↔ሴቶችና ሰላትን የተመለከቱ ህግጋት!!
★★★★★★☆☆☆★★★★
⇨ለሴት ልጅ ሰላት ውስጥ ድምፇን ከፍ አርጋ መቅራት ብይኑ ምንድነው?
"ሴቶችን የምታሰግድ ከሆነና ድምፅ ከፍ የሚደረግባቸው ሰላቶች ላይ የአላህን ቃል እስክታሰማቸው ድረስ እንዲሁም በሰሙትም ይጠቀሙ ዘንድ ድምፇን ከፍ አድርጋ መቅራት ይፈቀድላታል።"
📚ፈታዋ ኢብን ባዝ (12/131)
⇨ለሴቶች አዛንና ኢቃም ማለት ተደንግጓልን?
"ለሴት ልጅ ሀገሯ ላይም ሆነ መንገደኛም ብትሆንም አዛንና ኢቃም ማለት አይፈቀድም። ከመልእክተኛው ትክክለኛ በሆኑ ፈለጎች እንደተገኘው አዛንና ኢቃም ማለት ወንዶች ብቻ የሚለዩበት ተግባር መሆኑ ነው።"
📚ፈታዋ ኢብን ባዝ (10/356)
⇨ባለማወቅ ለሰላት ኢቃም ስትል የነበረች ሴት ወንጀለኛ ትሆናለች?
"ባለማወቅ የሰራችው በመሆኑ ወንጀለኛ አትሆንም። ኢቃምና አዛን ወንዶች የሚለዩበት ተግባር ነው። ይህን ካወቀች ዘንድ ወንጀለኛ እንዳትሆንና ቢድዓ ውስጥ እንዳትዘፈቅ ዳግም መተግበር የለባትም። ስለዚህ ኢቃም ማለትን መተው አለባት።"
🎙ኢብን ባዝ (ፈታዋ ኑሩን ዓል'ለ ደርብ)
⇨ሴት ልጅ ከሰላት ሰልፍ ጀርባ ብቻዋን ቆማ መስገድ ብይኑ ምንድነው?
"የምትሰግደው ከሴቶች ጋር በጀመዓ ከሆነና ከሰልፋቸው ጀርባ ለብቻዋ ከሰገደች ሰላቷ ትክክለኛ አይሆንም። ነገር ግን የምትሰግደው ከወንዶች ጋር ብቻ ከሆነ ከወንዶች ጀርባ ለብቻዋ ቆማ መስገዷ የተደነገገና ትክክለኛ ተግባር ነው።"
📚[ኢብኑ ዑሠይሚን መጅሙዓል ፈታዋ(13/39)]
https://t.me/abdurezaq27