ስለ ሁሉም ነገር ተሳስታችኋል (እኔም)
አንዳንድ እጅግ መጥፎ ወንጀለኞች ስለራሳቸው በጣም ጥሩ ይሰማቸዋል፡፡ ይህ ስለራሳቸው የሚሰማቸው ጥሩ ስሜት፣ በዙሪያቸው ካለ እውነታ ይልቅ ሌሎችን ለመጉዳትና ላለማክበር ምክንያት የመደርደር ስሜት የሚያሳዩበት ነው፡፡
ሌሎች ሰዎች ላይ በሚያደርጓቸው አሰቃቂ ድርጊቶች ምክንያታዊ መሆናቸው የሚሰማቸው ግለሰቦች በራሳቸው ጻድቅነት፣ በራሳቸው እምነቶችና ያንን ማድረግ የሚገባቸው መሆን ላይ የማይነቃነቅ እርግጠኝነት የሚሰማቸው ናቸው፡፡ ዘረኞች፣ የዘረኝነት ስራ ይሰራሉ፡፡ ምክንያቱም ስለራሳቸው ዘር የበላይነት እርግጠኞች ናቸው፡፡ የኃይማኖት አክራሪዎች ራሳቸውን ይጎዳሉ ወይም ብዙ ሰዎች ይገድላሉ፡፡ ምክንያቱም በመንግስተ ሰማያት ሰማዕታት የመሆን ቦታ እንዳላቸው እርግጠኞች ናቸውና፡፡ ወንዶች ሴቶችን አስገድደው ይደፍራሉ ወይም ሴቶች ላይ ጥቃት ይፈፅማሉ፤ ይህንንም የሚያደርጉት በሴቶች አካል ላይ ባላቸው የበላይነት እርግጠኞች በመሆናቸው ነው፡፡ክፉ ሰዎች ክፉ መሆናቸውን አያምኑም፡፡እንዲያውም የሚያስቡት ሌላው ሁሉ ክፉ መሆኑን ነው፡፡
እዚህ ላይ ችግሩ እርግጠኝነት ሊደርስበት የማይቻል መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ በብዙ ጉዳዮች ላይ እርግጠኝነትን መከተል በአብዛኛው ወይም መጥፎ በሆነ ሁኔታ የማያስተማምን ነገርን የሚፈጥር መሆኑ ነው፡፡
ብዙ ሰዎች ስራቸው ላይ ባላቸው ችሎታ ወይም በሚያገኙት የደሞዝ መጠን የማይነቃነቅ እርግጠኝነት አላቸው፡፡ ያ እርግጠኝነት ግን መጥፎ እንጂ የተሻለ እንዲሰማቸው አያደርጋቸውም፡፡ ሌሎች ከእነርሱ በላይ እድገት ሲያገኙ ሲመለከቱ ትንሽነት ይሰማቸዋል፡፡ ያለመደነቅና እውቅና ያለማግኘት ስሜት ይሰማቸዋል፡፡
የወንድ ጓደኛሽን የፅሁፍ መልእክቶች በሚስጥር ማየት ወይም ሰዎችን ስለ አንቺ ምን እንደሚሉ ጓደኛሽን የመጠየቅ አይነት ቀላል ባህርያት እንኳን የሚነሱት ዋስትና ከማጣትና እርግጠኛ ለመሆን ካለን ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ ነው፡፡
ከዚያ ውስጥ ውስጡን ስለሚበላን ራስን ከፍ አድርጎ የማየት ስሜት ተጠቂ የምንሆነው በእነዚህ ዋስትና ማጣትና ጥልቅ ተስፋ መቁረጥ ጊዜያት ነው፡፡
ይህ ውስጥ ውስጡን የሚበላ የበላይነት ስሜት መንገዱን ለማግኘት ትንሽ ማጭበርበር እንደሚገባን፣ ሌሎች ሰዎች መቀጣት እንደሚገባቸው ፣ የምንፈልገውን አንዳንዴም በኃይል ማግኘት እንደሚገባን ማመን ናቸው፡፡
ይህ እንደገና ወደኋላ የመመለስ ህግ ነው፡፡ ያም ስለሆነ ነገር እርግጠኛ ለመሆን የበለጠ በሞከርን መጠን፣ የበለጠ እርግጠኛ ያለመሆንና ዋስትና ማጣት ይሰማናል፡፡
የዚህ ግልባጭም እውነት ነው፡፡ እርግጠኛ ያለመሆንና ያለማወቅን የበለጠ በያዝን መጠን የማናውቀውን ለማወቅ የበለጠ ፍላጎት ይሰማናል፡፡
እርግጠኛ ያለመሆን ሌሎች ላይ የምንሰጠውን ፍርድ ያስወግድልናል፡፡ የሆነን ሰው በቴሌቭዥን፣ ቢሮ ውስጥ ወይም በመንገድ ላይ ስንመለከት የሚሰማንን አላስፈላጊ ኩረጃና አድልዎ ባዶ ያስቀርልናል፡፡ እርግጠኛ ያለመሆን በተጨማሪ ራሳችን ላይ ከመፍረድ ያሳርፈናል፡፡ ተፈቃሪ መሆን አለመሆናችንን አናውቅም፣ ምን ያህል እርግጠኞች እንደሆንን ለማወቅ ብቸኛው መንገድ ስለእነዚህ ነገሮች እርግጠኛ ባለመሆን መቆየትና በልምምድ ለማግኘት ክፍት መሆን ብቻ ነው፡፡
እርግጠኛ ያለመሆን የሁሉም እድገትና መሻሻል ስር ነው፡፡ አሮጌው ብሂል እንደሚገልፀው ሁሉንም እንደሚያውቅ የሚያምን ሰው ምንም አይማርም፡፡ በመጀመሪያ የሆነ ነገር የማናውቅ መሆናችንን ካላወቅን ምንም ነገር ልንማር አንችልም፡፡ ምንም የማናውቅ መሆናችንን የበለጠ ባመንን መጠን፣ የበለጠ የመማር እድል እናገኛለን፡፡
እሴቶቻችን ፍፁም ያልሆኑና ያልተሟሉ ናቸው፡፡ ፍፁምና የተሟሉ እንዲሆኑ አድርጎ መገመት ራስን ከፍ አድርጎ ማየትና ሀላፊነትን ችላ ማለትን የሚፈጥር በአደገኛ ሁኔታ ግትር አስተሳሰብ ውስጥ ያስቀምጠናል። ችግሮቻችንን ለመፍታት ብቸኛው መንገድ በመጀመሪያ እስከዚህ ነጥብ ድረስ ያሉት እርምጃዎቻችንና እምነቶቻችን የተሳሳቱ ሊሆኑ እንሚችሉ ማመን ነው፡፡
የትኛውም እውነተኛ ለውጥ ወይም እድገት እንዲካሄድ መሳሳታችንን ለማመን ግልፅነት መኖር አለበት፡፡ ወደ እሴቶቻችንና ቅድሚያ የምንሰጣቸው ነገሮች መመልከት ከመቻላችንና ወደተሻለና ጤናማ ልንለውጣቸው ከመቻላችን በፊት፣ በመጀመሪያ አሁን ስላሉት እሴቶቻችን እርግጠኛ አለመሆን ይገባናል፡፡ እሴቶቻችንን በመከፋፈል መመርመርና ስህተቶቻቸውንና ተፅዕኗቸውን ማየት፣ ከቀሪው አለም ጋር እንዴት እንደማይገጥሙ መመልከት፣ አላዋቂነታችንን ፊት ለፊት አፍጥጠን ማየትና ማመን አለብን፡፡
እድገት ማለቂያ የሌለው ተደጋጋሚ ሂደት ነው፡፡ አዲስ ነገር ስንማር፣ የምንሄደው ከ “ስህተት” ወደ “ትክክል” ሳይሆን ከስህተት ወደ አነስ ያለ ስህተት ነው፡፡ አንድ ተጨማሪ ነገር ስንማር አነስ ካለ ስህተት ከዚያ በመጠኑ አነስ ወዳለ ስህተት እየሄድን ነው፤ እንዲህ እንዲህ እያለ ይቀጥላል፡፡ ሁልጊዜ በፍፁም ወደ እውነትና ወደ ፍፅምና ባለመድረስ ወደ እውነትና ፍፅምና የመቅረብ ሂደት ላይ ነን፡፡ለራሳችን የመጨረሻውን “ትክክለኛ” መልስ ለማግኘት መፈለግ አይገባንም፡፡ በዚያ ምትክ ነገ ከዛሬ ይልቅ መሳሳታችን የቀነሰ መሆን እንድንችል ዛሬ ስህተት የሆንባቸውን መንገዶች ፈልገን ማግኘት ይገባናል፡፡
📚The subtle art of giving a f*ck
Mark Manson
ይቀጥላል....
@zephilosophy