ነገረ መለኮት ከሌላ ማዕዘን...
እኔ እንደ በርትራንድ ረስል ‹‹ሐይማኖት የፍርሃት ውጤት ነው›› አልልም፡፡ ይልቁንስ ምንነቱን እና ከየትነቱን የማያውቁት በቅጡ ያልተደመጠ፣ ምላሽ ያልተሰጠው ናፍቆት ወደ ማመን እንደሚመራን አስባለሁ፡፡ በእርግጥ የሕይወት፣ የአምልኮ ነገር ሲጀመር አደራረጉ እንደሞኝነት መሆን አለበት፡፡
አጀማመሩ ልክ ከፏፏቴ እንማውጋት፣ ለጨቅላ እንደማንጎራጎር፤ ምናልባት ለነፋስ እንደማፏጨት ስሜት የማይሰጥ ከሚመስል መዳዳት ሳይሆን አይቀርም፡፡ ነገርግን መሰረታዊው ሰው የመሆን ቅጥም የተሰራው በዚህ የገርነት ቅኝት መሆን አለበት፡፡ ሰው የፍጥረት የበላይ (superior) የመሆኑን ቀቢጽ የሚሰብኩት ከራሱ መካከል ተከስተው ሙሉ በሙሉ ከተፈጥሮ ቅኝት እስኪነጥሉት ድረስ የንጽህና ልጅ ነበር፡፡
ለምሳሌ የላቲን አሜሪካ ቅዱስ ሕዝቦች ኮጊዎች (Kogi) የክርስቶስን አዳኝነት፣ የነብዩ መሐመድን መልዕከተኝነትን ለመስማት ለአንድ ሺህ ስድስት መቶ ዓመታት የቅኝ ገዥዎችን መምጣት መጠበቅ ነበረባቸው፡፡ ነገርግን ሰው መሆን አልጠፋባቸውም፡፡ እንኳን ለመሰላቸው ለመላው ግዑዝ ለሆነው ስነፍጥረት ሁሉ ይራራሉ፡፡ ለሺህ ዘመናት አማኞች ነበሩ፡፡ ለዚያውም የተፈጥሮን ሥሪት የተከሉ... ዛሬም ድረስ የጥንታዊ አያቶቻቸውን የአምልኮ እና አስተሳሰብ ዘይቤዎችን እያስቀጠሉ ዘመናዊውን የሰው ልጅ ሽሽት በኮሎምቢያ አይደፈሬ የተራራ ሰንሰለቶች ይኖራሉ፡፡
እነዚህ ሕዝቦች ለተፈጥሮ ካላቸው ጥንቁቅነት የተነሳ መንገድ ስንኳ ለመስራት አንዲትም ድንጋይ ከቦታዋ አያፈናቅሉም፤ አንዲትም ሀረግ አይነቅሉም፡፡ ሁሉንም ነገር የሚከውኑት የተፈጥሮን የልብ ምት በተከተለ መልኩ ነው፡፡ ሰሚ ባያገኙም ቅሉ ስህተተኛው ታናሽ ወንድማችን ለሚሉት ዘመናዊው የሰው ልጅ ተፈጥሮን ስለመጠበቅ አስፈላጊነት በተከታታይ መልዕክቶችን ይልካሉ፡፡
እንዲህ የንጽህና ልጅ በነበረ ጊዜ ሰው ጨካኝ በሚመስለው ነገር ግን ፍትህና ርትዕ ሚዛኑ በሆነው ስሙር የተፈጥሮ ሰሌዳ ላይ ጊዜያዊያነቱን፣ አላፊ ጠፊነቱን በጸጥታ የተቀበለ ስኩን ፍጥረት ነበር፡፡ ተፈጥሮን ለመግዛት ለመግራት በበላይነት ስሜት ከመቋመጥ ይልቅ ተፈጥሮን መልበስ፣ መዋረስ ሰው የመሆን ደመነፍስን ያሰለጥን የለምን?
ሁሉም ነገር ሲጀመር የሰው ልጅ የመሆንን ነገረ ውል ለመካን ሙዝን ልጦ የመበላት ጥበብ ማወቅ ብቻ ይበቃው ነበር፡፡ ሲፈጠርም ጀምሮ ስሪቱ የተፈጥሮ ነው፡፡ በእርግጥም ያኔ የሰው ልጅ ደመነፍስ እንደመላዕክት፣ እንደመለኮቱ ጉልህ ‹እኔነቱ በስግብግብ ምሪት ያልደበዘዘ ገር (simplistic) ነበር፡፡
ሊዮ ቶልስቶይ የጻፈው በብዙዎች ዘንድ ሊታወቅ የሚችል አንድ አስገራሚ ተረት አለ፡፡ አሳጥሬ ልተርከው..
በአንድ ደሴት በብህትውና የሚኖሩ ሦስት ጻድቃን ነበሩ፡፡ አኗኗራቸው ተርታ ነው፡፡ ቀስ በቀስ ስለቅድስናቸው በአጎራባቿ ከተማና በመላው ሀገሪቱ ዝነኞች ሆኑ፡፡ ሰዎች ወደ እነርሱ ይጎርፉ ጀመር፡፡
ይህ ያላስደሰተው የአጎራባቿ ከተማ የቤተክህነት አስተዳዳሪ አንድ ቀን ሊገበኛቸው በጀልባ ሄደ፡
እንደደረሰም ጠየቃቸው..
‹‹ዝናችሁ በከተማውና በሀገሪቱ ናኝቷል፡፡ ለመሆኑ ለቅድስና ያበቃችሁ የተለዬ የምትጠቀሙት ጸሎት አለን?
‹‹እውነቱን መናዘዝ ይኖርብናል፡፡ በሥላሶች፣ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ከማመናችን የተለየ ምንም የምናውቀው ፀሎት የለም፡፡ ይልቁንስ የምንፈልገው መናገር ነው።ይፈጸምልናልም፡፡››
እንግዳው የቤተክህነት ሰው ሳቀ፡፡ ያለ ጸሎት የሚሆን ነገር እንደሌለ አስረድቶ ፀሎቱን አስጠናቸው፡፡
‹‹እባክህ እኛ የተማርን ሰዎች ባለመሆናችን ጸሎትህ ረጅም ከመሆኑ የተነሳ ልናስታውሰው አልቻልንምና ድገምልን፡፡›› ባሉት ጊዜ እንደገና አስጠናቸው፡፡ ጸሎቱን ለሦስተኛ ጊዜ እንዲያጠኑት ረዳቸው፡፡
በአሸናፊነት ስሜት ወደ እናት ከተማው መመለስ ጀምሮ የሀይቁ መሀል ላይ ሲደርስ ግን ለማመን የሚከብድ ነገር ሆነ፡፡ ሦስቱ መናኒያን በውኃው ላይ በፍጥነት እየተራመዱ ተጠጉት...
‹‹እባክህ ያስጠናኸን ጸሎት ረጅም ስለሆነ እኛም የተማርን ባለመሆናችን ተረስቶናል እና ብትደግምልን፡፡›› ተማጸኑት፡፡
በውኃ ላይ እንደቀላል መራመድ በሚያስችል ቅድስናቸው የተደነቀው እንግዳው ጎብኚ ግን በውኃ ላይ እስከመራመድ የሚያስችል የመብቃታቸውን ተዓምር ከተመለከተ በኋላ ...
«በፍጹም! ትክክለኛው ጸሎት የእናንተው ስለሆነ በዚሁ ቀጥሉ ብሎ አሰናበታቸው፡፡››
የሰው ልጅ የንጽህና ልጅ በነበረ ጊዜ እንደነዚህ ሦስት ጻድቃን ነበረ፡፡ በዘመን ሂደት ቀስ በቀስ ሰው መሆንን ረስቶ አውሬነትን ተለማመደ፡፡ ሰው የመሆን ውሉ ሲደናገረው በመጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ሰሎሞንስ ስንኳ በዚያ ሁሉ ክብሩ እንደነሱ አልለበሰም›› የተባለላቸው የሜዳ አበቦች ግን አበባ መሆን እንግዳ አልሆነባቸውም፡፡ አበባ ለመሆን ብዙ ምርምር፣ ላቦራቶሪ አላስፈለጋቸውም፡፡ የጽጌ ጌጥነታቸውን ለመቀዳጀት የንጽህና ልጆች መሆን ብቻ ይበቃቸዋል፡፡
የሰውን ልጅ ግን እናውቅልሃለን በሚሉ በራሱ በሰው ልጆች የመላው ፍጥረት የበላይ መሆኑን እየተጋተ ልጅነቱን ካደ፡፡ በሚያምነው ፊት ምንምን፣ ጊዜንም ቢሆን የማይፈራ የነበረውን ፍጥረት በሂደት ድንጉጥ አደረጉት፡፡ ድንጋጤው ጭካኔን ወለደ፡፡
ለራሱ ለመላው ስነፍጥረት ሁሉ ጭካኔን የሚነዛ አረመኔ ሆነ፡፡ ከጊዜና ከቦታ ጽንፍ፣ ከራስ መዳዳት በላይ አልፎ ማሰብ የማይችል ድኩማን...
በፍም እሳት ማቃመስ
ያዕቆብ ብርሀኑ
@Zephilosophy