☞
እራስህን ፈትሽ❗️
⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
📚ሱፍያን ኢብን ዑየይናህ ፦
"ቀኔ የሞኞች አይነት ከሆነ፣ ለሊቴ የጃሂሎችን ከመሰለ በተማርኩት ዒልም ምን ተጠቀምኩ?!"
[አኽላቁዐል ዑለማ ሊዐል ኣጁሪይ (44)]
☞ሸይኽ ዐብዱረዘቅ አል-በድር፦
☞ይህ ጣሊበል ዒልም ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ታላቅ ምክር ነው። ሰለፎች የተማሩት እውቀት በተግባራቸው ላይ ይስተዋል ነበር። እውቀታቸው በዒባዳቸው፣ በማህበራዊ ህይወታቸውና በስነምግባራቸው ላይ ይንፀባረቃል።
☞ልኩን ያወቀ ሰው አላህ ይዘንለት!
ታላቁ የሙስሊሞች ኸሊፋ የነበው ዑመር ኢብኑ ዐብዲልዐዚዝ ልጁ በአንድ ሺህ ዲርሀም የጣት ቀለበት እንደገዛ ሰማ። ወዲያውኑ ይህን ደብዳቤ ፃፈለት!
"በአንድ ሺህ ዲርሀም የጣት ቀለበት እንደገዛህ ሰምቻለሁ። ይህን ቀለበት ሽጠህ አንድ ሺህ የተራቡ ሰዎችን መግብበት። ለራስህ የነሀስ ቀለበት ግዛና በቀለበቱ ላይ "ልኩን ያወቀ ሰው አላህ ይዘንለት" ብለህ ፃፍበት!" አለው።
[ይህን ክስተት ቁርጡቢይ (አላህ ይዘንላቸው) በተፍሲራቸው ላይ ጠቅሰውታል (12/302)]
☞ሹዐይብ ኢብን ሐርብ፦
"ከሁለት አይነት ሰዎች ውጪ እንዳትቀመጥ! አብረኸው ስትቀመጥ ጠቃሚ እውቀት የሚያስተምርህና አንተም እውቀቱን የምትቀስምበት ወይም አንተ ጠቃሚ እውቀትን የምታስተምረውና የሚቀበልህ ከዚህ ውጪ ከሆነ ራቀው። ሽሸው!"
📚صفوة الصفوة
⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
https://t.me/abdurezaq27