የትኩረት መዛባት
በዚህ ማህረሰብ ውስጥ “ተመልከት የእኔ ሕይወት ከአንተ ሕይወት የበለጠ ያማረ ነው” በሚሉ በማህበራዊ ድረ- ገፆች በሚተላለፉ መልዕክቶች በኩል ጭንቀት፣ ፍርሃት፣ የጥፋተኝነት ስሜት ወዘተ... የመሳሰሉት አሉታዊ ልምዶች ያሉት ትውልድ እየፈራ ነው፡፡
ሰዎችም ሆነ የቲቪ ማስታወቂያዎች የመልካም ሕይወት ቁልፉ አሪፍ ስራ ማግኘት፣ ወይም ዘናጭ መኪና ወይም ቆንጆ ሴት ጓደኛ ያለህ መሆን እንደሆነ እንድታምን ይፈልጋሉ፡፡ አለም ያለማቋረጥ የሚነግርህ ነገር፣ የተሻለ የሕይወት መንገድ የሚባለው ብዙ መግዛት፣ ብዙ ማግኘት ፣ ብዙ መዋብ እንደሆነ ነው፡፡ ስለዚህ ሁልጊዜ በተደጋጋሚ ስለሁሉም ነገር ግድ እንዲኖርህ በሚነገሩ መልዕክቶች ስለምትጨናነቅ ያለማቋረጥ አዲስ ቅንጡ ነገሮችን ስለመግዛት፤ የእረፍት ጊዜህን ውድ በሆኑ ቦታዎች ስለማሳለፍ የምታስብ ትሆናለህ ወይም ፋሽን ልብሶች እና ኮስሞቲክሶችን ስለመግዛት የምታስቢ ትሆኛለሽ።
እነዚህ ነገሮች ከባድ የበታችነት እና የጭንቀት ስሜት ከመፍጠራቸውም በላይ በማይገባ አይነት የማይረቡና የውሸት ከሆኑ ነገሮች ጋር የተጣበቅክ እንድትሆንና ሕይወትህን ሙሉ የማይጨበጥ ደስታና እርካታ ስታሳድድ እንድትኖር ያደርግሃል፡፡ የመልካም ሕይወት ቁልፍ ስለ ብዙ ነገሮች መጨነቅ ሳይሆን፣ ስለ ትንሽ ለዚያውም እውነት፣ አስቸኳይና አስፈላጊ ስለሆነው ነገር ብቻ መጨነቅ ነው፡፡
Mark Manson
@zephilosophy