አስቸኳይ!ውድ ባለአክሲዮኖቻችን!
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን፤ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ (አክሲዮን) ባለቤትነት መዝገቦች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሥር በተቋቋመ ማዕከላዊ የሰነድ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት በተዘጋጀ ኤሌክትሮኒክ ዘዴ የሒሳብ መዝገብ ሥርዓት መተካት ያለበት መሆኑን አሳውቆናል፡፡ በመሆኑም እርስዎም የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥርዎን (FAN or FCN)፣ የብሔራዊ መታወቂያ ኮፒ፣ የመኖሪያ አድራሻ፣ የአድራሻ ለውጥ አድርገው ከሆነ አዲሱን አድራሻ፣ ኢ-ሜይል፣ ስልክ ቁጥር እንዲሁም ባለአክሲዮኑ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት ከሆነ የታክስ መለያ ቁጥር (TIN) እና የወኪሉ ሰው ሙሉ መረጃ ስለሚያስፈልግ በሁሉም የባንካችን ቅርንጫፎች እየቀረባችሁ እንድትሰጡ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
አሐዱ፡ባንክ
ከብዙዎች ለብዙዎች#_ምዕራፍ ፪ _“ከአሐዱ ጋር ነኝ"
የአሐዱ፡ባንክ ማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
👉
https://linktr.ee/Ahadu_Bank