5.የህዋ ግንዛቤ በዘመናዊ ፍልስፍና ታሪክ ውስጥ
የህዳሴውን ዘመንን ተከትሎ በሣይንሱም ሆነ በፍልስፍናው ብዙ አይነት አስተሳሰቦችና ትምህርቶች ይራመዱ ጀመር፡፡
ፍልስፍና “የሰውን ህይወት እጣፈንታ የሚወስን ኃይል አለ” ከሚል እምነት በመላቀቅ ሰው የራሱን ህይወት በራሱ ፈቃድና እውቀት መምራት ይችላል ወደሚል እምነት ተሸጋገረ፡፡
በመካከለኛው ዘመን ሰው ተስፋውን በአምላክ ጥሎ የራሱን ማንነት ረስቶ ነበር፡፡ በዚያ ዘመን ሰው ስለራሱ ማንነት ያንቀላፋበት ጊዜ ነበር፡፡ ከህዳሴው ዘመን ጀምሮ ግን ሰው ለረጅም ዘመን ከአንቀላፋበት ነቃ - ራሱን ማስተዋል ጀመረ፡፡ ወደራሱ በተመለከተ ቁጥር በሌላ ኃይል ከመተማመን ይልቅ የራሱ ኃይል ከምንም ነገር በላይ ሊያደርገው እንደሚችል አሰበ፡፡ በሳይንሳዊ እውቀት ምስጢሩን የተረዳውን ተፈጥሯዊ ሥርዓት በራሱ አቅም መግዛትና ለራሱ ጥቅም ማዋል እንደሚችል ድፍሩቱን ማሳየት ጀመረ፡፡
ይህ የህዳሴው ዘመን መንፈስ ነበር - በራሱ የመተማመን መንፈስ! የህዳሴው ዘመን ፍልስፍና የዘመናዊ ፍልስፍና መግቢያ በር ነው፡፡ ሙሉ ትኩረት የሰጠውም የሰው ልጅ ተፈጥሮን የመለወጥ አቅም ላይ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት የህዳሴው ዘመን ፍልስፍና ሰባዊነት - Humanism የሚል መጠሪያ አገኘ፡፡ እንደ ሉዶቪቾ ቫይቪስ (Ludovico Vives) ፣ ፔትሪስ ራመስ (Petrus Ramus) እና በርናርዲኖ ቴሎሶ (Bernardino Telesio) የመሳሰሉት ሰባዊ አስተሳሰብን በቀደምትነት ያራመዱ ፈላስፋዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ፈላስፋዎች የሰው ልጅ አጋዥ ሣያስፈልገው በራሱ አቅም የተፈጥሮን ኃይል ቀልብሶ ራሱን የበላይ አድርጐ መኖር ይችላል የሚል ከፍተኛ እምነት ነበራቸው፡፡ በዚህ አቋማቸው ሰውን አቅመ - ቢስ ያደረጉ እምነቶች ላይ አመጽ የጀመሩ ፈላስፋዎች ለመሆን ቻሉ፡፡ ሳይንስ ያመጣውን መነቃቃት ተከትሎ ሰባዊያን ያመጡት ፍልስፍና ለጨለማው ዘመን ማብቂያና የብርሃን ዘመን መምጣት የተበሠረበት ፍልስፍና ለመሆን ቻለ፡፡
ሳይንስ በፈጠረላቸው መደላድል ላይ ተመሥርተው ፍራንሲስ ቤከንና ቶማስ ሆብስ የተባሉ ፈላስፋዎች ሰው ከህዋ ጋር ያለውን ግንኙነት በእውቀት ላይ የተመሠረተ ሊሆን እንደሚገባው በማስገንዘብ የተፈጥሮን እንቅስቃሴና አጠቃላይ ሥርዐተ - ህጉን ማወቅ የሰው ልጅ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡በተለይ ለሆብስ የተፈጥሮ ህግ መታወቅ ከተቻለ ሰው ህጉን እንደፈቃዱ እያስተካከለ መኖር እንደሚችል እምነቱን ገለፀ፡፡
እነ ቶማስ ሆብስ ሁሉን ነገር ቁሳዊ አደረጉት፡፡ ህሊና-ሀሳብ - በእንቅስቃሴ ላይ ያለ ቁስ ነው፤ እግዚአብሔርም ቢሆን ቁስአካላዊ ነው፤ መንፈሳዊ የሚባል ነገር የለም የሚል እምነት ማራመድ ጀመሩ፡፡
በእንደዚህ አይነት አመለካከቶች ተጋግሎ የነበረው የሰባዊነት ፍልስፍና ሳይታሰብ መቀዝቀዝ ጀመረ፡፡
ለምን ??? ይቀጥላል..
@zephilosophy