የዓለም ሰላምን ማረጋገጥ
ኢማኑኤል ካንት ፤ በ1795 ዓ.ም ባዘጋጀው አነስተኛ በራሪ ወረቀት (Pamphlet) ላይም እንዴት በዓለም ላይ ፍጹማዊ ፍጹማዊ ሰላምን ማስፈን ይቻላል በሚል ደረጃ በደረጃ አስረድቷል፡፡
አገራት ሰላምን ማስፈን ከፈለጉ ሊከተሏቸው የሚገቡ ሶስት መንገዶች ብሎ የጻፋቸውን እንመልከት፡-
1. ሪፐብሊክ መሆን (ህዝባዊ መንግስት መመስረት)-
ካንት ሁሉም የሀገሪቷ ህዝብ በህግ ፊት እኩል መሆን አለባቸው ይለናል፡፡ ህጉም በዜጎች የጋራ ፍቃድ ሊጸድቅ ይገባዋል፡፡ እንዲህ ከሆነ ይለናል ካንት፣ ህዝቦች መንግስታቸው እንዳይዋጋ ያግዱታል፤ ምክንያቱም ወደ ጦርነት ከተገባ ንብረት የሚወድምባቸው እና የሚሰደዱት እነርሱ ናቸውና፡፡ ሃብታሞች እና አምባገነን ባለስልጣናት ብቻ ናቸው ጦርነትን የሚያውጁት፤ በጦርነቱ ከሚያጡትም ይልቅ ትርፋቸው
ይበልጣል፡፡
2. የሪፐብሊኮች ፌዴሬሽን መመስረት (ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩ መንግስታትን በአንድ ማቀናጀት) -
በንግድ ይሁን በሌላም መንገድ በመንግስታት መካከል ግንኙነቶች ሊመሰረቱ ይገባል፡፡ የዚህ ህብረት አካል የሆኑ መንግስታትም ሉአላዊነታቸውን አሳልፈው መስጠት እና በአንድ ንጉስ የመመራት ግዴታ የለባቸውም፤ ይልቁኑ በምክንያት የሚመራ የንግድ ትሥሥርን ይዘረጋሉ፡፡
3. ኮስሞ ፖሊታኒዝምን መቀበል (ሁሉም ሰዎች እኩል ናቸው ብሎ ማመን)
ካንት ሁሉንም ሰው በአንድ መደብ መድቦ እኩል ናቸው አላለም፤ ይልቁኑ ሰዎች በመሃላቸው የጋራ መከባበር ሊኖር ይገባል ይለናል፡፡ ሌላውን ሰው እንደ አውሬ እያየን ወይም ከሰው በታች ዝቅ አድርገን እያንቋሸሽነው ሰላምን ማምጣት አንችልም፡፡
አሁን ላይ የካንትን እሳቤ የሚከተሉ የዓለም አገራት አሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል አውሮፓውያን በአውሮፓ ህብረት ስር የጋራ የሆነን የንግድ ትስስር መስርተዋል፡፡ በእነዚህ አገራት መካከልም ጦርነት የመከሰት እድሉ በእጅጉ አናሳ ነው፡፡
@Zephilosophy