመጣ ቀጣዩ ፕሮጅክት ነው›› በማለት ይገልፁታል፡፡ በዚህ ትርጉም ከሄድን ‹‹ዘመነ አብርሆት›› የዘመናዊነት አካል ይሆናል ማለት ነው፤ ምክንያቱም ‹‹የአብርሆት እሴቶች ግልፅና ጉልህ ሆነው የወጡት በዘመናዊነት ነው፡፡

ዘመናዊነትን በአውሮፓ ለተከሰተው አዲስ ነባራዊ ሁኔታ የተሰጠ የአመለካከት ግብረ መልስ አድርገው የሚመለከቱትም አሉ፡፡ ይሄም አዲስ ነባራዊ ሁኔታ የሚገለፀው በዘመናዊ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ የብሔር መንግስታት መመስረት፣ በገንዘብ ኢኮኖሚ፣ በካፒታሊዝም እና በኢንዱስትሪ መስፋፋት ነው፡፡ ይሄም አዲስ ነባራዊ ሁኔታ በህጎች፣ በመመሪያዎች፣ በመለኪያዎችና በቁጥሮች የሚመራ ቢሮክራሲና የህይወት ዘይቤ እንዲኖር አድርጓል፡፡ ከዚህም በመነሳት ነው ጀርመናዊው ሶሲዮሎጂስት ማክስ ቬበር (Max Weber) ‹‹ዘመናዊነት ማለት በህጎች፣ በመመሪያዎች፣ በመለኪያዎች፣ በቁጥሮችና በቢሮክራሲ የሚመራ የህይወት ዘይቤ ነው›› በማለት ትርጉም የሰጠው፡፡

በአጠቃላይ ዘመናዊነት

💡በድሮው ላይ ማመፅ ነው፤ ይሄም አመፅ ጎጂና ኋላ ቀር ከሆኑ የድሮው (የመካከለኛው ዘመን) ልማድ፣ አሰራርና አስተሳሰብ መነጠልን የሚያመላክት ነው፤ ከእነሱም ተነጥሎም ህይወትን በዕውቀትና በአመክንዮ መዘወር ነው፡፡ ለምሳሌ፣ በዘመናዊነት ውስጥ ‹‹ድርቅ የተከሰተው የሰው ኃጢያት ስለበዛና እግዚአብሔር ስለተቆጣ ነው›› አይባልም፤ በዘመናዊነት ውስጥ ‹‹በሽታ የሰይጣን ሥራ ነው›› አይባልም፤ ‹‹እንደዚህ የሆንኩት የ40 ቀን ዕድሌ ስለሆነ ነው›› አይባልም፡፡ በዘመናዊነት ውስጥ ከእንደነዚህ ዓይነት አስተሳሰቦች እንነጠልና፣ የምናምነው ሳይንስ የሚነግረንን የመንስኤ ውጤት ህግጋትን ነው፡፡

💡የፕ/ር መሳይ ከበደን ‹‹ዘመናዊነት ማለት ከድሮው ባህልና አስተሳሰብ መነጠል ሳይሆን፣ እንዲያውም የድሮው ባህሎችና እሴቶች እንደገና እንዲያብቡ ማድረግ ነው››የሚለውን ሐሳብ ከወሰድን ደግሞ ‹‹ዘመናዊነት ማለት ለጥንት ባህላችንና እሴቶቻችን አዲስ አመክኖያዊ መሰረት መስጠትና ዘመናዊ አሰራርን ማላበስ ነው›› በማለት መተርጎም እንችላለን፡፡ ለምሳሌ፣ የዘመን መለወጫ በዓል በጣም የቆየ ባህል ነው፡፡ በበዓሉ ውስጥ እርድ፣ ጠላ መጥመቅ፣ ዳቦ መድፋት፣ ባህላዊ ልብሶች መልበስ፣ ቤተ ዘመድ መሰባሰብ፣ አንድላይ መመገብ...ይከናወናል፡፡ በዘመናዊነት ውስጥ ይሄንን ባህል አልተውነውም፤ እንዲያውም የበዓሉን አከባበር በዘመን አመጣሽ አልባሳት፣ ምርቶችና የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች በመጠቀም በዓሉን ይበልጥ ደማቅ እየሆነ ነው፡፡

የድህረ ዘመናዊነት እሳቤዎች

ከ1970ዎቹ ጀምሮ የተነሳው ድህረ ዘመናዊነት ሁለት መገለጫዎች አሉት፡፡

✍በአንድ በኩል፣ አሁን በተጫባጩ ዓለም ላይ ያለውን እውነታ የምናሳይበት መንገድ አድርገን ልንመለከተው እንችላለን፡፡

✍በሌላ በኩል ደግሞ፣ ድህረ-ዘመናዊነት ‹‹ሞደርኒቲ ከሽፏል፤ አልፎበታል›› የሚል አስተሳሰብ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

ሊዮታርድ ‹‹The Postmodern Condition: A Report on Knowledge›› በተሰኘ መጽሐፉ ውስጥ ድህረ-ዘመናዊነትን ሲተረጉመው እንዲህ ይላል፣

‹‹ድህረ-ዘመናዊነት በታላላቅ ትረካዎች አለማመን ነው

በዘመናዊነት ውስጥ የነገሮችን ተፈጥሮ እና ምንነት የምንረዳባቸው እንዲሁም እውነትን፣ ዕውቀትንና ግብረገብነትን የተመለከቱ ህይወታችንን የምንመራባቸው ቅቡል የሆኑ ታላላቅ ትረካዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ የዘመናዊነት ትረካዎች ውስጥ የተወሰኑት እንዲህ የሚሉ ናቸው፣

👉ሁሉንም ሰው የሚያስማማ እውነት አለ (There is Universal Truth)፤

👉ሁሉንም ሰው የሚያስማማ ሥነ ምግባር አለ (There is Universal Morality)፤

👉ዕውቀት ማግኘት ደስተኛ ያደርጋል፤

👉ዕውቀት ማግኘት ነጻነት ያለው ህይወት እንድንኖር ያደርገናል፤

ድህረ-ዘመናዊነት እንደነዚህ ዓይነቶችን ትረካ አይቀበልም፡፡ በመሆኑም፣ ድህረ- ዘመናዊነት ማለት፣

✍በእነዚህ የዘመናዊነት ትረካዎች የማናምንበትና የማንስማማበት፣

✍ሰዎችን ሁሉ እኩል በሆነ መንገድ የሚያስማማ የጋራ እውነት የሌለበት፣

✍እውነትና ሥነ ምግባር አንፃራዊ የሆኑበት፣

✍ሰዎች ሁሉ ትክክል የሆኑበት፣

✍ሁሉም ባህሎችና ሃይማኖቶች ትክክል የሆኑበት፤

✍ሰዎች እውነትን ገሃዱ ዓለምውስጥ ወጥተው የሚፈልጉበት ሳይሆን በዲስኩር፣ በቋንቋና በፖለቲካ ላይ ተሞርኩዘው የእውነትን ተፈጥሮ የሚረዱበት አዲስ ዓለምነው፡፡

በዘመናዊነት እና በድህረ-ዘመናዊነት አስተሳሰብ መካከል ያለውን ልዩነት የሚከተለውን ጥያቄ በማንሳት ማየት እንችላለን፡፡

💡አንድ ማህበረሰብውስጥ አላዋቂነት መኖሩ ነው ማህበረሰቡ እንዳይዘምን የሚያደርገው (The sleep of reason produces monsters)? ወይስ

💡የአዋቂዎች መብዛት ነው ማህበረሰቡ ውስጥ ችግር የሚፈጥረው (The dream of reason produces monsters)?

የመጀመሪያው፣ ‹‹አንድ ማህበረሰብ ውስጥ አላዋቂነት መኖሩ ነው ችግር የሚያመጣው የሚለው አስተሳሰብ ‹‹የሰው ልጅ የበለጠ ለባህልና ለሃይማኖት ራሱን በሰጠ ቁጥር፣የሰው ልጅ በዘፈቀደ ህይወቱን በመራ ቁጥር ነጻነትን ማግኘት አይችልም፣ ደስተኛ ህይወትን መምራት አይችልም››ወደሚል ድምዳሜ ይወስደናል፡፡ እንደ ካንትና ሄግል ያሉ ፈላስፎች ይሄንን አስተሳሰብ ተከትለው ነው ዘመናዊነት ምን እንደሆነ የሚነግሩን፡፡

ሁለተኛው፣ የድህረ-ዘመናዊነት ፍልስፍናን የሚያቀነቅኑ ፈላስፎች ደግሞ በተቃራኒው የሚሉን ‹‹የአዋቂዎች መብዛት ነው ማህበረሰቡ ውስጥ ችግር የሚፈጥረው፡፡ ይሄም ማለት በጣም ማለምም፣ በጣም መጠየቅም፣ በጣም ዘመናዊ መሆንና ምክኒያታዊነትን ማዳበርም አንድ ማህበረሰብ ውስጥ ተቃርኖን ይፈለፍላል፡፡ ለዚህ መደምደሚያ ማሳያ የሚሆነው ደግሞ ሉላዊ በሆነው ዓለም ውስጥ፣ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ተመንድጓል በምንልበት፣ የግለሰብ ነፃነት እስከ ጥግ በደረሰበትና ቁሳዊ ዕድገት ባለበት ዓለም ውስጥ እንደ ጀኖሳይድ እና ሆሎኮስት ያሉ እልቂቶች፣ የእርስበርስና የዓለም ጦርነቶች እንዲሁም የህይወት ትርጉም አልባ ስሜቶች ውስጥ መዘፈቃችን ነው፡፡

@zephilosophy

እስኪ እናንተ ጋርስ ያለው ሀሳብ ምንድነው ተወያዩበት👇👇👇

20 last posts shown.